Skip to main content

Amharic 11-15-2023


ኖቬምበር 15, 2023

ስለ 2024–2025 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ ግብረ መልስ ስለመፈለግ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2024–2025 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ በማዘጋጀት ላይ ስለሆነ፣ ድስትሪክቱ በሁለት ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች ላይ ከቤተሰብ፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰቡ ተጨማሪ ግብረመልስ ይፈልጋል። ዳሰሳው በማዘጋጀት ሂደት ላይ ያለውን ሁለተኛውን ምዕራፍ ይወክላል

 

ሁለቱም ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

 

  • በ 2024 የምስጋና በአል በሚከበርበት ሣምንት በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀናት (ሰኞ እና ማክሰኞ)።
  • ሰኞ፣ ዲሴምበር 23, 2024 ትምህርት የለም።
  • የስፕሪንግ መግቢያ ወቅት ዕረፍት (ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 12 እስከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 21፣ 2025)።


ተጨማሪ ዝርዝሮችን ይመልከቱ እና የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ

በትምህርት ላይ መገኘትና መከታተል ፋይዳ አለው፡ ሰኞ፣ ኖቬምበር 20 እና ማክሰኞ ኖቬምበር 21 የትምህርት ቀናት ናቸው።

ሰኞ፣ ንቬምበር 20 እና ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 21 ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀናት ናቸው። በሁለቱም ቀናት ውስጥ ጠቃሚ የማስተማር እና የመማር ሥራ ይከናወናል፤ ተማሪዎች ከአምስቱ የምስጋና ቀናት እረፍት በፊት ከመምህራኖቻቸው እና ከእኩዮቻቸው ጋር መገናኘት የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ ነው።

በእያንዳንዱ ቀን ትምህርት ቤት መገኘት አስፈላጊ እና ፋይዳ ያለው ነው።

እባክዎን ተማሪዎች በቅድሚያ በሚለቀቁባቸው በእነዚህ ሁለት ቀናት በሰዓቱ ተገኝተው ልጅ(ጆች)ዎን ለመቀበል የተቻለ ጥረት ያድርጉ።

ኖቬምበር 18 ለሚደረገው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምስጋና ሰልፍ ትርኢት አሁኑኑ በበጎ ፈቃደኝነት ይሳተፉ ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 18 ለሚካሄደው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምስጋና ሰልፍ ትርኢት ዕድሜያቸው 13 አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ በጎ ፈቃደኞችን ይፈልጋል። የሰልፉ ትርኢት የሚጀምረው Ellsworth Drive እና Fenton Street መሃል ሲልቨር ስፕሪንግ ላይ ሲሆን ወደ ደቡብ አቅጣጫ በጆርጂያ መንገድ እየተጓዘ Silver Spring Avenue ላይ ያበቃል። ዝናብ ቢኖርም ባይኖርም የሰልፍ ትርኢቱ ይካሄዳል።


በጎ ፈቃደኞች በተለየ አለባበስ ያጌጣሉ፣ በዩኒት መሪነት ያገለግላሉ፣ እና የሚነፉ ባሉኖችን እና ፊኛዎችን ያዥዎች ይሆናሉ። የበጎ ፈቃደኞች የአገልግሎት ሰአት ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 1:30 p.m. ነው። (በጎ ፈቃደኞች ሙሉውን ስድስት ሰዓት መገኘት አለባቸው)። ከ13 ዓመት በላይ የሆናቸው ተማሪዎች ለተሳትፏቸው የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ለሰልፍ ትርኢት በጎ ፈቃደኛነት እዚህ ይመዝገቡ።


2024 የኤድዋርድ ሸርሊ ሽልማት "Edward Shirley Award" እጩዎችን ጥቆማ ለማቅረብ ክፍት ሆኗል።

ለ2024 የዶክተር ኤድዋርድ ሸርሊ ሽልማት "Dr. Edward Shirley Award" በትምህርት አስተዳደር እና ቁጥጥር ልህቀት ብቃት ያላቸውን እጩዎች ጥቆማ ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የላቀ ብቃት ላለው/ላላት የ (MCPS) አስተዳዳሪ ወይም ሱፐርቫይዘር በየዓመቱ እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ፣ በእጩነት የሚቀርቡት ጥቆማዎች ብቁ ርእሰ መምህራን፣ ረዳት ርእሰ መምህራን፣ የትምህርት ቤት ቢዝነስ አስተዳዳሪዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ሌሎች የአስተዳዳር እና የቁጥጥር ሃላፊነት ያላቸውን ያካትታሉ።

እጩዎችን በ MCPS ሰራተኞች፣ ባልደረቦች፣ ጓደኞች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ሊቀርቡ ይችላሉ። እራስን መጠቆምም ተቀባይነት ይኖረዋል። የእጩዎችን ጥቆማ ማቅረቢያ ቀነ-ገደብ አርብ፣ ጃኑዋሪ 12, 2024 ከቀኑ 4 p.m. ነው። ሽልማቱ የሚሰጠው በሞንትጎመሪ ካውንቲ የአስተዳዳሪዎች እና ርእሰ መምህራን ማህበር/  Montgomery County Association of Administrators and Principals (MCAAP) አማካይነት ነው።


2024 ለኤድዋርድ ሸርሊ ሽልማት እጩ ማቅረቢያ ፓኬጅ

 

የዊንተር (የክረምት) ጃኬት እርዳታ በመሰብሰብ ላይ ነው

የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ቢሮዎች ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የአዳዲስ ጃኬት ልገሳዎችን እየተቀበሉ ናቸው። ኮፍያዎችን፣ የእጅ ጓንቶችን፣ የአንገት ልብሶችን/ስካርቮችን እና ቦት ጫማዎችንም በደስታ ይቀበላሉ። ለወንድ ልጆች እና ለሴት ልጆች የሳይዝ ቁጥራቸው 5, 6, 7, እና 8 የሆኑ ልገሳዎች ያስፈልጋሉ የልገሳ ዕቃዎች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8:30 a.m.–5 p.m., በዚህ አድራሻ "Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 141, Rockville, MD 20852"፣ በአካል አምጥቶ ማስረከብ ወይም በኦንላይን ታዘው በቀጥታ ወደ Rocking Horse Road Center ለሊዛ ኮሎን/Lisa Conlon እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ።


ለበለጠ መረጃ ሊዛ ኮንሎን/Lisa Conlon በስልክ ቁጥር 240-550-2615 ወይም 240-740-4530 ያነጋግሩ።

ቀኑን ያስታውሱ፦ አመታዊ ያገለገሉ መኪናዎችና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ዲሴምበር 9 ይካሄዳል

ለመጪው የመኪናዎች እና የኮምፒውተሮች ሽያጭ ቀን ለማስታወስ ካለንደርዎን ምልክት ያድርጉበት!

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች አውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን (ATF) እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) ያሉ ተማሪዎች እድሳት ያደረጉላቸውን ያገለገለ መኪናዎችን እና ኮምፒውተሮችን ቅዳሜ፣ ዲሴምበር 9 ከ9-11 a.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይሸጣሉ። የጌትስበርግ ትምህርት ቤት የሚገኝበት አድራሻ የሚከተለው ነው፦ 101 Education Blvd in Gaithersburg ሽያጩ የሚካሄደው auto bays (Summit Avenue አቅራቢያ የሚገኝ የትምህርት ቤት መግቢያ) ላይ ነው።

 

መኪናዎቹ እና ኮምፒዩተሮቹ የክፍል ውስጥ እና የላቦራቶሪ ጥናታቸዉ አካል በመሆን በተማሪዎች የታደሱ እና የተስተካከሉ ናቸው። ሽያጩ ተማሪዎች የሽያጭ ክህሎቶቻቸውን እንዲለማመዱ፣ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአታትን እንዲያገኙ እና ለማህበረሰብ ተሳትፎ ጥልቅ አድናቆት እንዲያዳብሩ እድል ይሰጣቸዋል።

 

ATF በተጨማሪም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እንዴት ያገለገሉ መኪናዎችን ብልሽት መፈተሽ፣ መጠገን እና ማደስ እንደሚችሉ የሚማሩበት የመኪናዎች ልገሳ ይፈልጋል። ATF በደማስከስ፣ በጌትስበርግ እና በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና በቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት በአጠቃላይ ከሰኞ እስከ አርብ  ከቀኑ 8 a.m.–3 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ አመቱን በሙሉ ልገሳዎችን ይቀበላል። ልገሳዎቹ ታክስ ያስቀንሳሉ።

 

ስለ አውቶሞቲቭ ፕሮግራም ጥያቄዎች፣ 240-740-2051 ለ Kelly Johnson ይደውሉ። የመኪና ልገሳ ቀጠሮ ለማስያዝ፣ ለሚካኤል ስናይደር (Michael Snyder) 240-740-2050 ይደውሉ።

 

የኣውቶሞቢሎች ንግድ ስራ ፋውንዴሽን (Automotive Trades Foundation)

 

የመረጃ ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (Information Technology Foundation)

 

ኖቬምበር 16 የሚካሄድ ነጻ የልጆች ደህንነት መጠበቂያ መቀመጫ

Fitzgerald Auto Malls ሐሙስ፣ ኖቬምበር 16 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 12:30 p.m. በ GMC/Buick Rockville የልጆች ደህንነት መጠበቂያ መቀመጫ ዝግጅት ያካሄዳል። ሁሉም የመቀመጫ ቴክኒሻኖቻቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የተመሰከረላቸው እና ነፃ ናቸው።


Fitzgerald Auto Malls GMC/Buick Rockville የሚገኝበት አድራሻ፦ 5501 Nicholson Lane፣ Rockville፣ MD 20852 ነው።

 

ተማሪዎች፡ በ "MoComCon 2023" የስነጥበብ እና ድርሰት ውድድር ላይ ተሳተፉ

MoComCon፣ አስቂኝ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ፣ ስዕላዊ ልቦለዶችን፣ እና አድናቂዎችን የሚያከብር ቀኑን ሙሉ የሚካሄድ፣ለሁሉም እድሜ ክልል የሚሆን ዝግጅት ሲሆን፣ ቅዳሜ፣ ጃኑዋሪ 20 በጀርመንታውም ቤተ መጻህፍት ይመለሳል


እንደ ክብረ በዓሉ አንድ አካል MoComCon የስነጥበብ እና የፅሁፍ ውድድሮችን ያካትታል። የስነጥበብ ውድድሩ በሦስት የዕድሜ ቡድኖች የተከፈለ ነው፡ ልጅ(5-12)፣ታዳጊ ወጣት(13–17) ወይም አዋቂ (18+) ተሳታፊዎች የሚወዱትን ገጸ ባህሪ ከማንኛውም ፋንዶም/fandom፣ መጽሐፍ፣ የቴሌቭዥን ትርኢት፣ ከፊልም፣ ከጨዋታ ላይ እንዲፈጥሩ ወይም የራሳቸውን ኦሪጅናል ገጸ ባህሪ እንዲፈጥሩ ይጠየቃሉ።


የድርሰት ውድድሩ ከ 8 እስከ 14 አመት እድሜ መካከል ለሚገኝ ለማንኛውም ሰው ነው። ተመዝጋቢዎች ከሚከተለው የጥያቄ ፍንጭ 300 እስከ 500 ቃላት የሚሆን ድርሰት እንዲጽፉ ይጠየቃሉ፡ ስለ አድናቂነት አጀማመርዎ ይንገሩን። መጀመሪያ የገቡበት የአድናቂዎች ቡድን የትኛው ነው እና ለምን? በእርስዎ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አሳድሯል፣ እና ለእርስዎ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድነው?

የሁለቱም ውድድሮች የመጨረሻው ቀን አርብ፣ዲሴምበር 1 ከቀኑ 5 p.m. ነው።


ለሥነ ጥበብ እና ለድርሰት ውድድሮች የመመዝገቢያ ቅጾች ከሚያስፈልጉ ሰነዶች ሁሉ ጋር መካተት አለባቸው እና የሚቀርቡት ሰነዶች ሁሉም በኤሌክትሮኒክስ መቅረብ አለባቸው። የውድድሩ የመጨረሻ እጩዎች እና አሸናፊዎች ከ MoComCon በፊት በኢሜል ወይም በስልክ ይነገራቸዋል።


የአርት ውድድር መመዝገቢያ ቅጽ

የድርሰት ውድድር መመዝገቢያ ቅጽ

ተጨማሪ መረጃ

መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

ሐሙስ፣ ኖቬምበር 16—የትምህርት ቦርድ የፋሲሊቲዎች እና ወሰኖች ውሳኔ

አርብ፣ ኖቬምበር 17—ልዩ የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ ስብሰባ (ቨርቹዋል)

ሰኞ፣ ኖቬምበር 20—ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 21—ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀናት (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)

እሮብ፣ ኖቬምበር 22—ስርዓት አቀፍ መዘጋት፦ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)

ሐሙስ፣ ኖቬምበር 23—አርብ፣ ኖቬምበር 24—የምስጋና በዓላት "Thanksgiving holidays" ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)