Grading & Reporting → Report Cards አማርኛ -- የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሪፖርት ካርዶችAMHARIC -- Report Cards for Elementary Schools MCPS ለመጪው 2018-2019 የትምህርት ዓመት ስለ ሪፖርት ካርድ እና የውጤት-ማርክ ስኬል(ሚዛን) ክለሳ ያደርጋል። ክለሳ የተደረገበት ምክንያት ትምህርትን ለተማሪዎች ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስተላለፍ እና ስለ ትምህርት ክህሎትና ስለ ሥራ እውቀት ልምድ ተጨማሪ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ለመስጠት የተነደፈ ነው። ለውጡ ወላጆች፣ የት/ቤት ሠራተኞች፣እና ማህበረሰቡ ያደረጓቸውን አስተዋፅዎች ያንፀባርቃል። ምን አዲስ ነገር አለ? ከ2ኛ–5ኛ ክፍሎች A, B, C, D ቁልፍ የመማር ክህሎቶችን ሪፖርትም ያካትታል። (ከእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት መመዘኛ/መለኪያ ርእሶች ላይ በተጨማሪ የዓመት-መጨረሻ አማካይ ውጤት) የአጠቃላይ ትምህርት ውጤትን ያካትታል። የመዋእለ ህፃናት ተማሪዎች በዓመት (ከሁለት ጊዜ ይልቅ) አራት ጊዜ የሪፖርት ካርድ ያገኛሉ።