News

የዊንተር እረፍት ተማሪዎች በአገልግሎት እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉና የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአቶችን ለማጠራቀም በጣም ጥሩ ጊዜ ነው። ተማሪዎች በተለያዩ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ ይችላሉ፡— ሾርባ በሚዘጋጅባቸው የምግብ ዝግጀት (ለድሆች በነፃ ምግብ የሚሰጥበት) ለመስራት፣ ያካባቢ መናፈሻ ቦታ ማፅዳት፣ ወይም ለችሮታ ልብስ ወይም ምግብ ማሰባሰብ። ሁሉም የ MCPS ተማሪዎች ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቅ 75 የ SSL ሰአቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። ስለ ተማሪ የአገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአቶች ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶችንና እድሎችን ፈልጋችሁ አግኙ። እንዲሁም፣በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚከናወኑ የተማሪ የአገልግሎት ትምህርት ሠዓቶች ለትምህርት ቤት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት አስተባባሪ ዓርብ፣ ጃኑወሪ 4/2019 ሪፖርት መደረግ እንዳለበት አይርሱ።