Skip to main content

የወሰን-ክልል ዝርዝር ጥናት

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አሁን ያለው የትምህርት ቤት እና የክለስተር ወሰን የትምህርት ቤት መገልገያዎችን/ፋሲሊቲዎችን ተፈላጊውን ውጤት የሚያስከትል ብቁ አጠቃቀም እንዴት እየደገፈ እንዳለ ወይስ መሰናክል እንደሆነ የውጭ ኮንሰልታንቶችን በመጠቀም በጥልቀት ጥናት እንዲደረግ እና በዝርዝር እንዲቀርብ ሱፐርኢንተንዳንቱ እንዲጠየቁ ጃኑወሪ 8/2019 የትምህርት ቦርድ ወስኗል። ቦርዱ የኮንሰልታንቶችን የሥራ አድማስ በሚመለከት፣ ስለ ዲስትሪክቱ የትምህርት ቤት እና የክለስተር ማካለል የጥናት ማዕቀፍ፣ እና ኮንሰልታንቶቹ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ሥራ ላይ እንዴት ማተኮር እንዳለባቸው ከማህበረሰቡ አስተያየቶችን ይሰበስባል። (ማሳሰቢያ፦ እስካሁን ምንም የተለየ የማካለል አስተያየቶች ትግበራ አልተደረገባቸውም። የመሰባሰቡ ዓላማ አስተያየቶችን/ሃሳቦችን ለማግኘት እና የኮንሰልታንቶቹን ሥራ ለመግለጽ ነው።)
ሒደቱን በሚመለከት፦ ይህንን ዝርዝር ጥናት የሚያደርጉ የውጭ ኮንሰልታንቶችን ለመምረጥ ፕሮፖዛሎችን መጠየቂያ ይሰጣል። በኮንሰልታንቶች የሚካሄደው የግምገማ ጥናት የተለየ ትምህርት ቤትን ምደባ ለመቀየር ታስቦ አይደለም። ኮንሰልታንቶቹ የመጨረሻ ሪፖርት እና ግኝት አማራጮችን ስፕሪንግ 2020 ላይ ለቦርድ ያቀርባሉ። የኮንሰልታንቶችን ጥናታዊ ትንታኔ ተከትሎ መወሰድ ያለበትን ቀጣይ እርምጃ ቦርዱ ይወስናል። ወደፊት ስለ ተማሪ ምደባ የማካለል ውሳኔ ለመስጠት ማናቸውም ሒደት በቀጣይነት ሊደረግ የሚችለው ስለ ትምህርት መገልገያዎች እቅድ "Educational Facilities Planning" የቦርድ ፖሊሲ - Board Policy FAA፣ ላይ የተገለጹትን አራት ምክንያቶች መሠረት በማድረግ ይሆናል። እነዚህ አራቱ ምክንያቶች፦ የተማሪዎች ስብጥር፣ ማህበረሰቡ ለትምህርት ቤቶች ያለው ጂኦግራፊያዊ ቅርበት፣ ምደባዎቹ በቀጣይነት የሚኖራቸው ዘለቄታ፣ የተመዝጋቢ ብዛት እና የትምህርት ቤት ስፋት/አቅም ናቸው።
ስለ ማካለል በትምህርት ቦርድ ማርች 7/2019 የተደረገውን ውይይት ይመልከቱ
ቪድዮ አገናኝ ወይም ምስሉን ይጫኑት

ውሳኔውን ያንብቡ

Boundary Assessment Study Given Revised Policy FAA, Educational Facilities Planning-Jan 8, 2019

ወደፊት የሚደረጉ የማህበረሰብ ውይይት ቀኖች
(ሁሉም ስብሰባዎች የሚካሄዱት ከ 7:00 p.m. እስከ 9:00 p.m. ነው)

ኤፕሪል 4: Quince Orchard High School 15800 Quince Orchard Road Gaithersburg, MD 20878
ኤፕሪል 10: John F. Kennedy High School 1901 Randolph Road Silver Spring, MD 20902
ኤፕሪል 11: Earle B. Wood 14615 Bauer Drive Rockville, MD 20853
ኤፕሪል 23: Walter Johnson High School 6400 Rock Spring Dr. Bethesda, MD 20814
ከእነዚህ ሁነቶች ለየትኛውም ለመመዝገብ -  RSVP