Skip to main content

Career Readiness for Students

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ  

Preparación Profesional para estudiantes

Career Readiness ለተማሪዎች

  • students
  • students
  • students
  • students
  • students
  • students

አማራጮችን መርምሩ

በMCPS ስለሚቀርቡ ልዩ ፕሮግራሞች ተማሩ። በእርስዎ መኖሪያ አካባቢ በተመደበ የአካባቢ ት/ቤት በርካታ ፕሮግራሞች ባብዛኛው ጊዜ ይገኛሉ። ወይም በአካባቢ ወይም በካውንቲ-አቀፍ ፕሮግራም ለመሳተፍ ይመርጡ ይሆናል፣ እዚያም የማመልከቻና የአቀባበል ሂደቶች እንደየፕሮግራሙ ሊለያዩ ይችላሉ።

የHS ፕላኖችን ማጤን

MCPS፣ እናንተን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የትኩረት ትምህርት ፕሮግራሞች ለመምራት ስራዎችን ወደ 11 የተለያዩ መስኮች የከፍሏቸዋል። ፕላኖቹ ከወደፊት ግቦቻችሁ ጋር የሚስማሙ ኮርሶች ለመምረጥ ያስችሏችኋል። አብዛኛዎቹ የኮሌጅ ክሬዲት እና የኢንዱስትሪ/የባለሙያ የምስክር ወረቀት/ፈቃድ ማስገኛ እድሎች ያካትታሉ።

[CTE Counselor ToolKit]

ፍላጎቶችን አጢኑ

Naviance Succeed በኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት ለመዳሰስ የሚያስችል የድር ፕሮግራም ነው። እጭር የስራ ታሪክ ለመገንባት፣ ግቦችን ለማጠቃለል፣ እና የኮሌጅና የስኮላርሺፕ ማመልከቻዎቻችሁን ለመከታተልም ልትገለገሉበት ትችላላችሁ። ለምዝገባ ኮድ በአካባቢያችሁ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወደሚገኘው የኮሌጅ/ስራ ማእከል ሂዱ።

ስራዎችን ዳስሱ

በCareer Coach ላይ ከፍላጎታችሁ ጋር የሚስማማ የስራ አይነት ለዩ፣ እናም ለወደፊት ግባችሁ ከአሁኑ መስራት መጀመር ትችላላችሁ። Career Coach በሜሪላንድ እና በዋሺንግቶን ሜትሮፖሊታን አካባቢ የወደፊት የስራ እድል ወይም የስራ ሁኔታዎችን ለመዳሰስ እድል የሚሰጣችሁ የመስመር ላይ የፍለጋ መሳርያ ነው።


¿

የህንፃ ተማሪዎች መኖርያ ቤት ሰሩ

በሲልቨር ስፕሪንግ 3718 Munsey St. የሚገኘው ባለ 2,500 ጫማ ካሬ ቤት፣ ሙሉ በሙሉ ተነድፎ የተገነባው የConstruction Trades Foundation/የህንፃ ስራዎች በጎ-አድራጎት ፕሮግራም አካል በሆኑ በMCPS ተማሪዎች ነው። ይህ በተማሪዎች ተነድፎ የተሰራ 39ኛው መኖርያ ቤት ነው።

 

የBlair STEM ተማሪዎች ሰብማሪን ገነቡ

የMontgomery Blair High School የኢንጂኔሪንግ ተማሪዎች ከዩንይትድ ስቴትስ የባህር ሀይል ጋር በመተባበር፣ በባህር ውስጥ ለውስጥ የሚሄዱ Sea Gliders የሚባሉ ድሮኖች/drones በመገንባት ተጨባጭ ተሞክሮ እያገኙ ነው። በባህር ሀይል ፕላኖችና በባህር ሀይል መለዋወጫዎች በመጠቀም በባህር ሀይል በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ በመዋል ላይ የሚገኙ የባህር ውስጥ ሮቦቶች 24 ሞዴሎች ይገነባሉ።

 

ለከፍተኛ ትምህርት መንገዶች

MCPS ተማሪዎችን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያሉ የኮሌጅ ክሬዲት ለማግኘት የሚችሉበት እድል ለመስጠት ከሞንጎመሪ ኮሌጅና ሼዲግሩቭ ከሚገኘው የሜሪላንድ የዩኒቨርሲቲዎች ስርአት ጋር ተሻርኳል።