Skip to main content

BOE-Banner-homepage-new3.jpg

 

Board of Education

ህዝባዊ ተሳትፎ 

ስብሰባዎችን መመልከት እና መስማት የሚችሉባቸው መንገዶች 

የቀጥታ ስርጭት ስብሰባዎችን ይመልከቱ

የቦርድ ስብሰባ ዘገባዎችና ማስታወቂያዎች

የስብሰባ ካለንደር 

የተሳትፎ መንገዶች 

ህዝባዊ ውይይቶች 

የትምህርት ቦርድ የሕዝብን ትኩረት በሚስቡ በርካታ ጉዳዮች ዙርያ ከህብረተሰብ ሃሳብና አስተያየቶችን ለመቀበል የጊዜ ሠሌዳ አዘጋጅቷል። ከህብረተሰብ ሃሳብና አስተያየቶችን ለመቀበል በሚካሄድ ስብሰባ ወቅት የቦርድ አባላት ተሟልተው መገኘት አይጠበቅባቸውም። ልዩ የህብረተሰብ ሃሳብና አስተያየት ከመቀበል በተጨማሪ፥ ቦርዱ በስትራቴጂያዊ እቅዱ ላይ፥ ዓመታዊ የሥራ ማስኬጃ ባጀት፥ ለካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) የቀረበ ፕሮፖዛል፣ እንዲሁም የትምህርት ቤት ማካለል በመሣሰሉ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ይደረጋሉ። የካፒታል ባጀት (CIP) እና/ወይም የትምህርት ቤት ማካለል ፕሮፖዛልን በሚመለከት የህብረተሰብ ውይይት የሚካሄደው በቦርድ ፖሊሲ "Board Policy FAA" መሠረት ይሆናል። የትምህርት ፋሲሊቲዎች እቅድ/Educational Facilities Planning.

ለሕዝባዊ ውይይት አጠቃላይ መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፦

ጉዳዩ፥ ቀኑ፥ እና የህዝብ አስተያየት ለመስጠት ምዝገባን በሚመለከት በቦርዱ መደበኛ የመገናኛ መረቦች አማካይነት ለሕዝብ የሚገለጽ ሲሆን፣ ይህም በቦርዱ ድረ ገጽ እና በዜና ማሠራጫ አውታሮች ይፋ ይደረጋል።

ለቦርዱ ህዝባዊ አስተያየት ለማቅረብ በማስታወቂያ ካልተገለጸ በስተቀር ከፍተኛው የተናጋሪዎች ቁጥር ምዝገባ ከሞላ ወይም የህዝባዊ አስተያየት ውይይት በሚደረግበት የሥራ ቀን ዋዜማ የሥራ ሠዓት ሲጠናቀቅ የአስተያየት መስሚያ አጀንዳ መቀበል ይዘጋል።

በቦርዱ የህብረተሰብ ውይይት ማስታወቂያ ላይ በተለይ ካልተገለጸ በስተቀር የውይይት-ምሥክርነት ቃል የሚሰማበት የጊዜ ገደብ እንደሚከተለው ይሆናል፦

ድርጅቶች*/የከተማ አስተዳደሮች/ተመራጭ ኃላፊዎች፦ 5 ደቂቃ (*ድርጅቶች የሚያካትቱት፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሪጅናል የተማሪ አመራር አሶስዬሽን/የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጁንየር ካውንስልስ፥ የከለር ማህበረሰብ ወላጆች አድቫንስመንት ናሽናል አሶስዬሽን ካውንስል፥ የማህበረሰብ ድርጅቶች፥ MCCPTA፥ ክለስተሮች፥ እና የሠራተኛ አሶስዬሽኖች፥ እና የማህበረሰብ ድርጅቶች—ስለ አንድ ድርጅት አመለካከት በጋራ ለማቀንቀን የሚሠራ ግለሰብ።)

ግለሰቦች፦ 3 ደቂቃ

 የክለስተር አስተባባሪ ወይም የአካባቢ ምክትል ፕሬዚደንት ካልሆነ(ች) በስተቀር ለመናገር የሚደውል ግለሰብ አንድ ጊዜ ብቻ ይመደብለ(ላ)ታል። ቦርዱ የተለየ ፈቃድ ካልሰጠ በስተቀር ከአንድ ድርጅት አንድ ተናጋሪ ብቻ ይመዘገባል። ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለሌሎች የተመዘገቡ ሰዎች ጊዜያቸውን አሳልፈው መስጠት አይችሉም። በህዝብ የተመረጡ ኃላፊዎች በአጀንዳዉ ላይ ለመናገር ራሳቸው የሚመርጡት ሠዓት ይመደብላቸዋል። ተናጋሪዎች ሃሳባቸውን ቢያንስ ከ 24 ሰዓት አስቀድመው ለትምህርት ቦርድ ጽ/ቤት በኤሌክትሮኒክስ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። የሚናገሩት አስተያየት ቀደም ብሎ ካልቀረበ፥ ተናጋሪዎች የሚያቀርቡትን ሃሳብ በሸንጎው ላይ ለቦርድ አባላት፥ ለሠራተኞች፥ እና ለመገናኛ ብዙሃን የሚሰጥ 20 ቅጅዎችን እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። የህዝባዊ ውይይት አስተያየቶች ሪኮርድ ይደረጋሉ፥ በቴሌቪዥን ይሠራጫሉ፥ እና በበይነመረብ ለሕዝብ ይተላለፋሉ።

በሾንጎ ስለሚሰጥ ህዝባዊ አስተያየት ተጨማሪ መረጃ በትምህርት ቦርድ መመሪያ መጽሃፍ (Board of Education Handbook) ላይ ይገኛል።


 

A. የመመዝገቢያ መመሪያዎች-መደበኛ የቦርድ ስብሰባ የሕዝብ አስተያየት

ግለሰቦች በቀጣዩ የቦርድ መደበኛ የሥራ ስብሰባ ላይ ህዝባዊ አስተያየት ለመስጠት እዚህ መመዝገብ ይችላሉ። በሌላ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር የምዝገባ ወቅት ለህዝብ ክፍት የሚሆነው ከመደበኛ ስብሰባ ቀን አንድ ሣምንት ቀደም ብሎ በ 6:00 p.m. ይሆናል።

ከኦገስት 24 ቀን 2021 ጀምሮ የትምህርት ቦርድ በአካል የሕዝብ አስተያየቶችን እንደገና መቀበል ይጀምራል፥ ይኼውም በውስን ደረጃ ለሕዝብ ክፍት ይሆናል። አስተያየቶችን ቨርቹወል ማቅረብ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ቦርዱ አስቀድሞ የተቀረፀ የኦዲዮ እና የቪዲዮ አስተያየቶችን መቀበል ይቀጥላል። አስተያየቶቹ-ምስክርነቶቹ በሙሉ "BoardDocs" ላይ ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ። የህዝብ አስተያየቶችን ለመስጠት የሚፈልጉ ግለሰቦች በኦንላይን የምዝገባ ቅጽ በመጠቀም ይመዘገባሉ እና በአመዘጋገባቸው ቅደምተከተል መሠረት ይመረጣሉ።

የቦርድ ስብሰባ በአካል መከታተል

የቦርድ ስብሰባዎች ለሕዝብ ምልከታ በቀጥታ ስርጭት መተላለፋቸው ይቀጥላል። ስብሰባዎች በውስን መቀመጫዎች ለሕዝብ ክፍት ናቸው። በስብሰባው ላይ በአካል ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች ከዚህ በታች ያለውን ኦንላይን የምዝገባ ቅጽ በመጠቀም ቢበዛ ሁለት (2) መቀመጫዎችን በቅድሚያ መያዝ ይችላሉ። የቦርድ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት አስቀድሞ ቦታ እንዲያዝ ባይጠየቅም፣ መቀመጫ ቦታ ለማግኘት አስተማማኝ እንዲሆን አስቀድሞ ቦታ ማስያዝ በጣም ይበረታታል። ወንበሮቹ ከሞሉ በኋላ፣ ተጨማሪ የሕዝብ ተመልካቾችን-ታዛቢዎችን ማስተናገድ አንችልም እና መጠባበቂያ ክፍል አይገኝም።

ቦታ ለማስያዝ እንደየአመጣጣቸው ቅደምተከተል መሠረት ስለሚሆን ከቦርዱ የስብሰባ ቀን አንድ ሳምንት በፊት 4፡00 p.m. ይከፈታል። መቀመጫዎቹ እስኪሞሉ ክፍት ይሆናል፥ ወይም መቀመጫዎቹ ካልሞሉ ከስብሰባው አንድ ቀን በፊት እስከ 12፡00 p.m. ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

በቦርድ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ለመመዝገብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

 

በአካል በታዛቢነት ለመከታተል እና ህዝባዊ አስተያየቶችን ለመስጠት የደህንነት አጠባበቅ ቅደምተከተሎች

በህንፃው አካባቢዎች በሙሉ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን መጠቀም ያስፈልጋል፥ እና ቀጥታ የህዝብ አስተያየቶችን በሚሰጡበት ጊዜ ጭምብል መልበስ አስፈላጊ ነው።

የሕመም ምልክቶች ካለብዎት እባክዎን በአካል ከመገኘት ይቆጠቡ።

በኮሪደሮች እና በሮች አካባቢ መሰብሰብ የተከለከለ ነው።

ለሕዝብ አስተያየት ተናጋሪዎች በስብሰባው ክፍል ውስጥ ለአንድ ሰው አንድ መቀመጫ ይመደባል።

ከ 8.5 ”x 11” በላይ ትልቅ የሆኑ ምልክቶች የተከለከሉ ናቸው።