Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: January 17, 2018

elementary students at recess

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የዛሬውን የት/ቤት መዘጋት አስመልክቶ የተላለፈ መልእክት

January 17, 2018

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፣

ይህንን የምጽፈው በዛሬው እለት ጠዋት ት/ቤቶች ሁለት-ሠዓት ዘግይተው እንደሚከፈቱ መልእክት ካስተላለፍን በኋላ ዛሬ ት/ቤቶች ለተማሪዎች እንዲዘጉ ያደረጉትን ምክንያቶች ለመግለጽ ነው።  በተለምዶ፣ ጠዋት በ 5:00 a.m ላይ የት/ቤት መዘጋትን ለመወሰን እንችል ነበር። በአስቸኳይ የአየር ሁኔታ ምክንያት ት/ቤት ይዘጋ እንደሆነ ለማረጋገጥ በመከታተል ላይ እያለን ሁለት-ሠዓት ዘግይቶ እንደሚጀመር 5:00 a.m ላይ ማስታወቂያ ይነገራል። ማንኛውም ወቅታዊ ሁኔታ ለውጥ ሲኖር በ7:00 a.m ላይ ውሳኔ ይተላለፋል።  ዛሬ ይህንን ያላደረግንበት ምክንያት ሁሉም የአየር ትንበያ ጣቢያዎች ጥቂት የበረዶ ክምችት ከወረደ በኋላ ቀደም ብሎ እንደሚያባራ/እንደሚያቆም እየተነገረ ስለቆየ ነበር። በክልሉ ያሉ አብዛኛዎቹ የትምህርት ዲስትሪክቶች MCPSን ጨምሮ የሁለት-ሠዓት መዘግየት እንደሚኖር ማስታወቂያ ተናግረዋል።

ነገር ግን፣ አንፃራዊ ከሆነ መጠነኛ የበረዶ ሁኔታ ባሻገር የሁለት-ሠዓት መዘግየት ማስታወቂያ ከተነገረ በኋላ፣ በአብዛኛው የካውንቲው አካባቢዎች የመንገዶች ሁኔታ ለት/ቤት ማጓጓዣ አስተማማኝ/ደህና አልነበረም።  በርካታ የአቅራቢያ/ጎረቤት አካባቢዎችም ተመሣሣይ ሁኔታ አጋጥሟቸዋል።  የወረደው በረዶ መጠን አነስተኛ ቢሆንም፣ የበረዶው እርጥበት ከአየሩ ቅዝቃዜ ጋር በመሆን/temperatures below freezing አደገኛ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።  አንዳንድ መንገዶች በደህና ሁኔታ ላይ ቢሆኑም፣ በሞንጎመሪ ካውንቲ በተለይ ከዋና መንገዶች ወጣ ያሉት አብዛኛዎቹ መንገዶች የት/ቤት አውቶቡሶች ለማስኬድ ዝግጁ አልሆኑም።

እኛ የምናጓጉዘው በየቀኑ እስከ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ተማሪዎችን ከ 1,300 የት/ቤት አውቶቡሶች በላይ ስለሆነ የተማሪዎቻችን ደህንነት ለእኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ትኩረታችን ነው።  በተጨማሪ፣ ራሳቸው መኪና የሚነዱ በርካታ ተማሪዎች ስላሉን ይህንንም በግምት ውስጥ ማስገባት አለብን።  ሁኔታዎችን እየተከታተልን ስናይ ተጨማሪ ጥርጊያና ጨው ማፍሰስ ቢደረግም፣ ግን የት/ቤት አውቶቡሶች ከመሰማራታቸው በፊት ለት/ቤት አውቶብሶች፣ መኪና ለሚነዱ ተማሪዎች፣ እና በእግራቸው ወደ ት/ቤቶች እና ወደ አውቶቡስ ማቆሚያ ለሚራመዱ ተማሪዎች የመንገዶቹ ሁኔታ የሚሻሻልበት ሁኔታ አልታየም።  በዚህ ምክንያት ለተማሪዎች ደህንነት ሲባል ት/ቤቶች ተዘግተው እንዲውሉ ከባድ ውሳኔ ወሰንን።

ስለ ት/ቤት መዘጋት በተቻለ መጠን ቀደም ተብሎ መነገር እንዳለበት እናውቃለን፣ እና በዛሬው እለት ይህንን ለማድረግ ባለመቻላችን አዝናለሁ።  ሁልጊዜም የትምህርት ጊዜን በጣም ውጤታማ ለማድረግ እና በማዘግየት እና ት/ቤቶችን በመዝጋት የሚባክነውን ጊዜ በጣም ለመቀነስ እንሞክራለን፣ ነገር ግን በተመሣሳይ ሁኔታ እነዚህን ውሳኔዎች ለቤተሰብ እና ለማህበረሰብ መጠነኛ የሆነ የጊዜ እጥረትም ቢሆን ማሳወቅ አለብን።

በእኛ በኩል በተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ የአየር ሁኔታ መልእክት ምክንያት ስለተፈጠረው ያልተመቸ ሁኔታ ይቅርታ እየጠየቅሁ የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ስንል የወሰነውን እርምጃ ስለምትረዱልንና/ስለምትገነዘቡልንም አመሰግናለሁ።

 

Sincerely,

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools