አማርኛ መረጃ

የኮቪድ ወረርሽኝን ይበልጥ ለመቀነስ ጊዜያዊ ሱፐር ኢንተንደንት ባለ አምስት ነጥብ ዕቅድ ይፋ አድርገዋል

ለ MCPS ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት በማረጋገጥ ትምህርት ቤቶችን ክፍት ማድረግ ነው። MCPS የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመገደብ በትምህርት ቤት ሕንፃዎች ውስጥ በርካታ ማሻሻያዎችን ከማከናወኑም በላይ የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ መመሪያዎችን አስቀምጧል። ሴፕቴምበር 9፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ሁሉም ሠራተኞች እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2021 ሙሉ በሙሉ ክትባት መውሰድ እንዳለባቸው ወስኗል። ይህ አስፈላጊ እርምጃ በት/ቤቶች እና በማህበረሰቡ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል። 

 

 

QuickNotes button