Reimagine, Reopen, Recover:

Fall 2020 Checklist for MCPS Parents/Guardians and Families

Getting Your Child Ready for Virtual Learning Success

 • ዳግም መተለም፣ ዳግም መክፈት፣ ማንሰራራት
  የ MCPS ወላጆች/ሞግዚቶች እና ቤተሰቦች የፎል 2020 የሥራ ዝርዝር
  ልጅዎን ለቨርቹወል ትምህርት ስኬት ማዘጋጀት

  1. መሠረታዊ ነገሮች
  2. የእርስዎ ልጅ መሠረታዊ ቴክኖሎጂ እና ተደራሽነት እንዳለዉ-እንዳላት ያረጋግጡ።
   1. Chromebook እና/ወይም WiFi hotspot ማግኘት አለብዎት (አስፈላጊ ከሆነ)  ከየት ለመውሰድ እንደሚችሉ፣ ቀኖቹን እና ሠዓቱን በሚመለከት ከእርስዎ ትምህርት ቤት ርእሰመምህራን በቀጥታ ለወላጆች መረጃ ይሰጣል።
   2. የ "parent portal" እና ሌሎችም ዲጅታል የመርጃ ሪሶርሶችን ሁሉ እንዴት ለመጠቀም እንደሚችሉ ለማወቅ MCPS Digital Backpack webpage ይመልከቱ
    1. Parent Portal (ParentVUE) Activation/እንዲሠራ ለማስጀመር.ከዓርብ ምሽት ኦገስት 21 ጀምሮ፣ ስለ አዲሱ ፓረንት ፖርታል "parent portal" አክቲቬሽን የሚገልጹ ኢሜሎች እና ደብዳቤዎች ለ MCPS ወላጆች ተልኳል። ወላጅ በፋይላችን ውስጥ ኢሜይል ካለው-ካላት፣ ስለ አክቲቬሽን የሚያስረዳ መግለጫ ይላካል (spam ፋይሎችን መፈተሽ ያስታውሱ)። ወላጅ በፋይል ላይ ኢሜይል ከሌለዉ-ከሌላት፣ደብዳቤ ተዘጋጅቶ በወላጅ አድራሻ ይላካል። ወላጆች አካዉንቶችን አክቲቬት በማድረግ/በማስጀመር ላይ ችግር ካጋጠማቸው፣ ወይም ምንም ግንኙነት ካልደረሳቸዉ፣ የ MCPS የእገዛ መስመርን በ 240-740-7020 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
   3. በቀላሉ ለመከፈት ተደራሽ እንዲሆን የእርስዎን ተማሪ የመክፈቻ-ሎግኢን መረጃ በጽሁፍ ወይም አትመው ያዙት።
   4. ትምህርት ቤት ከመጀመሩ በፊት የእርስዎ የቤት ኢንተርኔት ተገናኝቶ እንደሆነ ያረጋግጡ።
    1. እቤት የኢንተርኔት ግንኙነቱ የሚቆራረጥ ወይም ዝቅተኛ ከሆነ፣እንዴት በነፃ ለማስተካከል እንደሚቻል እዚህ ባለ አምስት ደረጃ መመሪያ ያገኛሉ።
  3. ስለ MCPS የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም ለውጦች እንደሚኖሩ ይገንዘቡ።
   1. አስፈላጊ ከሆነ፣ ስለ FARMS (የነፃ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች) ማመልከቻ መሙላት እንዳለብዎት ያረጋግጡ እና ምግቦችን እንዴት ለማግኘት እንደሚችሉ ያጣሩ። ኦንላይን ስለማመልከት እና ሌሎች በርካታ ዝርዝሮችን እዚህ ለማግኘት ይቻላል።
  4. ለልጅዎ-ለልጆችዎ ለሥራ አመቺ የሚሆን አካባቢ-ሁኔታ ያዘጋጁ።
   1. እቤት ውስጥ ልጅዎ ሥራው(ዋ)ን ለማከናወን የሚችልበት-የምትችልበት ሥፍራ ያግኙ።
    1. አንዳንድ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ግላዊ የሆነ ፀጥታ የሠፈነበት ሥፍራ ይበልጥ ይመቻቸዋል። አንድ ፍንጭ ለመስጠት ያክል፣ የእርስዎን ተማሪ ክፍል በሚጀመርበት ሠዓት ከበስተጀርባ ግርግዳ ላይ ምንም ሌላ ነገር በማይታይበት አካባቢ ያስቀምጡ።
   2. ትኩረት ወይም ሃሳብን ለሚበትኑ ነገሮች ይዘጋጁ።
    1. በተቻለ መጠን፣ ለእያንዳንዱ ልጅ የሚሠሩበት ቦታ ለያይተው ያስቀምጡ።
    2. ለልጆች እንደዚህኛው ዝቅተኛ ዋጋ ያለው አማራጭ ተስማሚ የሆነ የጆሮ ማድመጫ-headphones ወይም earbuds ትኩረት የሚስቡ ድምፆችን ለመቀነስ ይረዳል።
   3. እቤትዎ ውስጥ መሠረታዊ አቅርቦቶች የት እንደሚገኙ ይወቁ ።
    1. እርሳሶችን፣ እስክሪብቶዎችን እና የሚጽፉበት ማስታወሻ ደብተር ወይም ወረቀት አዘጋጅተው በትምህርት ሠዓት ያቅርቡ።
    2. ቤተሰብዎ መሠረታዊ አቅርቦቶች ያስፈልጋቸው እንደሆነ የእርስዎን ትምህርት ቤት ወይም ርእሰመምህር ይጠይቁ።

  2. ለመማር መዘጋጀት

  1. ልጅዎን ለሙሉ ቀን ትምህርት እና ሥራ ማዘጋጀት ይጀምሩ።
   1. መነሳት እና መነቃቃት፦ የእርስዎ ልጅ በቂ እርፍት አግኝቶ(ታ) በግዜ ለመንቃት እና የክፍል ትምህርት በንቃት ለመከታተል እንዲችል-እንድትችል፣ በጊዜ መተኛት እና በጠዋት መንቃትን ያበረታቱ። ጥሩ ቁርስ ይብላ-ትብላ።
   2. መልበስ እና ለትምህርት መዘጋጀት፦ በአካል ትምህርት ቤት ይከታተሉ እንደነበረው ተመሣሣይ የጠዋት ልምዶችን መከተል እንዳለበ(ባ)ት ያበረታቱ። የክፍል ተማሪዎች እና አስተማሪዎቻቸው በስክሪን ላይ እንደሚመለከቷቸው በማስታወስ፣ ተገቢ የሆነ የትምህርት ቤት አለባበስ የሚጠበቅ እና አስፈላጊም ነው።
   3. ምን እንደሚጠበቅ ተወያዩ። በቨርቹወል ትምህርት ሴሚስተር ስለሚጠበቁ ስነምግባሮች፣ ትምህርት የመከታተል እና የመሥራት ሃላፊነቶችን ከልጅዎ ጋር በቅድሚያ ተነጋገሩ። ስኬታማ ለመሆን የሚያስችላቸው ብዙ ድጋፎች መኖራቸውን በሙሉ እንዲያውቁት-እንዲገነዘቡት ያድርጉ።
  2. ከእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት የተላከልዎትን ቨርቹወል የትምህርት መርሃግብር ይመልከቱ።
   1. ትምህርት በቀጥታ ለሚተላለፍበት ጊዜ፣ በራስ አቅም ለመሥራት እና የተማሪ ድጋፍ ለመስጠት በቤተሰብ ውስጥ ሥራ የሚሠሩ አዋቂዎችን ጨምሮ ለእርስዎ ቤተሰብ ፍላጎት የሚመች መርሃግብር ያዘጋጁ።
   2. በቅድሚያ የተላከልዎት የግንኙነት መልእክቶችን በሚመለከት ምላሽ ስለመስጠት ጥያቄ የሚኖርዎት ከሆነ፣ የእርስዎን ተማሪ መምህር(ት) ያግኙ።
  3. ለተከታታይ የወላጅ ዌቢናር-Parent Webinar Series ይመዝገቡ (ለወላጆች)።
   1. በእነዚህ ክፍለጊዜያት ለወላጆች እና ለተማሪዎች የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮችን በሚመለከት ስልጠናዎች ይሰጣሉ።

  3. የመጀመሪያው የትምህርት ቀን - ኦገስት 31/2020 ነው

  1. ከእርስዎ ልጅ አስተማሪ ስለ ትምህርት ክፍል ጉዳዮች እና ማስተማርን በሚመለከት ለሚመጡ መልእክቶች የእርስዎን ኢሜይል ወይም portal ይመልከቱ።
  2. እያንዳንዱ አስተማሪ ለክፍል የሚፈልጋቸውን-የምትፈልጋቸውን ነገሮች ከልጅዎ ጋር በመመልከት ጥያቄ ካላቸው ይጠይቁ።
  3. ስለ ልጅዎ የሚያሳስብዎት ነገር ወይም የሚያዳግቱ ነገሮች ካሉ ማናቸውንም ማወቅ የሚገባቸዉን የተለየ አይነት መረጃ በሚመለከት ለእርስዎ ልጅ አስተማሪ ኢ-ሜይል ይላኩ።
   4. የእኔ ሚና ምንድነው? በሥራ ላይ ለሆኑ ወላጆች እና እንክብካቤ ለሚያደርጉ አዋቂዎች መመሪያ

  እንዴት እንደሚሠራ ፍንጭ፦

  1. የእርስዎን ልጅ የትምህርት ጊዜ ሠሌዳ በእርስዎ የሥራ ጊዜ ሠሌዳ አጠጋግተው ያቅዱ። ለምሳሌ፡-
   1. እርስዎ በሚገኙበት ሠዓት የእርስዎን ልጅ ይበልጥ አዳጋች-ጠንካራ የሆኑ አክቲቪቲዎችን እንዲሠራ-እንድትሠራ ያድርጉ።
   2. እርስዎ ሥራዎ ላይ በሚሆኑበት ወቅት ልጅዎ (ልጆችዎ) ለእርሱ-ለእርሷ-ለእነርሱ በጣም ቀላል የሚሆኑ ምንባቦች እና ትምህርቶች ላይ እንዲሠራ-እንድትሠራ (እንዲሠሩ) ያድርጉ
  2. እድሜ እና የክፍል ደረጃ የሚመጥን የሥራ እና የእቅድ መገልገያ መሣሪያዎችን ዝርዝሮች ይጠቀሙ። የቤት ሥራዎች በጊዜ መሠራታቸውን እና ተጠናቀው መመለሳቸውን ተከታትለው ያረጋግጡ።
  3. እንደሁኔታው መለወጥ.
   1. አንዳንድ ጊዜ ያለ እርስዎ ድጋፍ ልጅዎ ብቻው(ዋ)ን ለመሥራት የማይችልበት-የማትችልበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ያንን ሥራ ለሌላ ጊዜ ለማጠናቀቅ እንዲያቆዩት እና፣ ሌላ ነገር እንዲሠሩ ያድርጉ።
   2. ሙሉ ጊዜ ለሚሠሩ ወላጆች፣ ምሽት እና የሣምንት መጨረሻዎች ልጆቻቸው በእጃቸው ለሚሠሩት-ለሚያሠሩት ትምህርት ምርጥ ጊዜ ይሆናል።
  4. ለልጅዎ አእምሮ ለማሳረፍ እና ለመንቀሳቀስ እረፍት ይስጡ። ስለ ተማሪ የጤንነት ቁመና ትምህርት ሠጪ ፍንጮች እና ሪሶርሶች በ BeWell 365: Be Healthy፣ Be Kind፣ Be You BeWell በይነመረብ ላይ መግለጽ ይቀጥላል። ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ህዳግ-ምልክት በማድረግ ገጹን ዘወትር ይጎብኙ።

  5. እንዴት እርዳታ እንደሚገኝ

  1. ቴክኖሎጂ
   1. MCPS Digital Backpack
   2. ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞ እና ለተማሪዎች ተከታታ የ "Parent Webinar Series" ፕሮፌሽናል ትምህርት
   3. የቴክኖሎጂ ድጋፍ መስመርን በዚህ ስልክ 240-740-7020 ደውለው ያነጋግሩ።
  2. ስለ ማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ትምህርት
   1. BeWell365: ስለ ጤንነት፣ ስለ መልካምነት፣ እራስን መሆን
  3. የ MCPS ፓረንት አካዳሚ
   1. ቤተሰቦች እቤታቸው እንዲመለከቱ ተከታታይነት ያለው ቨርቹወል ዌቢነሮች *አዲስ* የፓረንት አካዳሚ ሊጀመር ነው
  4. ቀውስ ሲፈጠር ጣልቃ መግባት
   1. *አዲስ* "Text-To-911" አሁን በሜሪላንድ ሥራ ላይ ውሏል ድንገተኛ ሁኔታ አጋጥመዎት ከሆነ እና የድምጽ ጥሪ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ፣ ጽሑፍ/ቴክስት ወደ 911 መላክ ይችላሉ። በድንገተኛ አስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተሉ።
    1.  “To” በሚለው መስመር ላይ 911 ያስገቡ
    2. ድንገተኛ/አስቸኳይ ጊዜ ቦታው እና የሚፈለገዉ የአገልግሎት አይነት — ፖሊስ ፣ እሳት አደጋ ወይም አምቡላንስ የሚያካትት አጭር መልእክት ያስገቡ።
    3.  send የሚለውን ይጫኑ ።
    4. ከ 911 ባለሙያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ይስጡ እና የሚሰጥዎትን መመሪያዎች ይከተሉ።
   2. የሜሪላንድ ሠላማዊ ትምህርት ቤቶች ነፃ የአስቸኳይ ጥሪ መስመር - Safe Schools Maryland Hotline: 833-MD-B-Safe (833-632-7233)
   3. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች የመረጃ መስመር - Montgomery County Health & Human Services Information Line: 240-777-1245
   4. የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቀውስ ሁኔታ ማዕከል-Montgomery County Crisis Center: 240-777-4000
   5. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ወጣቶች ቀውስ ሁኔታ ክፍት መስመር - Youth Crisis Hotline of Montgomery County: 301-738-9697
   6. ባለፈው ሣምንት quicknotes ላይ የነበረውን አዲሱን "text to 911 for Maryland" ለመጨመር ይፈልጋሉ?
  5. አስፈላጊ የግንኙነት አካላት
   1. የግንኙነት መረጃዎችን በቀላል ማግኘት በሚችሉበት ያስቀምጡ፦
    1. የእርስዎ ልጅ መምህራን
    2. የእርስዎ ልጅ ርእሰመምህር(ት) እና ትምህርት ቤት
    3. የቴክኒክ ድጋፍ

  እቤት ውስጥ አዳጋች ሁኔታዎች ካለብዎት፣ ከእርስዎ ልጅ አስተማሪ እና/ወይም የትምህርት ቤቱ ርእሰመምህር ጋር ይነጋገሩ። በሌላ ቋንቋ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ AskMCPS በስልክ ቁጥር 240-740-3000 ይጠይቁ።

  የ MCCPTA Safe Tech Committee ከ MCPS ጋር በመተባበር የተሰጠ 6 ፍንጮች
  የእርስዎን ልጅ ቴክኖሎጂ ለትምህርት ማዘጋጀት

  1. ከ MCPS-የተሰጡት Chromebooks አዘናጊ ነገሮችን ለመቀነስ ታስቦ አግባብነት የሌላቸውን ነገሮች ልጅች እንዳይከፍቱ የተዘጉ-“locked down” ናቸው። ነገር ግን የግል ዲቫይስ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ሌሎች የማያስፈልጉ ነገሮችን እየተመለከቱ እንዳይዘናጉ የወላጅ መቆጣጠሪያውን ይዝጉት።
  2. የልጅዎን ስክሪን ወደ ግርግዳ ወይም ወደ መስኮት አቅጣጫ ሳይሆን እርስዎ (ወይም በአጠገብ የሚያልፍ ሰው) ለማየት ወደሚችሉበት አቅጣጫ መሆን አለበት።
  3. ከእያንዳንዱ 20  ደቂቃ በኋላ ዓይንን ማሳረፍ እና ሰውነትን ማፍታታት ያበረታቱ።
  4. በትምህርት ሠዓት የእጅ ስልኮችን ያስወግዱ።
  5. በትምህርት ሠዓት እቤት ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ዲቫይሶች በሙሉ ማስታወቂያዎችን ይዝጉ። ይህ አእምሮን ከመዘናጋት ያድናል!
  1. በተገቢ ሁኔታ መልበስ ያስፈልጋል እና ሌሎች ሰዎች እንዲመለከቱ የማይፈልጉት ምንም ነገር በስተጀርባ-በአጠገብ እንደማይታይ ያረጋግጡ።

Monitoring Your Kids' Social Media
icon schedulle