5 Things to Know

MCPS Things to Know

Thursday, May 4

  1. የልዩ ትምህርት ተማሪዎች ወላጆች የስቴት ዳሰሳን እንዲያጠናቅቁ ተጠየቁ

ልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት የሚያገኙ ከ3 እስከ 21 አመት የሆናቸው ልጆች ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እስከ አርብ፣ ሜይ 19 ድረስ በሜሪላንድ ልዩ ትምህርት የወላጅ ተሳትፎ ዳሰሳ ላይ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ።

የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) የዳሰሳ ጥናቱን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሚገኙ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ በፖስታ ተልኳል። የሚሰጠው መረጃ ስቴቱ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ልዩ ትምህርትና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል።

ዳሰሳውን ለመሙላት ሁለት አማራጮች አሉ።

  1. ይህን በይነመረብ በመጠቀም ዳሰሳውን ኦንላይን ይሙሉ https://www.mdparentsurvey.com.
  2. ከ MSDE የተላከውን የልጅዎ የክፍል ዳሰሳ ጥናት የወረቀት ኮፒ ሞልተው ካጠናቀቁ በኋላ በተከፈለበት ኤንቨሎፕ ላይ እስከ አርብ፣ ሜይ 19 ድረስ በፖስታ ቤት መልሰው ይላኩ።

ተሳትፎ የሚደረገው በፈቃደኝነት ሲሆን ማንነት ይፋ አይደረግም። አገልግሎቶችን ለሚያገኙ ለእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች የተለየ የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ ይጠየቃሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎን MSDE በስልክ ቁጥር፡ 410-767-7770 Kenneth Hudock ያነጋግሩ።
ወይም በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉ፡ Kenneth.Hudock@maryland.gov

  1. አመታዊ የጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል ሜይ 20 ይካሄዳል።

 

ልህቀት ያላቸው መጽሐፍት፣ ጸሃፊዎች/ደራሲያን እና የሊተርሲ ጠበብት በዓል በጌትስበርግ/ Gaithersburg ማህበረሰብ የሚከበርበት ቀን ስለሆነ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። የዘንድሮው የጌትስበርግ/ Gaithersburg የመፅሃፍት ፌስቲቫል/አውደ ርእይ ቅዳሜ፣ ሜይ 20 ከቀኑ 10 a.m.–6 p.m. በጌትስበርግ ቦህሬር ፓርክ/Bohrer Park in Gaithersburg ይካሄዳል። በፌስቲቫሉ የምርጥ ደራሲዎች ስብስብ እና በሁሉም እድሜ ላሉ ልጆች፣ የስነ ፅሁፍ አውደ ርእይ ለታዳጊዎች፣ ለጎልማሶች እና ለሌሎችም አስደሳች ክፍለጊዜ ይካሄዳል። እድሜአቸው 16 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን (SSL) ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ የፌስቲቫሉን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

  1. የተራዘመ የትምህርት አመት ሠመር ፕሮግራም ቡድን ይቀላቀሉ

 

ስለ ልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ስላሉት የስራ መደቦች የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ እሮብ፣ ሜይ 10 ከቀኑ 6–7:30 p.m. ቨርቹወል ፕሮግራም ስለሚካሄድ MCPS እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ዲፓርትመንቱ በተራዘመ የትምህርት ዓመት (ESY) ለሠመር ፕሮግራም ክፍት የሥራ ቦታዎችን ለመሙላት ይፈልጋል። ለተራዘመ የትምህርት ዓመት (ESY) የስራ መደቦች የተቀጠሩ መምህራን እና ፓራኢጁኬተርስ አሁን ካላቸው ደሞዝ በተጨማሪ 18% የማበረታቻ ክፍያ ያገኛሉ። የልዩ ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሥፍራው ይገኛሉ። እባክዎ ይመዝገቡ

ስብሰባ መግቢያ አገናኝ ቁጥር/Meeting: Zoom link
ስብሰባ መግቢያ ቁጥር/Meeting ID: 810 0827 8171
የይለፍ ኮድ ቁጥር (Passcode)፦ 898137

  1. ለመጀመሪያው የተማሪዎች የአየር ንብረት አክሽን ካውንስል ማመልከቻ ለማቅረብ ክፍት ነው።

ለዘለቄታው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚወዱ 8ኛ እስከ11ኛ ክፍል ያሉ የ MCPS ተማሪዎችን ያውቃሉ? አሁን ለተማሪ የአየር ንብረት አክሽን ካውንስል አባልነት ለማመልከት ክፍት ነው። አዲስ የተቋቋመው የተማሪዎች ካውንስል የሚከተሉትን ተግባሮች ያከናውናል፦

  1. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት።
  2. ስለ ዘላቂ የአየር ንብረት ለውጥ የመከላከል እርምጃ ለትምህርት ቦርድ እና ለሱፐርኢንቴንደንት ማማከር።
  3. በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ዘላቂነት ያለው የተማሪ ፕሮጄክቶችን ጥያቄ ይገመግማል፣ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ እንዲገኝ ይጠይቃል/ያግባባል።
  4.  ዘላቂነት ያለው ተነሳሽነትን ለማስተዋወቅ፣ ለመደገፍ እና ለማጎልበት፣ እና በሚመርጡት ሌሎች ትኩረቶች ላይ ለመስራት ከትምህርት ቤቶች እና ከተማሪዎች ጋር አጋር ይሁኑ።
  1. የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች

ተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች ለስኬታቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
"Montgomery County Black School Educators (MCABSE)" አመታዊ የአፍሪካን-አሜሪካን ምሁራን እና የማህበረሰብ መሪዎች የሽልማት ስነስርአት ላይ 27 ተመራቂ ሲንየር ተማሪዎችን እውቅና ሰጥቷል።
የትምህርት ቦርድ (BOE) የላቀ አገልግሎት ላበረከቱ 17 ግለሰቦች እና ድርጅቶች እውቅና ይሰጣል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በ 26ኛው አመታዊ የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም በህዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ላበረከቱት ሽልማቶችን እንደሚሰጥ አሳውቋል። የቀረቡት እጩዎች ከአጠቃላይ ማህበረሰብ፣ ከማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከንግድ ድርጅቶች፣ ከቦርድ አባላት እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች የተጠቆሙ ናቸው።
የበለጠ ለማወቅ የአሸናፊዎችን ሙሉ ዝርዝር ይመልከቱ።

ለወላጆች የመረጃ ክፍለ ጊዜ፡ ዝነኛ ባህል እና ጥላቻ፡ የእርስዎ ተማሪ በወቅቱ ማህበረሰቡ ውስጥ ያጋጠመውን/ያጋጠማትን መረዳት
ይህን ክፍለ ጊዜ የሚመሩት Liza Wiemer/ሊዛ ዊመር “The Assignment መጽሐፍ ደራሲ ናቸው። በተወዳጅ ባህል ውስጥ ጥላቻ እንዴት እንደሚስፋፋ፣ ጨዋታ እና ማህበራዊ ሚዲያ፣ በት/ቤቶች ውስጥ የጥላቻ ንግግሮች እና ድርጊቶች ጥቅም ላይ የሚውሉባቸውን መንገዶች እና ወላጆች እና አሳዳጊዎች ተማሪዎቻቸው የጥላቻ ንግግርን እንዲለዩ እና እንዲቃወሙ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ወላጆች እና ተንከባካቢዎች እንዲገነዘቡ በመርዳት ላይ ያተኩራል።የሚካሄድበት ሠዓት 7 PM - 8:30 PM
(እንግሊዝኛ) ሜይ 10፣ 2023 የመመዝገቢያ አገናኝ/Registration Link (እንግሊዝኛ በራሪ ወረቀት)
(ስፓኒሽኛ) ሜይ 31፣ 2023 የመመዝገቢያ አገናኝ/Registration Link (የስፓኒሽኛ በራሪ ወረቀት)



4. Applications Open for First Student Climate Action Council

 an MCPS student in grades 8-11 who is passionate about sustainability and combating climate change? Applications are now open for the Student Climate Action Council. The newly created council of students will work to:

  • Create the MCPS Climate Action Plan.

  • Advise the Board of Education and superintendent on sustainability/climate action.

  • Solicit, review and fund student sustainability projects in MCPS schools.

  • Partner with the schools and students to promote, support and empower sustainability initiatives, and work on other priorities they choose.


5. Bright Spots This Week

Graduating Seniors Recognized for Achievements

The Montgomery County Alliance of Black School Educators (MCABSE) honored 27 graduating seniors during its annual Distinguished African-American Scholars and Community Leaders Awards Ceremony on April 26. 


BOE to Recognize 17 Individuals, Organizations for Distinguished Service

The Montgomery County Board of Education has announced its recipients for the 26th Annual Awards for Distinguished Service to Public Education. Nominations were received from the general community, as well as community organizations, businesses, Board members and MCPS staff.

Learn more and see the full list of winners.


Information Session for Parents: Popular Culture and Hate: Understanding What Your Student Is Exposed to in Society Today

This session will be led by Liza Wiemer, author of The Assignment. It will focus on helping parents and caregivers understand how hate is spreading through popular culture, gaming and social media, ways in which hate speech and acts are used in schools, and how parents and caregivers can help their students identify and stand against hate speech. 7 PM - 8:30 PM

(English) May 10, 2023, Registration Link    (English Flyer)
(Spanish) May 31, 2023, Registration Link   (Spanish Flyer)

 


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools