Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 18, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ጉዳዮ፦ በ Santa Fe, Texas ስለተፈጸመው አሠቃቂ ሁኔታ ከሱፐርኢንተንደንት ጃክ ስሚዝ (Jack Smith) የተላለፈ መልእክት፦

በዛሬው ቀን በ Santa Fe, Texas የተደረገው ለመናገር የሚከብድ አሰቃቂ ድርጊት ሁላችንንም አንቀጥቅጦናል። በጠቅላላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ፀሎትና ሃሳብ በሃዘን ላይ ካሉት የአደጋው ሠለባ ከሆኑት ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች ጋር ነው።

እንደዚህ ዓይነት በት/ቤት-ፐብሊክ ስኩል የንጹሃን ልጆችን ሕይወት የሚቀጥፍ ሁኔታ ዳግመኛ ሲያጋጥም ለማሰብና ለመገመት እጅግ የሚከብድ ነው። የት/ቤት ሕንጻዎች ለተማሪዎች-ሠላማዊ ሥርፍራና ሁሉም ተማሪዎች ሠላምና ደህንነት እንዲሰማቸውና ወደ ትምህርታቸው የሚያተኩሩበት ሠላማዊ ሥፍራ መሆን አለባቸው። በመላው አገሪቱ የትምህርት መዋቅር ሠላምና ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ትኩረት ቢሆንም ነገር ግን ብቻችንን ልናደርገው አንችልም። የት/ቤቶቻችንን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅና ዳግመኛ ሌላ አሠቃቂ ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል እንድንችል የፌደራል እና የስቴት ኃላፊዎች አሁን እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ወላጅ አባት፣ አያት እና የትምህርት ባለሟል እንደመሆኔ መጠን፣ ይህ ዓይነቱ አሠቃቂ ሁኔታ በሁሉም ማህበረሰብ ላይ ምን ዓይነት ስጋትና ጭንቀት ሊፈጥር እንደሚችል እረዳለሁ/አውቃለሁ። የተማሪዎቻችንን እና የሠራተኞቻችንን ሠላምና ደህንነት ጉዳይ እጅግ ትኩረት በመስጠት የምንቀጥል መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ። በተጨማሪም ልጆቻችን በሙሉ ሠላማዊ በሆነ አካባቢ ምንም ስጋት ሳይኖርባቸው ለመማር እንዲችሉ የሚቻለንን ሁሉ እርምጃ እንወስዳለን።

ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንደዚህ ዓይነቱን አሳዛኝ ሁኔታ ለመወያየት ከባድ መሆኑ ይገባኛል። በዚህ ዓይነት ውይይት ለማገዝ/ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ መገልገያዎችን/resources በድረገጽ ላይ ለጥፈናል፦  http://www.montgomeryschoolsmd.org/emergency/preparedness/index.aspx#other በተጨማሪ፣ እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ክስተትን ተከትሎ ከሚመጣ አስደንጋጭ ሁኔታና ስሜት ጋር እንዴት ሊበረታቱ እንደሚችሉ ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ለመርዳት ሰኞ ቀን የት/ቤት ካውንስለሮች በየት/ቤቱ ይገኛሉ።

ከአክብሮት ጋር፣
Jack R. Smith, Ph.D. ዶ/ር ጃክ ር. ስሚዝ
Superintendent of Schools የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ