Skip to main content

የግማሽ አመት ማጠቃለያ

ከበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር ሞኒፋ ማክናይት (Dr. Monifa B. McKnight) ቢሮ

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች

በእኛ የ 2022-2023 የትምህርት አመት ትልቅ ምዕራፍ ተሻግረናል—የአጋማሽ ነጥብ። የተማሪ ሪፖርት ካርዶች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ ቤት ተልከው ነበር፣ እናም የሪፖርት ካርዶች ተማሪዎቻችን እንዴት እየሰሩ መሆናቸውን ለመለካት አስፈላጊ ቢሆንም፣ የMCPS ስራ ከውጤቶች በጣም የበለጠ ነው። ይሄ የግማሽ አመት ማጠቃለያ አንዳንድ ስራዎቻችንን አጉልቶ ያሳያል፣ ይሄም የሚያንፀባርቀው ለትምህርት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ነው።

በጣም አስደሳች ጊዜ ነው። የተማሪዎች እና የሰራተኞች ከፍተኛ መንፈስ/ሀይል የሚታይባቸው ቦታዎች የሆኑትን ትምህርት ቤቶችን እና ቢሮዎችን ደጋግሜ እጎበኛለሁ፣ እና በትምህርቶች፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች፣ የመስክ ጉዞዎች እና በፕሮጀክት ላይ የተመሰረተ ትምህርት ላይ ጥልቅ ተሳትፎን አያለሁ። ከወረርሽኙ በኋላ መደበኛ ብለን ልንጠራው የምንችለውን የመጀመሪያው እውነተኛ ዓመት ሁሉም ሰው እየተደሰተበት ነው! ስለዚህ እባኮትን በአንደኛው ሴሚስተር አጓጊ ስራ እና ተግዳሮቶች ላይ መለስ ብሎ በማሰላሰል ላይ ይቀላቀሉኝ።

 

አዲስ የትምህርት ዓመት

የ2022-2023 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሳምንት ግሩም ነበር!

ወደ 10,000 የሚጠጉ ሰዎችን በአመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ ላይ በማስተናገድ ነው የትምህርት አመቱን የጀመርነው። የመጀመሪያው ቀን ሁሌም እንደ ክብረ በዓል/መደሰቻ ነው፣ እናም በዚህ አመት ወደ 160,000 ከሚጠጉ ተማሪዎች ጋር የከፈትን ሲሆን፣ “ሁሉም በአንድነት፣ ሁሉም ለተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞቻችን እና ማህበረሰባችን” በሚል መሪ ቃል ነው።

የዚህ አመት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችም፡-

ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰብ ጋር መተማመንን መገንባት እና ማደስ።
 
የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን የአእምሮ ጤንነት እና ጤናማነት መደገፍ።
 
የዲስትሪክቱን ትኩረት ወደ ፍትሀዊ ማስተማር እና መማር መመለስ።
 

ታቅዶበት/ታስቦበት የሚሰጠውን ትምህርት፣ በመማሪያ ክፍሎቻችን ውስጥ ጥልቅ ተሳትፎን፣ እና የተነቃቁ ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን አይቻለሁ። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ አዎንታዊ/መልካም ሀይል/መነቃቃት ማየታችን መንፈስን የሚያድስ ነበር። አመታችን በአስደናቂ ሁኔታ እየጀመረ መሆኑን ለማረጋገጥ ማዕከላዊ አመራር በየዲስትሪክቱ ተሰራጭቷል።

MCPS 210ኛ ትምህርት ቤት ከፈተ–ሃሪየት ተብማን (Harriet Tubman) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የጌዘርስበርግ (Gaithersburg) ት/ቤት 99,893 ስኩዌር ጫማ የመማሪያ ቦታ አለው እና ከቅድመ መዋለ ህፃናት–4ተኛ ክፍሎች ድረስ ከፍቷል፣ 5ተኛ ክፍልም በ2023-2024 የትምህርት አመት ይከፈታል። ተቋሙ/የመማሪያ ቦታው ለትምህርት ፕሮግራሞ ግንኙነቶችን ያካትታል፣ በት/ቤት ቦታ ላይ የጤና እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ፣ እና እንደ ሀይል ቆጣቢ LED መብራት እና ከፍተኛ-ሀይል ቆጣቢ HVAC ማሽኖች አይነት በርካታ አካባቢን በዘላቂነት የሚጠብቁ መገለጫዎችን ለማቀናጀትም ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ጤና እና የሰው አገልግሎቶች ክፍል ጋር እና ከሌላ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ጋር በአጋርነት ይሰራል።

MCPS የትምህርት አመቱን የጀመረው 99 ፐርሰንት ሰራተኛ አሟልቶ ነው

ለአስተማሪዎች፣ ለአስተዳደሮች እና የባስ ሹፌሮችን ጨመሮ ለድጋፍ ባለሙያዎች ሰራተኞችን ማሟላት አሁንም ውድድር የተሞላበት ሆኖ ቀጥሏል። የሰው ሀይል ቀጣሪዎች በሀገሪቱ ወደ ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቅጥር አውደ ርዕዮች ተጉዘዋል፤ በአካባቢም፣ ዲስትሪክቱ በበርካታ የስራ መረጃ መርሀ ግብሮች እና አውደ ርዕዮች ላይ ተሳትፏል። የምንፈልጋቸውን ሰራተኞች መፈለግ፣ መቅጠር እና ማሰልጠን በጣም ብዙ/አስለፊ ስራ ነበር።

ደህንነት እና ጥበቃ ላይ ትኩረት

ደህንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አመቱን መጀመር

ደህንነት ለእኛ ተቀዳሚ ትኩረታችን ነው። ይሄን አመት የጀመርነው ስለ ኮቪድ-19 ደህንነት ከት/ቤታችን የህክምና ባለሙያ ከዶክተር ፓትሪሺያ ካፑናን (Dr. Patricia Kapunan) ጋር በመነጋገር ነው። ይሄም ስለግለሰብ ንፅህና ጠቃሚ ማሳሰቢያዎችን እና ኮቪድ-19 ቫይረስ አሁንም ከእኛ ጋር ስላለ ነቅተን እንድንጠብቅ የቀረበ ጥሪን አካቷል።

የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ

ከፍተኛ በሆኑ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ከተከሰቱት ጥቂት አጋጣሚዎች በኋላ፣ መንፈስ የተሞላበት እና ተወዳዳሪ የሆነ ጨዋታን አያስጠበቅን በጨዋታዎች ወቅት ደህንነትን እንዴት ማሳደግ የሚቻልበትን መንገድ መርምረናል። ወላጆችን፣ ሰራተኞችን፣ እና ደህንነትን እና ህግ አስከባሪዎችን የሚያካትት አንድ ቡድን፣ ጨዋታዎች እንዲቀጥሉ እና የደጋፊ ወዳጅነት እንዲቀጥል የሚያስችል የአትሌቲክስ ደህንነት ዕቅድ አዘጋጅቷል።

 

የኦፒዮይድ/ፌንታኒል (Opioid/Fentanyl) መገኘት መቻል በአጠቃላይ በዲስትሪክቱ ያሉ ተማሪዎችን አደጋ ላይ ይጥላል

መረጃ እንደሚያሳየው ከመጠን በላይ ዕፅ መጠቀም ላይ የመጠን መጨመር ብቻ ሳይሆን በህገ-ወጥ መድሃኒቶች ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፣ ብዙውን ጊዜም ከፌንታኒል (fentany) ጋር በተጣመሩ ኦፒዮይድስ (opioids) የተነሳ ነው። ከካውንቲ ህግ አስከባሪዎች፣ ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት፣ ከ Montgomery Goes Purple እና ከተጎዱ ቤተሰቦች ጋር የሚሰሩ ተሟጋቾች ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ MCPS ግንዛቤን ከፍቷል፣ እና መረጃ እና ግብዓቶችን ሰጥቷል። ይሄን አዝማሚያ/አካሄድ መቀልበስ አለብን። 

እየጨመሩ ያሉ የጥላቻ/አድልኦ እና የፀረ-ሴማዊነት ክስተቶች

MCPS ሁሉንም የፀረ-ሴማዊነት ድርጊቶች ያወግዛል። ግድግዳ ላይ የሚፃፉና የሚሳሉ አፅያፊ ነገሮች/ግራፊቲ፣ የቃላት ማስፈራሪያ እና የጥላቻ አስተያየቶች የት/ቤታችን ማህበረሰቦች እንዲረበሽ/እንዲታወክ አድርገዋል። እንደ የአይሁድ ማህበረሰብ ግንኙነት ምክር ቤት ካሉ ተሟጋቾች ጋር በመተባበር ተማሪዎችን ስለ ፀረ-ሴማዊነት ለማስተማር ጥረቶችን እንቀጥላለን፣ ይሄም ከተማሪዎች እና ሰራተኞች ጋር የማገገሚያ/የማስተካከያ ውይይቶችን ማድረግን እና የማህበረሰብ ስብሰባዎችን ይጨምራል። ፀረ-ሴማዊነትን ተቃውመን በአንድነት መናገር እና ሁሉንም የጥላቻ እና ዘረኝነት ድርጊቶች ማውገዝ አለብን።

ፍትሀዊ ማስተማር እና መማር

ሰራተኞች የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ግኝቶችን ነጣጥለው እየተመለከቱ እና እያካተቱ ነው

ኦዲቱ፣ ኦክቶበር ላይ ለትምህርት ቦርድ እና በኖቬምበር ላይ ለህዝብ የቀረበው፣ ዲስትሪክቱ የታሰበበት፣ የተዋሀደ እና የፀረ-ዘረኝነት ዕቅድ ለመፍጠር በሚሰራበት ጊዜ ቁልፍ ግኝቶችን ያቀርባል። የቀድሞ ተሞክሮዎች እንዳስተማሩንም ትኩረት የተደረገበት፣ ታስቦ የሚሰራ ዕቅድ እና ተግባራት ወደ ስኬት ያመራሉ። ሁሉን-አቀፍ የሆነ የትግበራ ዕቅድ በማርች ላይ ይጠበቃል። የሚከተሉትንም ያካትታል፦

  • ለቢሮዎች፣ ት/ቤቶች እና ሰራተኞች ግልፅ የሚጠበቁ ነገሮችን።
  • የሚጠበቁ ነገሮችን ቢሮዎች፣ ት/ቤቶች እና ሰራተኞች እንዲያሳኩ በምን መልኩ እንደሚደገፉ ዝርዝሮችን።
  • ቢሮዎች፣ ት/ቤቶች እና ሰራተኞች በምን መልኩ ተጠያቂ እንደሚሆኑ መመሪያዎችን።

እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፦

በማንበብና መፃፍ እና ሂሳብ ላይ የትምህርት እድገት እና የታሰበበት ትኩረት

የተማሪ የትምህርት እድገት ቁልፍ በሆኑ የምርቃት መስኮች ላይ እየጨመረ ነው፤ በላቀ ምደባ / Advanced Placement (AP) እና በአለም አቀድ ማችሎሬት / International Baccalaureate (IB) ኮርሶች የሚሳተፉ ተማሪዎች እና በ AP/IB ፈተናዎች ላይ ሦስት ወይም ከዛ በላይ ውጤት የሚያገኙ ተማሪዎች ቁጥር፤ እና የስራ ዘርፍ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት። በአንዳንድ ክፍሎች ውስጥ አሁንም ሂሳብ እና ማንበብና መፃፍ አዳጋች ሆነው ቀጥለዋል፣ በተለይም በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት። ለህዝብ የቀረበውን ቪድዮ እዚህ ተመልከቱ

የቀረቡትን ቻርቶች እዚህ ተመልከቱ።

የስራ ማስኬጃ በጀት

ለበጀት አመት 2024 የተመከረው የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ የተለቀቀው በሂሳብ፣ ማንበብና መፃፍ እና ሰራተኞች ላይ ለማተኮር ቁልፍ ኢንቨስትመንቶችን ያካትታል።

የተመከረው $3.15 ቢልዮን የስራ ማስኬጃ በጀት ረቅቂ/ምክረ ሀሳብ ከአለፈው አመት 8% የጨመረ ነው እና የተማሪዎችን ትምህርታዊ አሰራር፣ በተለይም በሂሳብ እና ማንበብና መፃፍ ላይ፣ ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ያስቀጥላል፣ እናም የሰራተኛ ቅጥር እና ማቆያን መደገፊያ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶችን ያደርጋል።

እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ.  

የተማሪ ደህንነትን መደገፍ

የአዕምሮ ጤና እና ደህንነት ሀብቶች/ጤና እና ደህንነት ማዕከላት ተስፋፍተዋል

ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ጤና ዲፓርትመንት/ክፍል እና የሰብአዊ/የሰው አገልግሎቶች ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ 19 ለደህንነት ድልድዮች (Bridge to Wellness) ማዕከላት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ተከፍተዋል። እነዚህ ተቋማት/አቅርቦቶች ለጤና እና ደህንነት አገልግሎቶች ቀላል ተደራሽነትን ይሰጣሉ።

የ MCPS Stronger Student (ጠንካራ ተማሪ) ሞባይል መተግበሪያ

ይሄ አዲስ፣ ነፃ የሞባይል መተግበሪያ ለአዕምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃ እና የአደጋ ጊዘ ግብዓቶች/ሀብቶች ደህንነት ያለው እና ጥበቃ የተደረገበት ማግኛ መንገድን ይሰጣል። ከአፕል (Apple) ወይም ከጎግል ፕሌይ መደብሮች (Google Play store) ማወረድ ይቻላል።

ስራ አፈፃፀሞች እና ቴክኖሎጂ

MCPS በዩ.ኤስ ውስጥ ትልቁን የት/ቤት ባስ ኤሌክትሪክ ማገናኘት ፕሮጀክት አክብሯል

MCPS እና Highland Electric Fleets (ደጋማ ኤሌክትሪክ መጓጓዣዎች)፣ በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ተቀዳሚ የት/ቤት ባስ መጓጓዣ ኤሌክትሪክ ማገናኘት-እንደ-አገልግሎት አቅራቢ የሆነው፣ ኦክቶበር ላይ በሀገር ውስጥ ብቸኛ ትልቅ የሆነ የኤሌክትሪክ የት/ቤት ባሶችን ስራ መመደብ አሳውቋል። በዲዝል የሚሰሩ የባስ መጓጓዣዎችን በኤሌክትሪክ ባሶች መለወጥ MCPS የግሪን ሀውስ ጋዝ መልቀቅን በ 2027 በ80% ለመቀነስ እና በ 2035 በ100% ለመቀነስ የገባውን ቃል ኪዳን ለማክበር አንድ እርምጃ ያስጠጋዋል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

የወደፊት ማስተማሪያ ቴክኖሎጂዎች።

MCPS የአስተማሪ መሳሪያ አውደ ርዕይን አዘጋጅቷል፣ ይሄም የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግ፣ ስነ-ጥበባት እና ሂሳብ (STEAM) ትምህርቶችን ለመደገፍ መምህራን አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተግባር የሚፈትሹበት እድል ነው።  በተጨማሪም መምህራን ከ 50 በላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የወደፊት ቴክኖሎጂ ግኝቶችን እሳቤ ውስጥ በማስገባት ፈትሸዋል፣ በመቀጠልም በመሳሪያዎቹ እና ዋነኛ መገለጫቸው በሆኑት ላይ ግብረ-መልስ ለመስጠት የዳሰሳ ጥናት መጠይቆችን ሞልተዋል።

የወደፊት ጠቃሚ ቴክኖሎጆዎች

በቀጣይ ትምህርት አመት ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን ለማካተት MCPS እየሰራ ነው፣ የሚያካትተውም፦

  • Know Where My Bus Is (የእኔ ባስ የት እንዳለ ማወቅ) / የሞባይል መተግበሪያ
    ይሄ ቴክኖሎጂ የሞባይል መተግበሪያ ሲሆን ወላጆች ጊዜውን የጠበቀ መረጃ የልጃቸው ባስ የሚገኝበትን ቦታ በሚመለከት እንዲደርሳቸው ያስችላል።
  • አዲስ ከት/ቤት-ወደ-ቤት ግንኙነት ስርዓት
    ለቀጣይ ትውልድ/የላቀ ከት/ቤት-ወደ-ቤት ግንኙነት መሳሪያዎች መስፈርቶችን ለመሰብሰብ የ MCPS ሰራተኛ አባላት ከቤተሰቦች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ጋር እየተሰበሰቡ ነው። በርካታ አማራጮች መኖራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት በፅሁፍ መልእክት፣ በኢሜል እና በስልክ እና በሌላ ተጨማሪ መንገዶች ማድረግ ያስችላል። ለቀጣዩ የትምህርት አመት ዝግጁ ለመሆን ይሄ ስራ አሁን ላይ እየተካሄደ ነው።
 

ግንኙነት እና ተሳትፎ

ከቤተሰቦች ጋር ግንኙነት 

  • የኢሜል ደብዳቤዎችን በመጠቀም ተደጋጋሚ የማህበረሰብ መልእክቶች
  • ስለ MCPS መረጃ መጠናቸው የጨመረ የፅሁፍ መልእክት መጠቀም
  • የ QuickNotes (ፈጣን ማስታወሻዎች)፣ የሰራተኛ ማስታወቂያ (Staff Bulletin) እና የ “ማወቅ የሚያስፈልጉ ነገሮች” (“Things to Know”) መልእክትን በመጠቀም ግልፅ ግንኙነቶች
  • ተጨማሪ “መልካም ዜና” ስለ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች በማህበራዊ ቻናሎች
  • በ MCPS ድረ-ገፅ፣ ማህበራዊ ሚድያ እና ቪድዮ በመጠቀም በስፓንሽ መልእክቶች
  • ቁልፍ/ዋነኛ ታሪኮችን በአካባቢ ሚድያ ውስጥ ማስቀመጥን መጨመር
  • ከ MCPS ዋና የህክምና መኮንን የጤና መልእክቶች ለቤተሰቦች
 

የማህበረሰብ ተሳትፎ

  • ከማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት፣ በአካል እና ቨርቹዋል፣ ተደጋጋሚ ስብሰባዎች
  • የስራ ማስኬጃ በጀት ፎረሞች (በአካል፣ ቨርቹዋል እና በስፓኒሽ)
    • ኖቬምበር 12 በማዕከላዊ-ካውኒ ክልላዊ አገልግሎቶች ማዕከል / Mid-County Regional Services Center (በአካል)
    • ኖቬምበር 28 በ ዙም / Zoom (ቨርቹዋል ብቻ)
    • ኖቬምበር 30  በካርቨር (Carver) የትምህርት አገልግሎቶች ማዕከል (CESC) – (በአካል፣ በስፓኒሽ ብቻ)
     
  • የ MCPS መሀል መሀል ላይ የሚኖሩ ዝግጅቶች ከማህበረብ ጋር ለሚደረግ የሰራተኞች ተሳትፎ
  • 48 ጉብኝቶች በሱፐሪንቴንደንት/የበላይ ተቆጣጣሪ ማክናይት (McKnight) (እና ቁጥሩ ይቀጥላል!)  ወደ ት/ቤቶች እና ቢሮዎች አስገራሚውን ስራ ለመመልከት እና ከሰራተኞች እና ተማሪዎች በቀጥታ ለመስማት
  • ሳምንታዊ የዜና እና መረጃ ማሳወቂያ ለትምህርት ቦርድ አባላት
  • ሳምንታዊ “ውድ ባልደረቦች” (“Dear Colleague”) ደብዳቤዎች ከ MCPS ስራተኞች ጋር መረጃን ለመጋራት።

የወላጅ አካዳሚ መርሀ ግብሮች

ቨርቹዋል አውደ ጥናቶች፣ ኦንላይን የፅሁፍ መልእክት መለዋወጦች እና “እንዴት እንደሚደረግ” (“how to”) ቪድዮዎች ለቤተሰቦች በአጠቃላይ ፎል (መኸር) እና ዊንተር (ክረምት) ወቅት ውስጥ ተደራሽ ነበር። እነዚህ ጠቃሚ መርሀ ግብሮች የሚያካትቱትም ወላጆች የልጆቻቸውን ትምህርት ለመደገፍ የሚያስፈልጓቸውን ጥልቅ እውቀት እንዲያጎለብቱ እና ክህሎቶችን እንዲማሩ እና እንዲያጎለብቱ እድሎችን የሚያቀርቡ ጥናት-መሰረት ያደረጉ ስልቶችን እና ክፍሎችን ነው። እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፦

መልካም ዜና

የሩት እና ኖርማን ሬልስ–ፓትሪሻ ቤር ኦ‘ኒል (Ruth and Norman Rales–Patricia Baier O'Neill) ስኮላርሺፕ ይፋ ተደረገ

የ $10 ሚልዮን ስጦታ ከሩት እና ኖርማን ሬልስ (Ruth and Norman Rales) ፋውንዴሽን በየአመቱ 200 ስኮላርሺፖችን ይሸልማል፣ ይሄም እያንዳንዱ $10,000 ዋጋ አለው፣ የሚሰጠውም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ከዝቅተኛ-እስከ-መካከለኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ነው። ይሄ ስኮላርሺፕ የሚሰጠው የረጅም ጊዜ የትምህርት ቦርድ አባል ፓትሪሻ ኦ‘ኒል (Patricia O’Neill)፣ በ 2021 ህይወቷ ያለፈ የተማሪዎች ቆራጥ/ታማኝ ተሟጋችን፣ ለመዘከር/ለማስታወስ ነው።

የ MCPS አስተማሪ የተከበረውን የሚልከን መምህር ሽልማት (Milken Educator Award) አሸነፈ

የ MCPS አስተማሪ ዳየን ጆንስ (Dion Jones)፣ በፌርላንድ (Fairland) የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሦስተኛ-ክፍል መምህር፣ ጃንዋሪ ላይ በሚልከን መምህር ሽልማት (Milken Educator Award) ክብር አግኝቷል። ጆንስ (Jones) በሜሪላንድ ብቸኛው ተሸላሚ ነበር፣  እና ገደብ የሌለበት የ $25,000 የገንዘብ ሽልማት ወስዷል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

የሙዚቃ መምህርት የብሔራዊ ስኬት ሽልማት (National Achievement Award) አሸንፋለች

አማንዳ ሀሮልድ (Amanda Herold)፣ በጆን ኤፍ. ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ የሙዚቃ መሳሪያ ሙዚቃ መምህርት፣ በብሔራዊ የሙዚቃ ትምህርት ማህበር የባለሙያ ስኬት ሽልማት (Professional Achievement Award) ተሰጥቷታል። 

ሰባቱ ከ 10 ምርጥ በሜሪላንድ ውስጥ የሚገኙ ፐብሊክ/የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚገኙት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ነው

ሁሉም የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከውጤት ደረጃ ምርጥ ግማሽ ውስጥ ናቸው፣ በ Niche መሰረት።

የ MCPS ኳስ ጨዋታ (Football) ቡድን የስቴት ሻምፒዮና አሸንፏል

በዲሴምበር፣ የኩዊንስ ኦርቻርድ (Quince Orchard) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኳስ ጨዋታ (Football) ቡድን ለሁለት ተከታታይ አመታት የ MPSSAA 4A ስቴት ኳስ ጨዋታ (Football) ሻምፒዮና አሸንፏል። ቡድኑ የጨዋታ ወቅቱን/ሲዝኑን የጨረሰው 14-0 ነው።

ተጨማሪ የመልካም ዜና ታሪኮችን ተመልከቱ።

በአጠቃላይ ዲስትሪክቱ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ስኮላርሺፖችን አገኙ

አስራ ሦስት ተማሪዎች የሙሉ-ትምህርት ፖዚ (Posse) ስኮላርሺፖች አግኝተዋል
አስራ ሦስት ተማሪዎች በፖዚ (Posse) ፋውንዴሽን የሙሉ-ትምህርት፣ የአራት-አመት የኮሌጅ ስኮላርሺፖችን አሸናፊዎች ተብለው ተመርጠዋል።

ተማሪዎች ለብሔራዊ የምጡቅነት ሽልማት ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል
MCPS ለ 2023 ብሔራዊ የምጡቅነት ችሎታ (Merit ) ስኮላርሺፕ ውድድር 147 የግማሽ ፍጻሜ ተወዳዳሪዎች አሉት። የግማሽ ፍጻሜ ተወዳዳሪዎቹ በስፕሪንግ (ፀደይ) ወቅት ይፋ ለሚደረገው ስኮላርሺፕ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይወዳደራሉ። 

አስራ አራት የሙሉ-ትምህርት ስኮላርሺፖችን ከኩዌስት ብሪጅ (QuestBridge) ተቀብለዋል

አስራ አራት የ MCPS ተመራቂ ተማሪዎች የአራት አመት፣ የሙሉ-ትምህርት ስኮላርሺፖችን ከኩዌስት ብሪጅ (QuestBridge) ተቀብለዋል፣ ይሄም ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዝቅተኛ-ገቢ፣ ከፍተኛ-ስኬት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ከ 45 በላይ የሚሆኑ ምርጥ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚያገናኝ ነው።