Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 4, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፣

የትምህርት ዓመቱ አልቆ እየተዘጋ ቢሆንም፣ የትምህርት ቤቶቻችንን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እኛ ሥራችንን እንቀጥላለን። በዚህ ስፕሪንግ፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የት/ቤት ሠላምና ደህንነትን በሚመለከት ሪፖርት አስተላልፏል። የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የትምህርት ቤት ሥርዓት የሚተገብራቸውን በርካታ አይነት የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ዝርዝር በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል። የዚህ ሪፖርት አካል የሆነ፣ ደህንነትን ለማስጠበቅ በምናደርገው ጥረት ወደ ቀጣዩ ደረጃ የሚያሸጋግረን የተግባር እቅድ ጨምረናል። ስለ ተግባር እቅዳችን የደረሰንበት ደረጃ ወቅታዊ መግለጫ እዚህ ይገኛል

በተጨማሪም፣ ስለ ት/ቤት ሠላምና ደህንነት ከተማሪዎች የሰማናቸውን በጥቂቱ ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ። ባለፈው ወር የት/ቤቶችን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ከተማሪዎቻችን አስተያየት ለመሰብሰብ ከአንዳንድ ተማሪዎች ናሙና  ጥናት አድርገናል። ከ 1,100 በላይ ምላሽ አግኝተናል። የተነሱት ቁልፍ የሆኑ ፍሬሃሳቦች ስረመሠረት/infrastructure ማሻሻል/ማጠናከር፣ የፀጥታ ጥበቃ ሠራተኞችን ቁጥር መጨመር፣ እና የአእምሮ ጤንነት አገልግሎቶችን ማስፋፋትና መርዳት ናቸው። በዚህ አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ላይ የሰጡትን ማስተዋል የተሞላበት ምላሽ በሙሉ አደንቃለሁ። የእነርሱን አስተያየት/ኢንፎግራፊክ ከዚህ ለማየት ይቻላል፦infographic (link to come)

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሰመር ወራትም የት/ቤት ሠላምና ደህንነትን በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን በድረገጽ/website ላይ ያስተላልፋል

የት/ቤቶቻችንን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ብቻችንን ልናደርገው አንችልም። ስኬታማ እንድንሆን የእርስዎ ድጋፍ እና አስተዋጽኦ ወሳኝ ነው። የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ እስካሁን ስላደረጉትና ወደፊትም ለሚያደርጉት ድጋፍና አስተዋጽኦ ሁሉ አመሰግናለሁ።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D. ዶር. ጃክ አር. ስሚት
Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ