News

ስለ "Homecoming" ክብረ በዓላት የሚደረጉ ለውጦች ይኖራሉ

 

በሁሉም የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች "Homecoming " በዓላት የሚጀምሩት በሴፕቴምበር ወር መጨረሻ ሲሆን እስከ ኦክቶበር መጨረሻ ድረስ ይቀጥላል። የትምህርት ቤት ማህበረሰቦቻችን የተማሪዎችን የትምህርት እንቅስቃሴ መንፈስ ለማዳበር እና ቡድኖቻቸውን እና ክለቦቻቸውን ለማሞገስ አስደሳች እንቅስቃሴዎችን በሚያሳዩ የበለፀጉ ወጎች ውስጥ ይሳተፋሉ። በዚህ ዓመትም እነዚህ homecoming ወጎች እና ክብረ በዓላት ይቀጥላሉ፣ ነገር ግን በጊዜው ባለው የ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሰበብ የተማሪዎቻችንን፣ የሠራተኞቻችንን እና የቤተሰባችንን ጤና እና ደህንነት ለማረጋገጥ ለውጦች ይደረጋሉ።

በኦገስት ወር፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን፣ ሠራተኞችን እና መሪዎችን ያቀፈ "Homecoming Innovation Committee" ኮሚቴ ሀሳቦችን ለማመንጨት እና ለማዳበር ስብሰባ አድርጓል። በተጨማሪም ኮሚቴው መመሪያና ድጋፍ ለማግኘት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ ተወካይ አሳትፏል። በዚህ የትብብር ሥራ ምክንያት፣ MCPS በሁሉም የ "homecoming" በዓላት አከባበር ላይ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ታሳቢ በማድረግ ይቀጥላል። 

 

 

 • ተማሪዎች እና ሠራተኞች በቤት ውስጥ በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች፣ በየእለቱ በሚካሄዱ የመማሪያ ክፍል ትምህርቶች፣ እና (ለምሳሌየኮሪደር ማስጌጫዎችን ለማዘጋጀት) በሚሳተፉበት ጊዜ ጭምብል እንዲለብሱ ይጠበቅባቸዋል።
 • የመተላለፊያ መንገድ/ተንሳፋፊ ማስጌጫዎች፣ የፔፕ (pep) ረድፎች እና ሌሎች "homecoming" ሥራዎች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሠረት ይካሄዳሉ። በተቻለ መጠን እንቅስቃሴዎች ከቤት ውጭ ይከናወናሉ።
 •  "Homecoming" ጭፈራዎች በሚከተሉት ማሻሻያዎች ይካሄዳሉ 
  • ምንም ሙዚቃ ወይም ጭፈራ በቤት ውስጥ አይደረግም። ትምህርት ቤቶች ለሙዚቃ እና ለዳንስ ከቤት ውጭ ያለውን ቦታ ያዘጋጃሉ። ስታዲየሞች ወይም አደባባዮች ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮች ናቸው።
  • የ "Homecoming Innovation Committee" ለአማራጭ እንቅስቃሴዎች ሀሳቦችን ፈጥሮ ለት/ቤቶች አጋርቷል። ት/ቤቶች በአማራጭ እንቅስቃሴዎች ላይ ከተማሪ እና ከወላጅ ድርጅቶች ጋር እንዲተባበሩ እናበረታታለን።
  • ትምህርት ቤቶች "homecoming" ጭፈራዎችን የቀን ብርሃን ለመጠቀም ቀደም ብሎ መጀመር እና በጊዜ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ትምህርት ቤቶች ለ " homecoming" ዳንስ “የዝናብ ቀን” አለመሆኑን እንዲለዩ ይበረታታሉ።
  • ትምህርት ቤቶች ድንኳኖችን ከመግዛት ወይም እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ከኩባንያዎች ጋር ከመዋዋል መቆጠብ አለባቸው።
  • ትምህርት ቤቶች እንግዶች ወደ "homecoming" እንዲመጡ ለመፍቀድ ነባር ልምዶችን መከተል አለባቸው። እንግዶች በአሁኑ ጊዜ ለተመዘገቡ የ MCPS ተማሪዎች ብቻ መገደብ አለባቸው።