Skip to main content

Amharic 10-12-2023


ኦክቶበር 4, 2023

ከኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር 4 ለሚካሄደው የአእምሮ ጤና የግንዛቤ ሳምንት ጊዜዎን ይቆጥቡ።

MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች ሳይኮሎጂስቶች ማህበር (MCSPA) ኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር 4 ባለው ሳምንት ወጣቶች እና ቤተሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ እድል ለመስጠት ነጻ ዝግጅቶችን ያስተናግዳሉ። የዝግጅቱ ሳምንት በአካል እና ቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ተናጋሪዎች ይኖራሉ፣ እና ወርክሾፖችንም ያካትታል፥ ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 4 ቨርቹዋል የሪሶርስ ትርኢት እና የኤክስፐርቶች ፓነል ይደመደማል።

 

እሮብ፣ ኖቬምበር 1 ከቀኑ 6–8 p.m. በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የቀድሞ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች በኋላም የአይምሮ ጤና ኤክስፐርት እና አቀንቃኝ የሆኑት ዶ/ር ጄይ ባርኔት ስለ አእምሮ ጤንነት፣መገለልን ማስወገድ እና እርዳታ መፈለግን በሚመለከት ለተማሪዎች በአካል ንግግር ያደርጋሉ። ይህ ዝግጅት MCPS-TV እና MCPS en Español ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ኖቬምበር. 4 ከቀኑ 11:30 a.m.–1 p.m. የሚካሄደው ቨርቹዋል የሪሶርስ ትርኢት እና ፓነል፣ ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው መገልገያ MCPS ያለውን የአእምሮ ጤናን የሚመለከቱ ሪሶርሶች፣አቅራቢዎች እና የማህበረሰብ አጋሮችን መረጃ ይሰጣል።

 

የሳምንቱ ዝግጅት ስለ ጤናማ ልማዶች፣ አወንታዊ የት/ቤት ሁኔታ፣ ልዩነትን በእኩልነት መደገፍ እና የማህበራዊ ስሜታዊ ቃላትን በአግባቡ በመጠቀም ችግሮችን መፍታት በመሳሰሉ ርእሶች ላይ አስቀድሞ የተቀረጹ ቪዲዮዎችን ያቀርባል። የአእምሮ ነርቭ ልዩነት/neurodiversity፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ደህንነት፣ ዮጋ እና ህመም ማስታገሻ፣ እና የአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም መከላከልን በተመለከተ ከባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስና ውይይት ይደረጋል።

 

በቅርቡ የሚጀመር፡ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች እና ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ ማመልከቻዎችን ለማቅረብ ክፍት ይሆናል።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ሰፊ እድሎች ይኖራቸዋል። ኦክቶበር 10 ማክሰኞ ቀን፣ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ParentVUE ማመልከቻ በመጠቀም ለሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች የማመልከት እድል አላቸው። በተጨማሪም ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ኦንላይን የፍላጎት ቅጽ በመጠቀም ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ ክፍለ-ጊዜዎች የሚኖሩ ሲሆን ሁሉም ቀናትልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ተዘርዝረዋል።


ማመልከቻዎችን ለማቅረብ እስከ ኖቬምበር 3 ድረስ ክፍት ይሆናል። ፕሮግራሞች-በጨረፍታ/Programs-At-A-Glance፣ስለ ብቁነት፣ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ኦክቶበር open house dates በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያገኛሉ፡ https://www.montgomeryschoolsmd.org/curriculum/specialprograms/high/

 

በዚህ ዓመት አዲስ የሚተገበር፡ 2ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች MCPS ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ትምህርት ቤት ማመልከቻ ፕሮግራሞች ጋር በማጣመር በሁለት የመግቢያ ምእራፎች ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ (MVA) ማመልከት ይችላሉ። የመጀመሪያው ዙር ከማክሰኞ፣ ኦክቶበር 10 እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 3, 2023 የሚካሄድ ሲሆን ወደ 2024–2025 የትምህርት አመት የሚሸጋገር እና እንዲሁም ለአሁኑ 2023–2024 የትምህርት አመት 2ኛ  ሴሚስተር በተጠባባቂ ዝርዝር የሚያዝ ነው። ሁለተኛው ዙር ከዓርብ ጃኑዋሪ 5 እስከ ፌብሩዋሪ 9፣ 2024 የሚካሄድ ሲሆን  2024-2025 የትምህርት አመት ተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ የሚካተት ነው። MVA በ PreentVUE ላይ ተጨማሪ ማመልከቻ አለው። ተማሪዎች MVA እንዲገቡ መደበኛው ማመልከቻ እና MVA ማመልከቻ ሁለቱም መሞላት አለባቸው።


MVA የሙሉ ጊዜ ኦንላይን የመማሪያ ስልት ሲሆን ሁለቱንም የተቀናጀ (ቀጥታ) እና ያልተቀናጀ (ገለልተኛ) የመማር ማስተማር ስልት የሚጠቀም የተዋሃደ ትምህርት ሞዴል ነው። MVA ዋና ትኩረቱ የሁሉንም ተማሪዎች ግላዊ ፍላጎቶች የሚያሟላ፣ ሁሉንም ያካተተ የኦንላይን ትምህርት አቅርቦትን ማሳደግ ነው።


እሮብ፣ ኦክቶበር 11 ከቀኑ 7 P.M.  ፍላጎት ላላቸው ቤተሰቦች በሙሉ መረጃዊ ዌቢናር ይኖራል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን MVA ድረገጽ ይጎብኙ: https://www2.montgomeryschoolsmd.org/schools/virtualacademy/news-index/2023-2024-school-year/

 

ለቅዳሜ ትምህርት ቤት (Saturday School) ምዝገባ አሁን ክፍት ነው።


George B. Thomas Sr. Learning Academy, Inc.፣ እንዲሁም ቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School በመባል የሚታወቀው ት/ቤት 2023–2024 የትምህርት አመት ምዝገባ ክፍት ነው። የቅዳሜ ትምህርት ቤት K–12ኛ ክፍል በሂሳብ እና በእንግሊዝኛ/ቋንቋ ስነ ጥበብ የአካዳሚክ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይሰጣል።


በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የቆየ የማስጠናት እና የማማከር ፕሮግራም ሴፕቴምበር 30 በስምንት ቦታዎች ላይ ተጀምሯል፣እንዲሁም ቨርቹዋል አማራጭ ይሰጣል። ሥርዓተ ትምህርቱ MCPS ጋር የተጣጣመ ከመሆኑም በላይ የሚያስተምሩት ሠርተፊኬት ያላቸው መምህራን ናቸው። ቦታዎቹ፦ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ አልበርት አንስታይን፣ ፔይንት ብራንች፣ ስፕሪንግብሩክ፣ ዊተን፣ ጌትስበርግ፣ ክላርክስበርግ እና ኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ዓመታዊ ወጪው $85፣$40 ለነጻ እና ለቅናሽ ዋጋ ምግብ (FARMs) ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች። 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School ምዝገባ እዚህ ይገኛል። ለመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ እዚህ ይገኛል።
በ$150 ተጨማሪ ክፍያ፣ የቅዳሜ ትምህርት ቤት ለአምስት ሳምንት ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ ትምህርት ይሰጣል።


ቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School በክላርክስበርግ፣ስፕሪንግብሩክ፣ እና ኖርዝዌስት አንደኛ ደረጃ እና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የእንግሊዝኛ እና የሂሳብ ትምህርት የግል አስተማሪዎችን/tutors ይፈልጋል። እንዲሁም ለኮዲንግ እና ለሮቦቲክስ የግል አስተማሪዎችን ይፈልጋሉ። የግል አስተማሪዎቹ ሠርተፊኬት ያላቸው አስተማሪዎች መሆን አለባቸው። ሰዓቱ 8፡15–11፡15 a.m. ሲሆን ማካካሻ በሰአት $38 ይከፈላል።


ለአጠቃላይ መረጃ 301-287-8980 ይደውሉ።


በነዚህ ት/ቤቶች በግል ማስተማር ከፈለጉ፦

  • ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ Terrence Fisher ያነጋግሩ
  • ኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ Elyse Ridges ያነጋግሩ
  • ስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ Nikki Morales ያነጋግሩ

ቅዳሜ ትምህርት ቤት 2023–2024 ቀን መቁጠሪያ/Saturday School 2023–2024 Calendar

 

ከቤት ውጪ የሚካሄድ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ትምህርት 60ኛ አመቱን ኦክቶበር 14 ያከብራል።


ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቡ ከቤት ውጭ የአካባቢ ትምህርት ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 14 ከቀኑ 10 a.m.–1 p.m. Lathrop E. Smith Environmental Education Center, 5110 Meadowside Lane in Rockville፡ 60ኛ አመቱን የሚያከብር ስለሆነ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።


ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ፦

  • ከቤት ውጪ የሚሰጥ የአካባቢ ትምህርት መስራች ከሆነው ጆ ሃዋርድ/Joe Howard እና በአካባቢ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ከመረጡት ከቀድሞ ተማሪዎች ይሰማሉ።
  • በደን መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ላይ ይሳተፉ እና ዱባ አስጊጠው ወደ ቤትዎ ይውሰዱ።
  • በዊህልስ የሳይንስ መስክ ጣቢያ የሜሪላንድን ግብርና እና ተፈጥሮን ይቃኙ።
  • ስለ ተፈጥሮአዊ ዓለም እና ስለ አካባቢ ጥበቃ አስተዳደር የበለጠ ለማወቅ የተለያዩ ትርኢቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ይጎብኙ።

ቬንደሮቹ የሚከተሉትን እንደሚያካትቱ ይጠበቃል፡- ሞንትጎመሪ ፓርኮች፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአካባቢ ጥበቃ ዲፓርትመንት፣ ኢዛክ ዋልተን ሊግ፣ ኔቸር ፎርዋርድ፣NASA፣ የሜሪላንድ የግብርና ትምህርት ፋውንዴሽን፣ MCPS ዘላቂ የከባቢ ጥበቃ ዲቪዝዮን፣ ኔሽን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ የፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግሎባል ኢኮሎጂ ፕሮግራም፣ ዋን ሞንትጎመሪ ግሪን፣ ሜዳውሳይድ የተፈጥሮ ማዕከል እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የደን ጥበቃና እንክብካቤ ቦርድ።

 

 

 

 

ሁለተኛው ዙር አመታዊ የላቲን ሌጋሲ ኮንፈረንስ ኦክቶበር 14 ይካሄዳል።

ቅዳሜ ኦክቶበር 14 የተዘጋጀው ሁለተኛው ዙር አመታዊ የላቲና ሌጋሲ ኮንፈረንስ  የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የላቲን ሴት ተማሪዎችን ለማበረታታት እና ለማነሳሳት የሚደረግ ዝግጅት ነው። ይህ በነጻ የሚከናወነው ዝግጅት በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ታኮማ ፓርክ/ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ 9 a.m. to 3 p.m. ይካሄዳል። ዋናው ተናጋሪ በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት ቪልማ ናጄራ ናቸው።

የዘንድሮው የኮንፈረንሱ ጭብጥ ¡Unidas, Adelante! ውይይት የሚደረግባቸው አርእስቶች የላቲና ደህንነት እና የአእምሮ ጤና፣ ላቲና በትምህርት፣ ላቲናን ማብቃት፣ እና ማህበራዊ ፍትህ እና የላቲን ተማሪ ድምጽ የተሰኙትን ጉዳዮች ያካትታሉ።

ዝግጅቱ፦ MCPS Office of Strategic Initiatives, Montgomery College and Poder Educators. ተቀናብሮ የሚቀርብ ነው። ለመመዝገብ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እስከ ሰኞ፣ ኦክቶበር 9 ድረስ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የትምህርት ቤታቸውን ተወካይ ማግኘት አለባቸው።

9ኛ ክፍል ተማሪ ላላቸው ወላጆች በሙሉ የተደረገ ጥሪ፡ ስለ ውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ የጥያቄ እና መልስ ፕሮግራም ለኦክቶበር 24 ተዘጋጅቷል።

የስርአተ ትምህርት እና የትምህርት ፕሮግራሞች ፅህፈት ቤት ስለ ቅርብ ጊዜው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ማክሰኞ ኦክቶበር 24 ቀን 6 p.m. ቨርቹዋል የወላጅ/አሳዳጊ የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ አዘጋጅቷል።

 

ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች 2023-2024 የትምህርት አመት (2027 ተመራቂዎች) ጀምሮ፣ የሜሪላንድ አጠቃላይ የምዘና ፕሮግራም (MCAP) የመጨረሻ ኮርስ (EOC) የሳይንስ እና የስነመንግስት ትምህርት ፈተናዎች ከተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባዮሎጂ እና የስነመንግስት ኮርሶች (NSL) የመጨረሻ ክፍል 20 ፐርሰንት ይያዛል።


20 ፐርሰንቱ በሁለተኛው ሴሚስተር ወይም ሴሚስተር B ኮርስ የመጨረሻ ውጤት ላይ ይሰላል። ተማሪዎች ለመመረቅ EOC ፈተናዎችን ማለፍ አይጠበቅባቸውም ነገር ግን ለመመረቅ የሚያስፈልገውን የኮርስ ክሬዲት ለማግኘት ኮርሱን ማለፍ አለባቸው። መስፈርቱ በአሁኑ ጊዜ በማናቸውም ክፍሎች ወይም AP ወይም IB ደረጃ ባዮሎጂ እና የስነመንግስት ኮርሶች ለሚማሩ ተማሪዎች አይተገበርም።


ይህ ለውጥ የተደረገበት ምክንያት በስቴቱ ፖሊሲ ላይ በተደረጉ ለውጦች የተነሣ ነው። ጁላይ 25, 2023 የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ በሜሪላንድ ህግጋት 13a.03.02 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ መስፈርቶች ላይ ለውጦችን አፅድቋል።

 

ይህ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (ተደጋጋሚ ጥያቄዎች) ሰነድ MCAP የሁለተኛ ደረጃ ኮርስ የመጨረሻ ፈተናዎች ትግበራ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ይህ ሰነድ በየጊዜው ይሻሻላል፣ እና ወቅታዊ እትም የሜሪላንድ ፐብሊክ ስኩልስ በይነመረብ ላይ ይገኛል።

 

ቨርቹዋል የጥያቄና መልስ Q&A ክፍለ ጊዜ

ቀን: ማክሰኞ፣ኦክቶበር 24 ቀን 6 p.m.

ስብሰባ አገናኝ/ሊንክ:

https://mcpsmd.zoom.us/j/87155024563?pwd=akRNU1VJQlFrZTZaakJxRE5JWU1KQT09

ኦክቶበር 21 የትምህርት ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 21 ከጠዋቱ 8:30 a.m.–5 p.m. በመጀመሪያው USA የትምህርት ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል

ፖቶማክ በሚገኘው የሴይንት አንድሪው ኤፒስ ቆፖሳል ትምህርት ቤት የለውጥ እና የማሻሻል ትምህርት ማዕከል ዝግጅቱን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ ይህም መምህራንን፣ ተመራማሪዎችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን የሚያገናኝ እና AI፣ የመማር ሳይንስ፣ የተማሪ እና የመምህራን ደህንነት፣ አሰልጣኝ እና የትምህርት ቤት ዲዛይን የመሳሰሉትን ግንባር ቀደሞቹን የት/ቤት ለውጦች ያጠቃልላል። ዝግጅቱ በዩናይትድ ኪንግደም በዌሊንግተን ኮሌጅ በየጊዜው የሚካሄድ ታዋቂ ሁነት ሲሆን ይህ የትምህርት ፌስቲቫል ዝግጅት በዩናይትድ ውስጥ የሚካሄደው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

የእለቱ አጀንዳ ከ50 በላይ ክፍለ-ጊዜዎች እና ከተናጋሪዎች ዝርዝር ውስጥ የትምህርት ዲፓርትመንት ረዳት ጸሐፊ ሮቤርቶ ሮድሪጌዝን፣ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን ያካትታል። ከአካባቢ የት/ቤት ዲስትሪክቶች መሪዎችን እና የፖሊሲ አውጪዎችን እንዲሁም የጆንስ ሆፕኪንስ የትምህርት ፖሊሲ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ስቲነርን ይገኛሉ።

MCPS ሰራተኞች፣ አስተዳዳሪዎች እና ቤተሰቦች በምዝገባ ወቅት በዚህ ኮድ ቅናሽ የቲኬት ዋጋ ሊያገኙ ይችላሉ። ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ይኖራል። ጥያቄ ካላችሁ ግሌን ዊትማንን ያግኙ።

Regeneron Science Talent Search አሁን ክፍት ነው!

2024 Regeneron Science Talent Search (Regeneron STS) ለማመልከት አሁን ክፍት ነው! በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየሮች ከወደፊቱ የሳይንስ መሪዎች አንዱ ለመሆን እና $250,000 ከፍተኛ ሽልማት ለማግኘት የመጀመሪያ ምርምራቸውን ለሀገሪቱ አንጋፋ STEM የተማሪዎች ውድድር ለማቅረብ ይህንን እድል በጉጉት ይጠባበቃሉ።

ኦንላይን ማመልከቻ ድርሰቶችን፣ ስለተማሪዎች እና ምርምሮቻቸው ጥያቄዎች፣ ከመምህራን እና ከግል አስተማሪዎች የተሰጡ ምክሮችን እና ሌሎችም ዋናውን የጥናት ወረቀት ማቅረብን ያካትታል። የዚህ ዓመት የመጨረሻ ቀነ ገደብ ረቡዕ፣ ኖቬምበር 8፣2023 ከቀኑ 8 p.m. ET ነው።

 

ምርጥ 300 ምሁራን እያንዳንዳቸው $2,000 የሚያገኙ ሲሆን ትምህርት ቤቶቻቸውም እንዲሁ ያገኛሉ። ቢያንስ $25,000 እና የሚከፈልበት የመጨረሻ ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ለ40 ለፍጻሜ የደረሱ እጩዎች ስለሚሰጥ ተማሪዎችዎ እንዳያመልጣቸው።

 

ለፕሮግራሙ አዲስ ነዎት? ይህን አጭር መመሪያ የላክነው ለእርስዎ ብቻ ነው– በዲስትሪክትዎ ካሉ አስተማሪዎች እና ተማሪዎች ጋር ዛሬ ይህንኑ ቃል ማሰራጨትዎን ያረጋግጡ።

በዚህ አመት ከማህበረሰብዎ የመጡ ተማሪዎችን በአመልካቾች ዝርዝር ውስጥ ለማየት እንጠባበቃለን!

 

የኪነጥበብ እና ሰብአዊ ምክር ቤት አመታዊ የተማሪ ኪጥበብ ተግባራት መመሪያ አውጥቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኪነጥበብ እና ሰብአዊ ካውንስል CultureSpotMC 2023-2024 የትምህርት አመት የተማሪ ኪነጥበብ እንቅስቃሴዎች መመሪያ መውጣቱን ሲያበስር በጣም ደስታ ይሰማዋል።

ይህ መመሪያ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ፈጠራን፣ መማርን እና ንቁ የጥበብ ማህበረሰብን እውቅና ይሰጣል። ካውንስሉ በሁሉም ዕድሜ ላሉ ተማሪዎች ተስማሚ የሆኑ አስደሳች የኪነጥበብ ዝግጅቶችን፣ ፕሮግራሞችን እና ተግባራትን አዘጋጅቷል። ወላጅ፣ አስተማሪ ወይም ተማሪ፣ ቢሆኑ በዚህ አመት መመሪያ ውስጥ ለሁሉም የሚሆንና የሚስማማ ነገር አለ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያለውን የተማሪዎች ስነጥበብ እንቅስቃሴዎችን ለማሰስ ዝግጁ ነዎት?

2023-2024 የትምህርት አመት መመሪያ እዚህ ተመልክተው ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ኪነጥበብ ያመራሉ።

መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 5 – የወላጅ አካዳሚ MCPS አትሌቲክስ - #WeR.A.I.S.E.

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 5—አርብ፣ ኦክቶበር 6 – ተማሪዎች በቅድሚያ የሚለቀቁባቸው ቀኖች (ኢኖቬቲቭ ት/ቤቶች)

ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 7 - SAT ፈተና የሚሰጥበት ቀን

ሰኞ፣ ኦክቶበር 9 – ለሠራተኞች የሙያ ማበልፀጊያ ቀን ስለሆነ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት የለም (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)

እሮብ፣ ኦክቶበር 11 - PSAT ፈተና ይካሄዳል

እሮብ፣ ኦክቶበር 11 – የወላጅ አካዳሚ፡ ስለ አዎንታዊ/ፖዚቲቭ ዲስፕሊን

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 12 – የትምህርት ቦርድ ስብሰባ

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 12 – የወላጅ አካዳሚ፡ ንቁ ወላጅነት አሁን! ክፍል 1

ሰኞ፣ ኦክቶበር 16 – የወላጅ አካዳሚ፡ ቅድመ ጥንቃቄ፡ በአስቸጋሪ ጊዜያት ጭንቀትን ስለመቋቋም

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 17 – የትምህርት ቦርድ የሥራ ማስኬጃ በጀት የስራ ክፍለ ጊዜ

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 17 – የወላጅ አካዳሚ፡ ፊደላትን ከድምፅ ጋር በማቀናጀት የንባብ ችሎታን በቤት ውስጥ ማዳበር

እሮብ፣ ኦክቶበር 18 – የወላጅ አካዳሚ፡ ለልጆች እና ለታዳጊ ወጣቶች በኦንላይን የሚሰጥ የደህንነት ምክር አገልግሎት

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 19 – የወላጅ አካዳሚ፡ ንቁ ወላጅነት አሁን! ክፍል 2