Skip to main content

Amharic Quicknotes 09-01-2023


በዚህ ቅዳሜ ኦገስት 26 በሚካሄደው ዓመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ አውደ ርዕይ እባክዎ ከእኛ ጋር ይሁኑ።

 

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦች አዲሱን የትምህርት አመት ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 ቀን 10 a.m. to 1 p.m. ድረስ በዌስትፊልድ ዊተን ሞል ተገኝተው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ስርዓቱ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችን እንዲሁም ካውንቲው ስለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች፣ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ መዝናኛዎች፣ ነጻ የክትባት ክሊኒክ እና ሌሎችንም እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው።

አድራሻ: Westfield Wheaton Mall, 11160 Veirs Mill Road, Wheaton.

ነጻ መጓጓዣ አለ፡ MCPS ከዝግጅቱ ቦታ ወደሚከተሉት MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደርሶ መልስ ነጻ የማመላለሻ አውቶቡሶችን ያቀርባል።

  • ሞንትጎመሪ ብሌር፡ Montgomery Blair, 51 University Blvd. ኢስት ሲልቨር ስፕሪንግ East, Silver Spring
  • ፔይንት ብራንች፡ Paint Branch, 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville
  • ጌትስበርግ፡ Gaithersburg, 101 Education Blvd., Gaithersburg
  • ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፡ Richard Montgomery, 250 Richard Montgomery Drive, Rockville

የመጀመሪያው ማመላለሻ ሸትል ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች 9፡00 a.m. ይነሳል። እና የመጨረሻው ማመላለሻ አውቶቡስ ከዌስትፊልድ ዊተን 2 p.m. ላይ ይወጣል።

 

 

እንኳን በደህና መጣችሁ!

 

ወደ 2023-2024 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ! ሰኞ፣ ነሐሴ/ኦገስት 28፣ MCPS ወደ 162,000 ለሚጠጉ ተማሪዎች በሩን ይከፍታል። ለመምህራን፣ ለሰራተኞች እና ለአስተዳዳሪዎች፣ ይህ ቀን ለወራት ስንጠብቀው እና በጋውን በሙሉ ስንዘጋጅበት የነበረ ቀን ነው።የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዘዳንት ካርላ ሲልቬስትሬ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና ሰራተኞችን ድስትሪክቱ አዲሱን የትምህርት አመት ሲጀምር እንኳን ደህና መጣችሁ ይላሉ።

 

የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ፎቷችሁን አጋሩ!

ለህጻናት መዋዕለ ሕፃናት የመጀመሪያ ቀንም ሆነ ሲንየር ተማሪዎችም ቢሆኑ፣ የትምህርት የመጀመሪያ ቀን ምንጊዜም ልዩ ነው። የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ጊዜዎን በማጋራት ደስታ እንድንላበስ ያግዙን! ሰራተኞች፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የሚወዷቸውን የት/ቤት የመጀመሪያ ቀን ቅጽበተ-ፎቶዎችን ሰኞ ኦገስት 28 እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የተመረጡ ፎቶዎች ከሰኞ ጥዋት ጀምሮ በዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይጋራሉ። ፎቶ መስጠት ማለት MCPS ድረ ገጽ ላይ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ እንደሚታተም ተስማምተዋል ማለት ነው። በኢሜል በመላክ ወይም በማህበራዊ አውታረመረቦች ላይ ለእኛ ምልክት በማድረግ ፎቶዎችን መላክ ይችላሉ።

ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ማድረስ እና ከትምህርት ቤት መመለስ፡ የትምህርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች እና ጊዜዎች

የትራንስፖርት ዲፓርትመንት 1,355 አውቶቡሶችን ሙሉ በሙሉ በአውቶቡስ ኦፕሬተሮች እና በአስተናጋጆች በማሟላቱ 1,193 የአውቶቡስ መስመሮችን በመሸፈን ለተማሪዎቻችን የምናቀርብ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን።

 

ወላጆች እና አሳዳጊዎች የሁሉንም ተማሪዎች ደህንነት ለማረጋገጥ ቀላል መመሪያዎችን እና ምክሮችን በመከተል የተመቻቸ የትምህርት አመት መክፈቻ ላይ መርዳት ይችላሉ።

 

የትምህርት ቤት አውቶቡስ መስመሮችን እና ጊዜዎችንደንቡን በማክበር መጓዝን ጨምሮ የትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓጓዣን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። በትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓዝ ለበለጠ መረጃ እባክዎን MCPS በይነመረብ ላይ ያለውን መጓጓዣ ድረገጽ ይመልከቱ።

 

MCPS 33 ርእሰ መምህራንን ተቀብሏል

2023–2024 የትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ 162,000 የሚጠጉ ተማሪዎች ሰኞ ኦገስት 28፥ ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ። 920 የሚጠጉ መምህራን እና 280 የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሰራተኞች የተቀጠሩ ሲሆን 33 አዳዲስ ርእሰ መምህራን፣ ለት/ቤታቸው አዲስ ርዕሰ መምህራን እና ተጠባባቂ ርእሰ መምህራን አዳዲስ ተማሪዎቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመገናኘትና ለመተዋወቅ በጉጉት ይጠባበቃሉ። እነዚህ መሪዎች የትምህርት ቤታቸው ማህበረሰብ እንዲያውቀው የሚፈልጉትን አስደሳች ወይም አዝናኝ እውነታ እንዲያካፍሉን ተጠይቀዋል። ከዚህ በታች አንብቧቸው።

አንደኛ ደረጃ (ኤሌሜንተሪ) ት/ቤቶች

ኦሊቪያ ኬ. ቤይሊ/Olivia K. Bailey፣ ተጠባባቂ፣ ሮክ ቪው

በኮሌጅ እያለሁ የሪዘርቭ ሰራዊት ተቀላቅዬ በኦፕሬሽን ኢራቅ ፍሪደም II ውስጥ አገልግያለሁ። ኢራቅ እያለሁ እና አሁንም ድረስ ለማድረግ የምወደውን—በማህበረሰብ ውስጥ ካሉ ልጆች ጋር መስራት።

ኢራይዳ ኤ. ቦድሬ-ዉድስ Iraida A. Bodre-Woods፣ ተጠባባቂ፣ ኢስት ሲልቨር ስፕሪንግ

ወላጆቼ ከዶሚኒካን ሪፑብሊክ የተሰደዱት በ1970ዎቹ ነው። እኔ በቤተሰቤ ውስጥ በዩኤስ የተወለድኩ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ።በአብዛኛው የአካዳሚክ ጉዞዬ፣ 27 አመታት የትምህርት ቆይታዬ ግማሹን ተማሪ፣ በኒውዮርክ ስቴት የመድብለ ቋንቋ/ሁለትዮሽ ቋንቋ መምህር ሆኜ አገልግያለሁ። 2021 ወደ ሜሪላንድ ከተዛወርኩ በኋላ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ወደ ስኬት በሚያደርጉት ጉዞ ለመደገፍ እድሉን አግኝቻለሁ።

ላቪና ካሪሎ/Lavina Carrillo፣ ተጠባባቂ፣ ሮክ ክሪክ ፎረስት

ዕድሜአቸው 11፣ 19 እና 23 የሆኑ ሦስት አስደናቂ ልጆች ያሉኝ ኩሩ ወላጅ ነኝ፣ እያንዳንዳቸው ስለ ሕይወት ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ይሰጡኛል። ከማፈቅረው ባለቤቴ ጋር፣ ጉዞ ማድረግ እና መቃኘትን፣ ትዝታዎችን መፍጠር እና እንደቤተሰብ ያለንን ትስስር ማዳበር እወዳለሁ።

ስቴፋኒ አር. ዲንጋ፣ ካቢን ብራንች

ለዶክትሬት ዲግሪዬ ሁሉንም ኮርሶቼን ጨርሻለሁ፥ እና ርእሰ መምህራን አስተማሪን በማቆየት ላይ ያላቸውን ተፅእኖ በተመለከተ የመመረቂያ ጽሁፍ በማጠናቀቅ ላይ ነኝ። ስፕሪንግ 2024 ላይ ለመከላከል እየጠበኩ ነው!

ሚሼል ኤል. ፎርቹን/Michelle L. Fortune፣ ስኖውደን ፋርም

የመጣሁት ከአስተማሪ ቤተሰብ ነው! እናቴ የአራተኛ ክፍል አስተማሪ ነበረች እና አባቴ ምሽት ላይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ያስጠና ነበር። ከስኖውደን ፋርም ማህበረሰብ ጋር ለመተዋወቅ በእውነት እጓጓለሁ!

ዳርሻን ኬ ጄን/Darshan K. Jain፣ ዳርነስታወን

ትምህርት ላይ ከመስራቴ በፊት፣ የስፖርት ጋዜጠኛ ስለነበርኩ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ለፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እግር ኳስ ቡድኖች ሠርቻለሁ።

ጄሰን ኤ. ጀፈርሰን/Jason A. Jefferson፣ ሼርዉድ

ያደግኩት Buffalo, N.Y. ሲሆን የሠራሁት STEM እና ሥርዓተ ትምህርት በማስተማር ነው፣ከቤት ውጭ ጊዜ ማሳለፍን፣ ፐዝሎችን በማጠናቀቅ ወይም ስፖርቶችን በመመልከት ጊዜ ማሳለፍ እወዳለሁ።

ሮዛ ኢዛቤል ሜንሳህ/Rosa Isabelle Mensah፣ ሮሊንግ ቴራስ

ቤተሰቤ ከዶሚኒካን ሪፑብሊክ የመጡ ናቸው፥ እና ከልጅነቴ ጀምሮ ማንጉ ማብሰል እና ማሬንጌ መደነስ ተምሬያለሁ። ከቤተሰቤ ጋር መጓዝ እና በተለይም ብሔራዊ ፓርኮችን ማሰስ እወዳለሁ።

ፓሜላ አር. ፓርከር/Pamela R. Parker ተጠባባቂ፣ ሞንትጎመሪ ኖልስ

አስተማሪ ከመሆኔ በፊት በአሜሪካ አየር መንገድ የጥሪ ማዕከል ውስጥ እሠራ ነበር። ወደ ቺካጎ፣ ዳላስ እና ሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ የቀን ጉዞዎችን የማደርገው በ$5 ብቻ ነበር።

ጄኒፈር ኤም. ሬደን/Jennifer M. Redden፣ በርኒንግ ትሪ

ሞኒክ ቢ. ሪስ/Monique B. Reese፣ አሽበርተን

በትምህርት ዘርፍ 22ኛ አመቴን የያዝኩ ሲሆን በት/ቤት አስተዳዳሪነት 16ኛ አመት እየገባሁ ነው። እንደ አስተማሪ ሆኜ ማገልገሌ እርካታ እና ደስታን ሰጥቶኛል።

ካትሪን ኤ. ሽዋርትዝ/Katherine A. Schwartz፣ ተጠባባቂ፣ ዉድፊልድ

ከባለቤቴ፣ ከሦስት ልጆቼ እና ከውሾቼ ጋር ከቤት ውጭ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ካያኪንግ እና በፈረስ ግልቢያ ጊዜ ማሳለፍ እወዳለሁ። በፈረስ ግልቢያ 10 ስቴቶች እና በሶስት የውጪ ሀገራት ደስታን አገኝቻለሁ።

ማርኩየታ (ረኔ) ሲንግልቶን/Marquetta (Renee) Singleton፣ ብራውን ስቴሽን

በትርፍ ጊዜዬ የሃሪ ፖተርን ፊልሞች ማየት፣ ተራቪያ ጨዋታዎችን መጫወት እና ከ11 አመት ልጄ ጋር አሳ ማጥመድ ያስደስተኛል። ልደቴን ሳከብር፣ በሚያማምሩ የመሬት ገጽታዎች ላይ ስካይዳይቪንግ ደስ ይለኛል!

ሻውንቴ ኤፍ. ስፓው/Shauntae F. Spaugh፣ ፎልስሚድ

ያደግኩት "Huntsville, Ala., the Rocket City" በሚገኝ ትልቅ የከብት ርባታ ውስጥ ሲሆን የጠፈር ተመራማሪ የመሆን ህልም ነበረኝ። እንደ አስተማሪ እና የማስተማር መሪነት የህይወቴ ተልዕኮ ተማሪዎች ህልማቸውን ከዋክብት ባሻገር አሻቅበው እንዲያሳድዱ መደገፍ ነው።

ናዲያ ጄ. ክላይን-ቴይለር/Nadia J. Kline-Taylor፣ ተጠባባቂ፣ ፖቶማክ

ባለፉት 22 ዓመታት በሦስት ስቴቶች እና በሁለት የትምህርት ቤት ደረጃዎች እያስተማርኩ ኖሬአለሁ። በትርፍ ጊዜዬ የድሮውን ቤቴን ከባለቤቴ ጋር እድሳት እንሠራለን።

ኒኮላ ኤ. ዋለን/Nichola A. Wallen፣ ጎሸን

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ኦፊሰር ስመለከት ዞር ብሎ ወደ እኔ ተመለሰ እና “ወ/ሮ ዋለን/Wallen!” አለኝ። በዚህ ጊዜ፣ እሱ ወደ እኔ ተጠግቶ ነበርና ቀና ብዬ ተመለከትኩት እና በፍርኃት ድምፅ  “አቤት” ብዬ መለስኩለት። እሱም በደስታ ስሜት፣ “እኔ ነኝ! በስላይጎ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአስተማሪዎቼ አንዷ ነበርሽ።” ፈገግ እያለ፣ በአይኖቹ በሥስት እና በእንክብካቤ ሲመለከተኝ፣ በአንድ ወቅት የ12 አመት ተማሪ እንደነበረ እና አሁን የ31 አመት እድሜ ያለው ፖሊስ መሆኑን ተረዳሁ። በሚገርም ሁኔታ እርጅና ተሰማኝ፣ ግን ደግሞ ኩራት ተሰማኝ። መምህራን ከፊታችሁ ያለው ትንሽ ልጅ አድጎ ትልቅ ሰው እንደሚሆን አትርሱ። እናንተ በጎነትን እና አዎንታዊነትን ወደ እነርሱ ስታንቆረቁሩ እነርሱ መልሰው ወደ አለም ሁሉ ያፈሳሉ። እናንተን እና እናንተ ያሳደራችሁባቸውን ተፅእኖ ያስታውሳሉ።

ትራቪስ ጄ. ቪይቤ/Travis J. Wiebe፣ ሶመርሴት

እኔ የተጓዥነት ጉጉት ያለኝ ስለሆንኩ በየዓመቱ ቢያንስ ሁለት አዳዲስ አገሮችን ለመጎብኘት እሞክራለሁ። በዚህ ዓመት ወደ ደቡብ አፍሪካ የመሄድ እቅድ አለኝ፤በዚያውም ፈረንሳይን እና ጣሊያንን እጎበኛለሁ።

ኤስ. ፒተር ያንግ II/S. Peter Young II፣ ዊይንጌት

ወጣት በነበርኩ ጊዜ ስምንት አመት ቧልሩም ዳንስ/ballroom dancing እንደወሰድኩ ብዙ ሰዎች አያውቁም!

መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

አህመድ አዴሌካን/Ahmed Adelekan፣ ተጠባባቂ፣ ቤንጃሚን ባነከር

እኔ የመጣሁት አባቴን፣ እህቴን፣ ባለቤቴን እና የአጎት/አክስት ልጆችን ጨምሮ ከአስተማሪዎች ቤተሰብ ነው ። በትምህርት ዘርፍ መስራቴ እኔና ቤተሰቤን በመንግስት አገልጋይነት ጉልህ እርካታ አስገኝቶልናል። አስተማሪ ከመሆኔ በፊት በሆሊውድ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከበርካታ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እና ፊልሞች ጀርባ እሠራ ነበር።

ፓትሪክ ኤች ቢሎክ/Patrick H Bilock፣ ተጠባባቂ፣ ሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል

የምትችሉትን ያህል ብዙ ነገሮችን አስሱ! ፍላጎቶችህ ወዴት እንደሚወስዱህ አታውቅም ይህም ወደ ዕድሜ ልክ ፍላጎት ሊመራህ ይችላል… እና ሁልጊዜ እራስህን ሁን።

ዶ/ር ናታሻ ኤች. ቡምስ/Booms፣ ተጠባባቂ፣ ኦዴሳ ሻነን

የተወለድኩት በአንኮሬጅ፣ አላ ነው/Anchorage, Ala.። ቤተሰቦቼ ወደ ሜሪላንድ የመጡት የሦስት ዓመት ልጅ እያለሁ ነው።

ዊልያም አር. ከረንሴ/William R. Currence፣ ተጠባባቂ፣ ሮዛ ኤም. ፓርክስ

ከቤት ውጭ ማሳለፍ እወዳለሁ! ያደግኩት አናፖሊስ ውስጥ ሲሆን፣ሠመር በውሃ ላይ፣በፎል እና ዊንተር ላይ ጫካ ውስጥ እየተዘዋወርኩ አሳልፋለሁ፣እና በስፕሪንግ ወቅት ቤዝቦል ዳይመንድ ላይ አሳልፋለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከሁሉ የላቀ የነበረ “አንድ ቀን የራሱን የዓሣ ማጥመድ ወይም የአደን ትርኢት ሊኖረው ይችላል!”

ዶ/ር ካርላ ኤም ማክኔል/Dr. Carla M. McNeal፣ ሀሊ ዌልስ

የእኔ አስደሳች እውነታ ከሚስ አሜሪካ በፊት ሚስ አላባማ በመሆን ተወዳድሬ ነበር፣ እና ችሎታ ስላለኝ የኦፔራ ዘፈን ሙሉ በሙሉ በጣሊያንኛ ዘፍኛለሁ።

ብራንዲ ኬ ኦቨርተን/Brandi K. Overton፣ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ጁኒየር

ዩኒቨርሳል የቺርሊዲንግ ማህበር አባል እንደመሆኔ፣ በለንደን፥ ኢንግላንድ በአዲስ አመት የሰልፍ ትርኢት ቀን በሁለት አጋጣሚዎች የጎዳና ላይ ትርኢት አሳይቻለሁ።

አንጀሊካ ኤል. ሪቫስ-ስሚዝ/Angelica L. Rivas-Smith፣ ተጠባባቂ፣ ዊልያም ኤች. ፋርኩኸር

2008 ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ስመጣ NIH ማህበረሰብ ኦርኬስትራ ውስጥ የመጀመሪያ ወንበር ተቀምጬ string ሙዚቀኛ በመሆን ቫዮሊን እና ቫዮላ/violin and viola እየተጫወትኩ ነው ያደግኩት። ከባለቤቴ እና የ10 አመት ሴት ልጃችን እና የ8 አመት ወንድ ልጃችን ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ እወዳለሁ።

ዶ/ር ዳሺያ ኤፍ. ስሚዝ/Dr. Dacia F. Smith፣ ፎረስት ኦክ

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች

ቪኪ ፒ. አደምሰን/Vickie P. Adamson፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ

እኔ መጀመሪያ ከሳውዝ ካሊፎርኒያ ስሆን L.A., ስላደግሁበት ሁኔታ እና UCLA ስለመማሬ እና በዚያ ስላጋጠመኝ የዘር እና የፖለቲካ ገጽታ ልብ ወለድ ጽፌአለሁ። ጽሑፍ የእኔ ፍላጎት ሆኖ ይቀጥላል፣ እንዲሁም የጽሑፍ ፍቅርን እና የራስን ታሪክ ለተማሪዎች የመንገርን አስፈላጊነትን ማዳበር እወዳለሁ።

ክሪስቶፈር ጄ. አሰየንዞ/Christopher J. Ascienzo፣ ተጠባባቂ፣ ኮሎ. ዛዶክ ማግሩደር 

ዕድሜ ልኬን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ እንደመሆኔ፣ C&O Canal እና Seneca Greenway የመሳሰሉ ሃይክ ማድረግ እና የሩጫ መንገዶች ላይ መሮጥ እወዳለሁ። ለእኔ ጥሩ ቅዳሜና እሁድ የምለው ከ14 ዓመቷ ሴት ልጄ እና የ10 አመት ሀውንድ የሚባል ውሻችን ጋር በሱጋርሎፍ ተራራ/Sugarloaf Mountain ዙሪያ ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪነት ስድስተኛ አመቴ ነው እና ህልሜን እየኖርኩ ነው። የሶሻል ስተዲስ አስተማሪ እንደመሆነ መጠን፣ ሁሉም ሰው በተቻለው መጠን ይህንን ዓለም/ምድር እንዲያይ እመክራለሁ። የራሴን ሃሳብ ለመከተል እሞክራለሁ — ስልኬን አስቀምጬ ወደ ውጭ መውጣት!

ዶ/ር ዴብራ ኬ. ሙጌ/Dr. Debra K. Mugge፣ ተጠባባቂ፣ ዊተን

ለዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲስ አይደለሁም። ያለፉትን ሰባት ዓመታት በርእሰመምህርነት ካገለገልኩ በኋላ 2021 ላይ ከ MCPS ጡረታ ወጥቻለሁ። እንደገና ከWHS ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ጋር ለመስራት እጓጓለሁ። Go Knights!

ቪልማ ሲ. ነጄራ/Vilma C. Nájera፣ ዋትኪንስ ሚል

ከ15 በላይ ማራቶን ሮጬያለሁ እና የቦስተን ማራቶንን ሶስት ጊዜ ሮጫለሁ፤ አንድኛውን ጊዜ (በወረርሽኙ ወቅት ማለት ይቻላል) ሮጫለሁ። መክሰስ እወዳለሁ … ፋንዲሻ እና ቺፕስ እና ሳልሳ የእኔ ተወዳጅ መክሰስ ናቸው። ሁለት ቋንቋ መናገር (እንግሊዘኛ/ስፓኒሽ) አቅም ከሚሰጡኝ ነገሮች አንዱ ነው!

ሻናይ ኤ. ስኔድ/Shanay A. Snead፣ ጄምስ ሁበርት ብሌክ

ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ጠቃሚ ምክር፡ በዚህ አመት ምንም ነገር ወደኋላ እንዲይዛችሁ አትፍቀዱ። ዓመቱን በክፍት አእምሮ ይጀምሩ እና ከእርስዎ የሚጠብቁትን እና ከሌሎች የሚጠበቁትን እንዴት እንደሚሻገሩ ይመልከቱ።

ልዩ ት/ቤቶች

ዶ/ር ሊዛ ሚሼል ገይላርድ-ጆንስ/Dr. Lisa Michelle Gaillard-Jones፣ ሮክ ተሬስ

ሁሉም ልጆች መማር እንደሚችሉ አምናለሁ! ይህ ከአስተማሪዎች - ከምሁራን ፣ ከትምህርት ቤት ካውንስለሮች ፣ ከአስተዳዳሪዎች እና ሱፐርኢንተንደቶች ቤተሰብ በመሆኔ ይሄ ዋና እምነቴ ነው። ሁሉም ልጆች በየቀኑ የእኛ ምርጥ ነገሮቻችን ይገባቸዋል!

ቨርቹወል አካደሚ

ጃኪ አር. ዴሉሲያ/Jackie R. DeLucia፣ ተጠባባቂ፣ ሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ—አፐር ስኩል

እኔ በልቤ እዚሁ ተወላጅ እንደሆንኩ ይሰማኛል! ተወልጄ ያደኩት ኖርዝ ኢንዲያና ነው፣ ግን ላለፉት 16 ዓመታት እንደቤቴ የምቆጥረው ጌትስበርግን ነው። እኔና ባለቤቴ ሰባት ልጆች እና ሁለት ድመቶች የሚያምር የተዋሃደ ቤተሰብ አለን። ትልልቆቹ ልጆቻችን የማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ ታናናሾቹ ልጆቻችን ደግሞ MCPS ፈረንሳይኛ ኢመርሽን ፕሮግራም 4ኛ ክፍል፣ 5ኛ ክፍል እና 6ኛ ክፍል ናቸው።

ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአደጋ ጊዜ መረጃ እንዴት ማግኘት  እንደሚቻል

 

MCPS ስድስቱን የአሠራር ሁኔታ አማራጮችን ለማሳየት የቀለም ኮዶችን ይጠቀማል፦

 

ስለ ቀለሞች እና ትርጉማቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት MCPS የስራ ሁኔታ እና የቀለም ኮዶች ድረ-ገጽ ይጎብኙ። ተማሪዎች በተቻለ መጠን ከጥቂት የትምህርት ማቋረጦች የበለጠ እንዳይገጥማቸው፣ MCPS በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ወደ ቨርቹወል ትምህርት (MCPS Operating Status Purple: Virtual Learning Day) በመሸጋገር ትምህርታቸው እንዳይጓደል ጥረት ያደርጋል።

 

MCPS አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ቨርቹወል ትምህርት

 

ወላጆች እና አሳዳጊዎች ስለ MCPS ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ።

ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ይተላለፋሉ።

ስለ ትምህርት ቤቶች ስራ የአደጋ ጊዜ መረጃ ይሰጣል። ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ይላካሉ/ይተላለፋሉ።

  • ማህበራዊ ሚዲያ

Twitter http://twitter.com/mcps

Facebook https://www.facebook.com/mcpsmd

Instagram @mcps_md

  • MCPS የኬብል ቻነሎች/Cable Channels

ኮምካስት ቻነል 34፡ Comcast Channel 34

ቨራይዘን ፋዮስ ቻነል 36፡ Verizon Fios Channel 36

RCN Channel 89

  • የስልክ መረጃ መስመር፡ 301-279-3673
  • የአደጋ ጊዜ መረጃ ለማግኘት የአካባቢ ቲቪ እና የሬዲዮ ጣቢያዎችን ይከታተሉ።

 

ስለ ተማሪዎች ምግብ ጠቃሚ መረጃ

 

2023–2024 አዲሱ የትምህርት አመት፣ 58 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች በማህበረሰብ ብቁነት ደንብ (CEP) ይሰራሉ። በእነዚህ CEP ትምህርት ቤቶች የተመዘገቡ ተማሪዎች የቤተሰብ ገቢ ምንም ይሁን ምን ቁርስና ምሳ ሊያገኙ ይችላሉ። የሚሳተፉ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር እዚህ ማግኘት ይችላሉ።

 

(DFNS) የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ዲፓርትመንት፤ CEP በማይሳተፉ ትምህርት ቤቶች የተመዘገቡ ተማሪዎች ሁሉም ነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግብ ማመልከቻ ሞልተው እንዲያቀርቡ ያበረታታል።

 

MCPS የተማሪዎችን የጣዕም ምርጫ እና ተጨማሪ የአትክልት ተመጋቢዎች/ቬጀቴሪያን አማራጮችን ጨምሮ 2023-2024 የምግብ አገልግሎት ዝርዝሮችን (ሜኑ) ስናጋራችሁ ደስታ ይሰማናል።

 

ቤተሰቦች የልጆቻቸውን የትምህርት ቤት ምግብ ክፍያ ለመፈፀም፣ የቅርብ ጊዜ ግዢዎችን ለማየት እና ለአካውንቱ ቅድመ ክፍያ ለማድረግ MySchoolBucks አማራጭ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ።

 

ስለ ምግብ ዋጋ፣ እንዴት ወደ ልጅዎ አካውንት ገንዘብ እንደሚከፍሉ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል ድረ-ገጽ ይጎብኙ። በዚህ ፎል/መኸር ስለ አዲሱ እና ወቅታዊ የምግብ ዝርዝር/ሜኑ የማህበረሰብ እና የተማሪዎች ግብረመልስ አስተያየት ለመስማት እንፈልጋለን።

 

ሥር የሰደደ ከትምህርት ቤት መቅረትን ለመከላከል MCPS ት/ቤት የመገኘት የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል።

ኦገስት 22 በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ MCPS ትምህርት ቤት የመገኘትና በሥነ ስርአት ትምህርት የመከታተል የድርጊት መርሃ ግብር መጀመሩን አስታውቋል፣ “አሁን ሁሉም አንድ ላይ፣ በት/ቤት አንድ ላይ፣ አብሮ መማር፣ አንድ ላይ ማሳካት” በሚል መርህ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ ዘርፈ ብዙ ተነሳሽነት የተማሪዎችን ሥር የሰደደ ከትምህርት ቤት የመቅረት ችግር የሚፈታ ሲሆን በዲስትሪክቱ ውስጥ ባሉት ተማሪዎች መካከል ትምህርት ቤት መገኘትና መማርን ወጥነት ባለው አሠራር ያበረታታል። በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ስልቶችን በመተግበር እና በባለድርሻ አካላት መካከል ትብብርን በማጎልበት፣ MCPS የተማሪዎችን ት/ቤት የመገኘትና ትምህርት የመከታተል  እንቅፋቶችን ለመቀነስ እንዲሁም ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ለማበረታታት የታለመ ነው።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተማሪዎች ትምህርት ቤት መገኘት ላይ ያስከተለውን ተጽእኖ በመገንዘብ፣ MCPS በተጨማሪም ስለ ፍትሃዊነት እና አካታችነት ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ አፅንዖት በመስጠት በፀረ-ዘረኝነት ስርዓት ኦዲት ላይ ተለይተው የታወቁ የባህል እና የትምህርት ቤት ድባብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል።

ት/ቤት የመገኘት የድርጊት መርሃ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

በመረጃ የተደገፈ ፋውንዴሽን/Data-Driven Foundation፡ MCPS በትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረተ ከትምህርት ቤት የመቅረት መረጃዎችን፣ የተማሪ ቡድኖችን፣ የሳምንቱን ቀናት፣ ዲፓርትመንቶችን፣ ኮርሶችን፣ አስተማሪዎችን እና የትምህርት ክፍለጊዜዎችን ያካተተ አጠቃላይ ትንተና ያደርጋል። ይህ ትንተና ዋና መንስኤዎችን ለይቶ ለማወቅ እና የተማሪዎችን የት/ቤት ክትትል ለማሻሻል የታለሙ ጣልቃገብነቶችን ለማዘጋጀት ይረዳል።

ትምህርት ቤትን መሠረት ያደረገ በመረጃ ላይ የሚደገፍ እቅድ እና ክትትል፡ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት በሚፈልገው አይነት የተስተካከል፣ ሊለካ የሚችል፣ ሊከናወን  የሚችል፣ አስፈላጊ፣ አግባብነት ያለው፣ የጊዜ ማእቀፍ ያለው፣ አካታች እና ፍትሃዊ ግቦች ያሉት የክትትል እቅድ ያዘጋጃል። መደበኛ ትምህርት ላይ የመገኘት መረጃዎችን የመገምገም ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፣ የንዑስ ቡድን ትምህርት ላይ መገኘት ይተነተናል፣ እና ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ግለሰብ ተማሪዎች ተለይተው ይታወቃሉ።

ማዕከላዊ አገልግሎት መዋቅር፣ ድጋፎች እና ተነሳሽነት፡ MCPS ትምህርት ቤት በመደበኛነት ስለመገኘት አስፈላጊነት ግንዛቤን ለማሳደግ በመላው የትምህርት ሥርአቱ ስለ ት/ቤት ክትትል አስፈላጊነት የማስገንዘብ ዘመቻ ይጀምራል። በተጨማሪም፣ አስተዳዳሪዎች፣ ካውንስለሮች፣ ሶሻል ዎርከርስ፣ የተማሪ ሰራተኞች፣ የወላጅ ማህበረሰብ አስተባባሪዎች፣ የትምህርት ቤት ነርሶች እና ት/ቤት የመገኘት ተቆጣጣሪ ፀሃፊዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የስራ ሀላፊዎች የተወከሉ አባላት በመደበኛነት ትምህርት ቤት መገኘት እና ትምህርት መከታተልን ለማሻሻል ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን በመተባበር ይረዳሉ።

"ለእያንዳንዱ ተማሪ በአካዳሚክ ስኬታማ ለመሆን እኩል እድሎች ሊሰጥ እንደሚገባ እናምናለን፣ እና ትምህርት ቤት በመደበኛነት መገኘት ይህንን ለማሳካት ወሳኝ ነገር ነው" ብለዋል ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት። "ባለ ብዙ ፈርጅ ሁለገብ አሠራራችንን በመተግበር የሁሉንም ተማሪዎቻችንን ደህንነት እና የትምህርት እድገት የሚደግፍ ትምህርት ላይ የመገኘት እና የመማር ባህልን ለማዳበር አላማ እናደርጋለን።"

MCPS የእቅዱን "Future-Ed.org" ፕሌይ ቡክ በማዳበር ረገድ ያለውን ጉልህ ሚና ይገነዘባል። የመግለጫ መጽሐፉ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ላይ የመገኘትን መጠን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማሻሻል ጠቃሚ ግንዛቤዎችን እና ምርጥ ልምዶችን ይሰጣል።

MCPS ትምህርት ቤት የመከታተል/የመገኘት የድርጊት መርሃግብር እቅድ ለማንበብ፣እባክዎ ይህን አገናኝ/ሊንክ ይጎብኙ

ሥራውን የሚመራው ቁልፍ ውሂብ/ዳታ

ሥር የሰደደ መቅረት ማለት ያለፈቃድ በአንድ የትምህርት አመት ውስጥ 18 ወይም ከዚያ በላይ ቀናት ከትምህርት ቤት መቅረት ነው (10%)።

2018-2019 እና 2022-2023 የትምህርት ዓመታት ሥር የሰደደ መቅረት መረጃ

2018-2019 የትምህርት አመት - 30,349 ተማሪዎች ረዥም ጊዜ ከት/ቤት ቀርተዋል  (19.55%)

2022-2023 የትምህርት ዓመት – 42,863 ተማሪዎች ረጅም ጊዜ ትምህርት ቤት አልተገኙም (27%)

ሥር የሰደደ ከት/ቤት መቅረት በደረጃ

 

2018-2019 በጠቅላላ ሥር የሠደደ መቅረት የሚያበዙ ቡድኖች በመቶኛ  ስሌት

2022-2023 ከጠቅላላ ንዑስ ቡድኖች ውስጥ አዘውትረው ከትምህርት ቤት መቅረት የሚያበዙ በመቶኛ ሲሰላ

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

29.48%

35.79%

መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

14.51%

22.18%

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (ቅድመ መዋእለ ህጻናትን/Pre-K) ሳይጨምር

12.00%

19.99%

ቅድመ–ሙዓለ ህጻናት-Pre-K

31.78%

45.63%

 

MCPS እና MedStar Health ኢኖቬቲቭ የስፖርት ህክምና አጋርነት ጀምረዋል

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MPCS) እና MedStar Health በካውንቲው የፎል ስፖርት ልምምዶች እና ሙከታዎች ቀን ኦገስት 9፤ የትምህርት ቤቶችን የስፖርት ህክምና ፕሮግራም ለማሻሻል አዲስ አጋርነት መመስረታቸውን አስታውቀዋል።

 

ከመጪው 2023-2024 የትምህርት አመት በፊት፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MPCS) የተቀጠሩት አዲስ የተመሠረተው 12 ወራት ሠረተፊኬት ያላቸው የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ቡድን በሁሉም 25 የካውንቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሥራ ጀምሯል። ግባቸው በሁሉም የአትሌቲክስ ፕሮግራሞች ውስጥ ለተማሪ-አትሌቶች ትኩረት እና የተሻሻለ እንክብካቤን መስጠት ነው።

 

MCPS የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ዶ/ር ጄፍ ሱሊቫን እንዳሉት "በእያንዳንዱ 25 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሠርተፊኬት ያላቸው የሙሉ ጊዜ የአትሌቲክስ አሰልጣኝን የሚያካትት ኢኖቬቲቭ የስፖርት ህክምና ፕሮግራማችንን በፍጥነት ለማስጀመር እንጓጓለን" ብለዋል። “የትምህርት ቤቶቻችን መሪዎች ለደህንነት ስላላቸው ቁርጠኝነት ምስጋና ይግባውና ከሪጅኑ ትልቁ የጤና ጥበቃ ስርዓት ከሜድስታር ሄልዝ "MedStar Health" ጋር በመተባበር የተማሪ-አትሌቶችን ጉዳት፣ መከላከል፣ ማገገሚያ እና ሌሎችንም ሁኔታዎች ለመገምገም እና ለማከም የሚረዱ የህክምና ባለሙያዎች አሁን በሰራተኞቻችን መካከል ይገኛሉ።”

 

MCPS፣ የሜሪላንድ ትልቁ የትምህርት ስርዓት ሲሆን፣ የዚህ አይነት የስፖርት ህክምና አጋርነትን ከሪጅኑ ትልቁ የስፖርት ህክምና ተቋም እና ትልቁ የአጠቃላይ የጤና እንክብካቤ ተቋም "MedStar Health" ጋር ለመመስረት በስቴቱ የመጀመሪያው ነው።

 

እንደ ኢኖቬቲቭ አጋርነት አካል፣ MedStar Health ሐኪሞች እና የስፖርት ህክምና ክሊኒኮች በትምህርት አመቱ በሙሉ በት/ቤት ለሚገኙ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የህክምና ክትትል እና ድጋፍ ይሰጣሉ። እንዲሁም፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ አትሌቶች  MedStar Health ታዋቂ የስፖርት ህክምና አገልግሎቶችን በቀጥታ ያገኛሉ። እነዚህ አገልግሎቶች፤ የላቀ ስፖርት ኦርቶፔዲክስ፣ ዋሽንግተን ዊዛርድስ፣ ዋሽንግተን ካፒታልስ፣ ዋሽንግተን ምይስቲክስ፣ ባልቲሞር ሬቨንስ፣ ባልቲሞር ኦሪዮልስ፣ እና ጆርጅታወን ዩኒቨርሲቲ፣ ታውሰን ዩኒቨርሲቲ፣ እና ጎላዴት ዩንቨርስቲ የመሣሰሉ ከፍተኛ የኮሌጅ ፕሮግራሞችና የሪጅኑ ከፍተኛ የሙያ ስፖርት ቡድኖች ጥሩ ተቀባይነት አላቸው።

 

Katie Brodka, MS, ATC በዋሽንግተን ዲ.ሲ., ሪጅን የሜድስታር ጤና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ አገልግሎቶች ኃላፊ እንደገለጹት “ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና MedStar Health አብረው በመስራት፣ ቤተሰቦች የተማሪ-አትሌት ተጫዋች በሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ስለሚያገኙት እንክብካቤ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ይችላሉ” ብለዋል።

 

"በሪጅኑ ውስጥ የስፖርት ህክምና መሪ እንደመሆናችን ከብዙዎቹ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዳዲስ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ጋር ሠርተናል፣ እናም ከእነርሱ ጋር ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ደህንነትና ከተጓዳኝ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበርን ለመቀጠል እንጓጓለን።"

 

ወደ አዲሱ የትምህርት አመት ስንገባ፣ አጋር የስፖርት ህክምና ሰጪዎች የአስቸኳይ/የአደጋ ጊዜ የድርጊት መርሃ ግብር (EAP) መሳሪያዎችን ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች በማዘመን፣ ለ25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ምቹ የመማር አከባቢን በመፍጠር እና ለፈቃድ አስፈላጊ የሆኑ የመገምገም እና የህክምና ፕሮቶኮሎችን በማቋቋም ላይ ያተኩራሉ።

 

ማስታወሻ፦ ParentVUE አካውንት ይመዝገቡ

 

ቤተሰቦች በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ParentVUE እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ።

ParentVUE ማለት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኦንላይን የቤተሰብ ፖርታል (portal) ሲሆን የሚያገለግለውም እንደ ተቀዳሚ የግንኙነት መስመር በመሆን የት/ቤቶች ውጤቶችን ለማየት፣ ትምህርት ላይ መገኘትን ለመከታተል፣ የተለያየ ቀጠሮ/መርሃ ግብር ለማስያዝ፣ ወደ myMCPS Classroom ለመግባት እና ለሌሎችም ነገሮች የሚያገለግል ነው።

 

ParentVUE ሁሉንም ከት/ቤት ጋር የሚገናኙ መረጃዎችን፣ዳታ/ውሂብ ለሁሉም የተማሪ አትሌቲክስ እና የልዩ ፕሮግራሞች መመዝገቢያ፣ እንዲሁም ከአስተማሪዎች ጋር ለመገናኘት እና የተማሪዎን መረጃ በየአመቱ ለማረጋገጥ የሚያስችል መረጃ ይሰጣል።

 

ከዚህ በታች ስለ ParentVUE ፈጣን መመሪያ፣ እንዴት መመዝገብ፣ እንዲሠራ መክፈት፣ እና ስለ ParentVUE ድጋፍ ማግኘት የሚገልጹ ርእሶች ናቸው። መመሪያው በሰባት ዋና ዋና ቋንቋዎች ይገኛል።

 

ParentVUE ፈጣን መመሪያ ላይ የሚዳሰሱ ርዕሶች

የተተረጎሙ ParentVUE ፈጣን መመሪያዎች

·        ስለ ParentVUE አላማ ማብራሪያ

·        ParentVUE ባህሪዎች

·        ParentVUE ለመጫን QR ኮድ iOS እና Android የስልክ መሳሪያዎች

·        ParentVUE የቃላት የይዘቶች ትርጉም

·        ParentVUE አካውንትን ለመክፈት  (activate) የሚጠቅሙ መመሪያዎች

·        ParentVUE ለመጠቀም የሚያስችሉ ኦንላይን ምዝገባዎች

·        ParentVUE ድጋፍ መመሪያ ጋር ማገናኛ

·        እንግሊዘኛ (English)

·        ስፓንሽኛ-Spanish

·        ኮሪያንኛ (Korean)

·        Chinese (ቻይንኛ)

·        Amharic (አማርኛ)

·        Portuguese (ፖርቹጋልኛ)

·        ፈረንሳይኛ (French)

·        Vietnamese (ቬትናሚኛ)

ስለ "ParentVUE" የድጋፍ መመሪያ

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ወቅታዊና የተሻሻሉ መረጃዎች

 

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት አለባቸው። ከ 6 ኛ ክፍል በኋላ በ MCPS የተመዘገቡ ተማሪዎች የ SSL መስፈርትን በማጣጣት-የሚያካክስ እፎይታ ያገኛሉ። የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 2023-2024 የትምህርት አመት በተማሪ የአገልግሎት ትምህርት (SSL) ዕድሎች በመሳተፍ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በይነመረብ - MCPS SSL webpage (www.mcps-ssl.org) - ዝርዝር ላይ የተገለጹትን SSL መመሪያዎችን ከሚከተሉ ኤጀንሲዎች ጋር  ቨርቹወል/የርቀት እድሎችን በመጠቀም SSL ሰዓቶችን ማግኘት አለባቸው።

 

ተማሪዎች SSL የሚሳተፉባቸውን ድርጅቶች እና እድሎችን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የበጎፈቃደኝነት ማእከል ድረገጽ "Montgomery County Volunteer Center website" ላይ ሊያገኙ ይችላሉ። እነዚህ ድርጅቶች እና እድሎች MCPS SSL ሰማያዊ ቀለም የመመረቂያ ቆብ ምልክት ተለይተዋል።  SSL እድሎችን የሚሰጡ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቀባይ ድርጅቶችና ኤጀንሲዎች ወቅታዊ ዝርዝር በሙሉ በሚከተለው ፈጣን ማገናኛ/ሊንክ ላይ ይገኛል፡ https://bit.ly/SSLOpportunities እና https://bit.ly/VirtualSSL2020።

 

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኝነት ማእከል ድረ ገጽ ላይ ዝርዝራቸው ያልወጣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ላይ ለመሳተፍ፣ ተማሪዎች በግል SSL አክቲቪቲ መጠየቂያ ቅጽ (https://bit.ly/SSLPreApproval) ሞልተው አገልግሎት ከመጀመራቸው ቢያንስ ሁለት ሣምንት በፊት ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እንዲረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።

 

2023 ሠመር ላይ የተጠናቀቁ የተማሪ አገልግሎት SSL አክቲቪቲ ማረጋገጫ ማረጋገጫ ቅጾች በሙሉ (https://bit.ly/SSLReflection) በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሴፕቴምበር 29, 2023 ወደ ት/ቤቱ SSL አስተባባሪ መቅረብ አለባቸው። 2023 ሠመር እና 2023-2024 የትምህርት አመት ላይ የተሞሉ SSL ቅጾች በሙሉ  ከተወሰነው የመጨረሻ ቀን ሜይ 31, 2024 በፊት ወደ ትምህርት ቤቱ SSL አስተባባሪ መቅረብ አለባቸው።

 

የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 75 ሰአት የመመረቂያ መስፈርቶችን በማጠናቀቅ የሱፐርኢንቴንደንት SSL ሽልማት ለማግኘት እንዲሰሩ ይበረታታሉ። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመራቂ/ሲንየር ተማሪዎች 240 ወይም ከዚያ በላይ SSL ሰዓቶችን አገልግሎት በማጠናቀቅ ምስጋናና ሽልማት የሚገባው የአገልግሎት ሠርተፊኬት "Certificate of Meritorious Service" ከሀምራዊ መነሳነስ ጋር እንዲያገኙ እናበረታታለን። ለእነዚህ ሽልማቶች የሚያበቁና SSL ሰዓቶች የተመዘገቡባቸው ማንኛውም SSL አክቲቪቲ ማረጋገጫ ቅጾች ከኤፕሪል 5, 2024 በፊት ለትምህርት ቤቱ SSL አስተባባሪ መቅረብ አለባቸው።

 

ተማሪዎች https://bit.ly/SSLonVUE ላይ ያሉትን ደረጃ በደረጃ መመሪያዎች በመከተል SSL ሪኮርዳቸውን ሙሉ መረጃ Student/ParentVUE ላይ ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች SSL ቅጾችን፣ መመሪያዎችን፣ ሪሶርሶችን/ግብዓቶችን እና ሌሎችንም MCPS SSL Hub Students/Families (https://bit.ly/SSLHubMCPS) ላይ ማግኘት ይችላሉ።

 

ስለ SSL ፕሮግራም ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎን ለትምህርት ቤትዎ SSL አስተባባሪ ኢሜይል ያድርጉ (https://bit.ly/SSLCoordinatorsMS and https://bit.ly/SSLCoordinatorsHS) or the MCPS SSL office at SSL@mcpsmd.org.

 

SSL መመረቂያ መስፈርትን በተመለከተ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች እና ማሻሸያዎች 2023-2024 ለተማሪዎች/ለቤተሰቦች በሚተላለፉ መልዕክቶች ይደርሳቸዋል። የዚህ መልእክት ትርጓሜ በሚከተለው ፋይል ውስጥ ይገኛል።

 

 

ለዓመታዊ "GIVE Backpacks Campaign" ዘመቻ በመለገስ የተቸገሩ ተማሪዎችን ይርዱ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት እቃ መያዣ ቦርሳዎችን እና የት/ቤት አቅርቦቶችን ለማከፋፈል 12ኛው አመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ ልገሳ ያድርጉ።

$20 ለተቸገረ ተማሪ በትምህርት ቤት ቁሳቁሶች የተሞላ ቦርሳ፣ እርሳሶች/እስክሪብቶዎች፣ ከለሮች/የቀለም እርሳሶች፣ ማጣበቂያ ሙጫ፣ ማህደር፣ ፋይል መያዣ ባይንደሮችን እና ሌሎችንም የትምህርት መርጃዎች ጭምር መስጠት ይችላሉ።

የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በራሪ ወረቀቱን ለስራ ባልደረቦችዎ፣ ለቤተሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ፣ እርስዎ ለሚሠሩበት ኩባንያ እና ለማህበረሰብ አባላት በማጋራት ስለዚህ ዘመቻ በመቀስቀስና በማሰራጨት ያግዙን።

ስለ "GIVE BACKpacks" የበለጠ ይወቁ።

 

 

መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

ሐሙስ፣ ኦገስት 24— አርብ፣ ኦገስት 25 – ለመምህራን ሙያዊ ቀናት (መደበኛ የት/ቤት ካለንደር የሚከተሉ ትምህርት ቤቶች)

ሐሙስ፣ ኦገስት 24 — አርብ፣ ኦገስት 25–ትምህርት የማይሰጥባቸው ቀናት። ለተማሪዎች እና ለመምህራን ትምህርት ቤት የለም (ኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤቶች)

ሐሙስ፣ ኦገስት 24 – የትምህርት ቦርድ ስብሰባ

ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 – MCPS ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርእይ  ዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል (ሞል)

ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 - SAT ፈተና የሚወሰድበት ቀን

ሰኞ፣ ኦገስት 28 - ለተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን (መደበኛ የትምህርት ቤት ካለንደር የሚከተሉ ት/ቤቶች)

አርብ፣ ሴፕቴምበር 1 – ከት/ቤት በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን (ኢኖቬቲቭ ት/ቤቶች)

ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 4 - የሰራተኞች ቀን (ሌበር ዴይ) በዓል፣ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 7 – የትምህርት ቦርድ ስብሰባ