Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 20, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ስለ ተቀጣሪው ሠራተኛ መታሰር ከትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጃክ አር. ስሚዝ/Superintendent Jack R. Smith የተላለፈ መልዕክት፦

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

እንደምታውቁት ስቲቨን ካትዝ/Steven Katz የተባለ በሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተተኪ መምህር በአነስተኛ እድሜ ካለች ልጅ ጋር ግብረሥጋ ግንኙነት በመድፈር እና ከክሎቨርሊ ኤለመንተሪ ት/ቤት (Cloverly Elementary School) ተማሪ ጋር ተገቢ ያልሆነ 4ኛ ደረጃ የግብረስጋ ንኪኪ ግንኙነት በማድረግ (charges of sexual abuse of a minor and fourth degree sexual offense stemming from inappropriate contact) በወንጀል ድርጊት ስለተከሰሰ ዓርብ ማርች 16 ታስሯል።

የተጠርጣሪው ዓይነት ባህሪይ ግንዱ ከአንድ ት/ቤት ቢሆንም፣ ይህንን ኢንፎርሜሽን ለማህበረሰቡ የማካፍልበት ምክንያት Mr. Katz ከ MCPS ጋር በተተኪ መምህርነት ተቀጣሪ በነበረበት ወቅት በተለያዩ ት/ቤቶች ስለሠራ ነው። የእነዚህ ት/ቤቶች ርእሰመምህራን በሣምንቱ ማለቂያ ላይ የግለሰቡን መታሠር ለማህበረሰቡ ከማሳወቃቸውም በላይ እንደየአስፈላጊነቱ ለተማሪዎችም የምክር አገልግሎት/ካውንስሊንግ እየተሰጠ ነው። Mr. Katz የሠራባቸው ት/ቤቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ብሩክ ግሮቭ (Brooke Grove)፣ በርኒንግ ትሪ (Burning Tree)፣ በርንት ሚልስ (Burnt Mills)፣ በርተንስቪል (Burtonsville)፣ ኦልኔይ (Olney)፣ ሰቨን ሎክስ (Seven Locks)፣ ሼርውድ (Sherwood) እና ዌይሳይድ (Wayside) ኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች/elementary schools፤ ዊሊያም ኤች. ፋርኩኻር (William H. Farquhar)፣ ሮበርት ፍሮስት (Robert Frost) እና ቶማስ ደብሊዩ ፓይለ (Thomas W. Pyle) ሚድል ስኩልስ/middle schools፣ እና ጆን ኤፍ. ኬኔዲ (John F. Kennedy)፣ ፔይንት ብራንስ (Paint Branc) እና ሼርውድ (Sherwood) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች/high schools ናቸው።

Mr. Katz በ MCPS በተተኪ መምህርነት የሠራው ከ ሜይ/May 2017 እስከ ማርች/March 12/2018 ሲሆን በት/ቤት ስርአቱ ተጠርጣሪነቱ በተነቃበት ጊዜ ከቦታው ተወግዷል።

የሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ መምሪያ እና የስቴት ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት ምርመራ በሚያደርጉበት ወቅት ሁሉ
ከ MCPS ሙሉ ትብብር ተደርጓል። ከእነዚህ ኤጄንሲዎች ጋር ያለንን የትብብር አሠራር እና የMCPS ፖሊሲዎችን እና ደንቦችን በመመርኮዝ፣ እየተካሄደ የነበረው ምርመራ እንዳይደናቀፍ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከመታሠሩ በፊት ከት/ቤቶቻችን ዝርዝር ሁኔታውን ለማህበረሰቡ በስፋት ለመግለጽ አልተቻለም።

እንደዚህ ዓይነት ወንጀል የሚያበሳጭና ተቀባይነት የሌለው ነው። በእንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች የ MCPS ፖሊሲ የተጣሰ እና ተጻራሪ ከመሆናቸውም በላይ የትምህርት ቤት ሥርዓትን አይወክሉም። በዲስትሪክታችን የእያንዳንዱ ተማሪ ሰላምና ደህንነት ዋነኛው ቅድሚያ ትኩረታችን እና በቀላል የማንወስደው ኃላፊነታችን ነው። ት/ቤቶቻችን ሰላማዊ የመማሪያ ስፍራ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እየሠራን ቆይተናል ወደፊትም ይህንኑ በማጠናከር እንቀጥላለን።

ምናልባት እርስዎ ወይም የእርስዎ ልጅ ለምርመራ ክትትሉ የሚጠቅም መረጃ/ኢንፎርሜሽን ካላችሁ በሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ መምሪያ ልዩ ጥቃት የደረሰባቸው ምርመራ ክፍል/Special Victims Investigations Division of the Montgomery County Police Department በስልክ ቁጥር፦ 240-773-5400 ደውላችሁ እንድታነጋግሩ እጠይቃለሁ።

ከአክብሮት ጋር
Jack R. Smith Ph.D. ጃክ አር. ስሚዝ ዶ/ር
Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ