በአማርኛ የተዘጋጀ መረጃ
(Information in Amharic)

News

 • የፋይናንሳዊ እርዳታ አውደጥናቶች ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተዘጋጅቷል
 •  

  ስለ ኮሌጅ እና እንዴት እንደሚከፈልበት ማገናዘብ ጀምራችሁ ከሆነ፣ በፎል ወራት በሙሉ በMCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሚካሄደው በነፃ የፋይናንስ እርዳታ ዎርክሾፖች ተገኝታችሁ ተማሩ። ፋይናንሳዊ እርዳታ ምን እንደሆነ፣ ምን አይነት የፋይናንሳዊ እርዳታዎች እንዳሉ እና ተማሪዎች need-based financial aid (በዕርዳታ ፈላጊነት ላይ የተመሠረተ ፋይናንሳዊ እርዳታ) ማመልከት እንዴት እንደሚችሉ ወላጆችና ተማሪዎች በነዚህ አውደ ጥናቶች ይማራሉ። የመጀመርያው አውደ ጥናት ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 6 በSpringbrook High School እንዲከናወን በፕሮግራም ተይዟል። ለተጨማሪ መረጃ ከልጅዎ ት/ቤት ጋር ይገናኙ።

   

 • የቅዳሜ ት/ቤት ተማሪዎችን ስኬታማ እንዲሆኑ ያግዛል።
 •  

  George B. Thomas, Sr. Learning Academy የ2015-2016 ወራት የቅዳሜ ትምህርት ቅዳሜ፣ ኦክተ. 3 ይጀምራል። የቅዳሜ ትምህርት/Saturday School ባለ ዝቅተኛ ዋጋ በግል የማስተማርያና የመቆጣጠርያ ፕሮግራም ተጨማሪ የመማርያ ቀን የሚያቀርብ እና የMCPS ተማሪዎች ዋነኛ የአካዴሚ ርእ ሶችን የመቆጣጣር አቅማቸውን ያሚያዳብር ነው። ተጨማሪ አካዴሚያዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች በMontgomery County ዙሪያ ከሚገኙት 12 ቦታዎች አንዱ ላይ ፕሮግራሞችን መከታተል ይችላሉ። ትምህርቶች ቅዳሜ፣ ኦክቶ. 23 ተጀምረው ሜይ ውስጥ ያልቃሉ። የምዝገባ ዋጋ Free and Reduced-price Meals (ነፃና የቅናሽ ዋጋ ምግብ) (FARMS) ለሚቀበሉ $40 ነው FARMS ለማይቀበሉ ደግሞ $70 ነው።

  George B. Thomas, Sr. Learning Academy

ለወላጆች እና ለተማሪዎች
(For Parents & Students)

ከእኛ ጋር ይገናኙ
(Contact Us)

MCPSን ይጠይቁ (እንግሊዝኛና ስፓኒሽኛ)
301-309-MCPS(6277)
ሰኞ-አርብ
7:30 -5:30

Click here to log in