አማርኛ መረጃ

ወደ ሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) እንኳን ደህና መጡ

 

ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ እንኳን ደህና መጡ!
እርስዎና ቤተሰብዎ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አካል በመሆናችሁ ደስታ ይሰማናል።
ምናልባት እርስዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አዲስ ሊሆኑ ይችላሉ፣ አለያም ለማህበረሰቡ አዲስ ይሆናሉ፣ ወይም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አባል ቤተሰብ በመሆን ብዙ ዓመት ቆይተው ሊሆን ይችላል። ይህ የመገናኛ ድረ-ገጽ/አውታረ መረብ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደሆነ እንደሚያውቁት ተስፋ እናደርጋለን። ይህንን አውታረ መረብ ያዘጋጀነው ለእርስዎ ነው።
በት/ቤቶች ሥራ እንዴት እንደሚካሄድ በቪድዮ ሊመለከቱ ይችላሉ፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የዜና ትሮች ጋር በሚያገናኙ ገጾች ላይ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ተፈላጊ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይችላሉ።
በዚህ ክፍል የሚገኙት መረጃዎችና ሠነዶች በሙሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ/የተተረጎሙ ናቸው። 
በት/ቤቶቻችን የሚማሩ የእርስዎ ልጆች ምርጥ የሆነ ትምህርት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የትምህርት ሥራ ባልደረቦች በሙሉ ተግተው ይሠራሉ። 
በድጋሚ ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እንኳን ደህና መጡ!

 

የQuickNotes የኢሜይል ዜና አገልግሎት

 

QuickNotes button

አማርኛ መረጃ