አምስት መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS Things to Know

ማክስኞ፣ ሜይ 25

narcan

ሜይ 31 የምርቃት ስነ ስርዓት ይጀመራል

በመክፈቻ ስነ ስርዓቶቹ ላይ ከዕረቡ፣ ሜይ 31፣ እና ሀሙስ፣ ጁን 15 መካከል ወደ 12,000 የሚጠጉ የ MCPS ተማሪዎች ዲፕሎማቸውን መቀበል ይጀምራሉ። የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች በተናጠል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣ በዋሽንግተን ዲሲ DAR ኮንስቲትዩሽን ሆል፣ እና ማውንት ሴንት ሜሪ ዩንቨርስቲ ካምፓስ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲ ኦቭ ሜሪላንድ ባልቲሞር ካውንቲ ይካሄዳሉ።

የዚህ አመት ዋና ዋና ንግግር አድራጊዎች የሚያካትቱትም የቶኒ (Tony) ሽልማት አሸናፊ ተዋናይ ማይልስ ፍሮስት (Myles Frost)፣ ከ Maryland Lt Gov አሩና ሚለር (Aruna Miller)፣ ባል-እና-ሚስት የሆኑት ጋዜጠኞች ፒተር ቤከር (Peter Baker) ከ The New York Times እና ሱሳን ግላሰር (Susan Glasser) ከ The New Yorker፣ የቀድሞ የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እና የ NBA ተጫዋች ዋልት ዊሊያምስ (Walt Williams)፣ ደራሲ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ጆርጅ ፔልካኖስ (George Pelecanos)፣ እና ሌሎችም።

የምረቃ ቀናት፣ ጊዜያት፣ እና ቦታዎች ሙሉ ዝርዝር
ይበልጥ ያንብቡ

audit

የትምህርት ቦርድ የስነምግባር ፓነልን ስራ መደብ/ቦታ ለመሙላት አመልካቾችን ይፈልጋል

የMontgomery County የትምህርት ቦርድ ለባለ ኣምስት ኣባል የEthics Panel (የስነምግባር ጓድ) ኣንድ ክፍት ቦታ ለመሙላት ይፈልጋል። ክፍት የስራ መደቦቹ ከጁላይ 1, 2023 ጀምሮ ለሶስት አመት የስራ ዘመን ነው።  ኣባላት የሚያገለግሉት ያለምንም ማካካሻ ነው።

በቦርድ ፖሊሲ "Board Policy, BBB" ላይ እንደተገለጸው፣  ከስነምግባር፣ፓነሉ ኃላፊነቶች መካከል (1) የፋይናንስ መግለጫ ቅጾችን ማጽደቅ፤ (2) የትምህርት ቦርድን የስነ-ምግባር ፖሊሲ መተርጎም እና ስለ አተገባበሩ ምክርና አስተያየት መስጠት፣ እና (3) ጥሰትን በሚመለከት በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ችሎት ማካሄድን ያጠቃልላል።

አመልካቾች ማመልከቻቸውን እንዲደግፍ የፍላጎት መግለጫ ደብዳቤን ከስራ ልምድ ማስረጃ ወይም ሌላ ሰነዶች ጋር አብሮ በማድረግ እስከ ከሰአት 5 p.m. ድረስ አርብ፣ ጁን 9፣ 2023 ማስገባት አለባቸው።

ይበልጥ ያንብቡ

የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች

ተማሪዎች 43ተኛ የወጣት አሜሪካዊ ቤት (Young American Home) አጠናቀቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች የግንባታ ንግድ ፋውንዴሽን በቅርቡ 43ተኛ የወጣት አሜሪካዊ ቤትን (Young American Home) በሲልቨር ስፕሪንግ (Silver Spring) ገንብተው አጠናቀዋል። ቤቱ የተነደፈው እና የተገነባው ከ 300 በላይ በሆኑ ተማሪዎች፣ ሁሉንም 26 የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወክለው ነው። ሜይ 23 ላይ የመሠረት ድንጋይ አከባበር እና የመክፈቻ መድረክ (open house) ተካሄደ። የቪድዮ ሊንክ

audit

ኖርዝዉድ (Northwood) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ RAMP Designation (ስያሜ) ወሰደ፣ በ MCPS ውስጥ የመጀመሪያው ነው

ኖርዝዉድ (Northwood) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በቅርቡ እውቅና ያለውን ASCA ሞዴል ፕሮግራም (RAMP) ስያሜ አገኘ። የ RAMP ስያሜ እውቅና የሚሰጠው በመረጃ-የተደገፈ የት/ቤት ካውንስሊንግ/ማማከር ፕሮግራምን ለማቅረብ በቁርጠኝነት ለሚሰሩ ት/ቤቶች ነው፣ ይሄም አክብሮ የሚሰራው የ ASCA ብሔራዊ ሞዴልን ነው፦ የት/ቤት ካውንስሊንግ/ማማከር ፕሮግራም መዋቅር።

audit

175 ተማሪዎች በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በተዋሀደ የመስክ ቀን (Unified Field Day) ላይ ተሳተፉ

ዊተን (Wheaton) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያውን በተዋሀደ የመስክ ቀን (Unified Field Day)  ሜይ 23 ላይ ከአልበርት አንስታይን፣ ጆን ኤፍ. ኬኔዲ እና ስፕሪንግብሩክ (Springbrook) ት/ቤቶች ጋር በመሆን አዘጋጅቷል። በራስን መቻል (LFI) ውስጥ እና ት/ቤት መሰረት ያደረጉ የማህበረሰብ (SCB) ፕሮግራሞች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ልዩ ልዩ/ብዝኃነት ያላቸው ለሆኑ ብቃቶቻቸው በተዘጋጁ ዝግጅቶች ውስጥ ተወዳድረዋል። የጊልበርት ጨዋታዎች (Gilbert Games) የተዘጋጁት የነበረው ለቀድሞዋ የ LFI ዊተን (Wheaton) ተማሪ ለነበረችው፣ ህይወቷ ላለፈው ሳራ ጊልበርት (Sarah Gilbert) ክብር ነው።

audit

MCPS የወደፊት መምህራንን አክብሯል

MCPS የወደፊት መምህራንን ክብረ በዓል ለ 24 የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ሜይ 24 ላይ አዘጋጅቷል። ይሄ የሰው ሀብቶች እና እድገት ቢሮ “የራሳችሁን አሳድጉ” / “Grow Your Own” ስልትን የማስተማር ስራ ዘርፍ ውስጥ በዲስትሪክታቸው ሊገቡ የሚችሉ የ MCPS ተማሪዎችን ለመሳብ፣ ለመመልመል እና ለማነሳሳት ሲያዘጋጅ አሁን ሁለተኛ አመቱ ነው።

ዝግጅቱ እውቅና የሰጠው የላቀ የትምህርት አሰራር እና ኮሌጅ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ MCPS ለመመለስ ለቆረጡ ተማሪዎች ነው። በተጨማሪም፣ እያንዳንዱ እነዚህ ተማሪዎች ለኮሌጅ ትምህርታቸው የ $5,000 ስኮላርሺፒ ይወስዳሉ።

የ MCPS የቪድዮ ክስተቶች እና MCPS በዜና ላይ

NBC 4፦ አዲስ MCPS  ክፍል በእስያ አሜሪካዊ ትምህርት መስኮች

የምግብ ዋስትና እጦት ቀን በጌይተርስበርግ (Gaithersburg) መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ፕራይድ ታውን አዳራሽ / Pride Town Hall 2023

የ MCPS መምህራን በጌይተርስበርግ (Gaithersburg) የመፅሀፍ አውደ ርዕይ ላይ ተካተው ነበር

BLK GRLZ THRVN ፌስቲቫል



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools