Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: June 15, 2017

Other Languages: English | Spanish | French | Korean | Chinese | Vietnamese

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

የትምህርት ኣመቱ መጨረሻ የበኣል፣ የማንሰላሰል፣ እና ስለወደፊቱ ፕላን የማድረጊያ ጊዜ ነው። የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ስለሆንኩበት የመጀማርያ ኣመት ሳሰላስል፣ እጅጉን ብዙ የምናከብረው እና እንዳውም ይበልጥኑ ለ2017-2018 የትምህርት ኣመት ተስፋ በምናደርገው እደሰታለሁ።

የፈፀምናችው More than 10,000 Graduates at MCPS

የ2016-2017 የትምህርት ኣመት ኣዳዲስ መገልገያዎችና ት/ቤቶችን ኣምጥቶልናል። የMontgomery County ስራ ኣስፈፃሚ Isiah Leggett/ኣዛያ ለጌት፣ የMontgomery County ምክር ቤት ፕረዚደንት Roger Berliner/ሮጀር በርሊነር፣ የትምህርት ሊቅመንበር Craig Rice/ክሬግ ራይስ፣ እና የካውንቲ ምክር ቤት በጠቅላላ፣ እና የትምህርት ቦርድ ምስጋና ይግባቸውና፣ Montgomery County Public Schools የትምህርት ኣመቱን የጀመሩት ከትርጉም ካዘለ የስራ ማስኬጃ ጭማሪ ጋር ነው። እነዚህ ኢላማ ያላቸው ገንዘቦች የመማርያ ክፍል ተማሪዎችን ቁጥር የመቀነስ ሂደትን ለመጀመር ኣግዘውናል እናም የግኝትን ክፍተት ለመዝጋትና ለተማሪዎቻችን እድሎችን ለመጨመር ጥረቶቻችንን እንድናራምድ መገልገያዎችን ሰጥተውናል። በተጨማሪ ኣዲሱን ኣመት ከኣዲስ ት/ቤት ጋር ጀመርን—Hallie Wells Middle School ካርስበርግ ውስጥ—ታይቶ የማይታወቅ የተማሪ ምዝገባ እድገት ለመቋቋም፣ እንዲሁም ተማሪዎች ወደ ት/ቤት በሰላም መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ኣዲሱ የኣውቶቡስ የካሜራ ደህንነት ፕሮግራም

በ204 ት/ቤቶቻችን ውስጥ፣ ተማሪዎች ሳይንስን፣ እንግሊዘኛን፣ ቋንቋዎችን፣ ኪነጥበባትን፣ ሂሳብን፣ ዲጂታል ዜግነትን እና ሌላም ሌላም ዳስሰዋል። የዚህ ለትምህርት የተገባ ግዴታ ውጤቶች፡- 10,600 ተማሪዎች ከMCPS የተመረቁ።  እነዚህ ተመራቂዎች ለስኮላርሺፕ $350 ሚልዮን ኣግኝተዋል፤ ከነዚህ ውስጥ 44ቱ የNational Merit Scholar ተሸላሚዎች ናቸው (ሌላ ተጨማሪ የኣሸናፊዎች ዙር በጁላይ ወር ይገለፃል)፤ 10ቹ የPosse Foundation ስኮላርሺፕ ሙሉ-ትዊሽን ኣሸንፈዋል፤ እናም ሶስቱ የRegeneron Science Talent Search ለመጨረሻ ዙር ተሰይመዋል፣ ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ። MCPS athletic teams won a total of 212 championships

ከመማርያ ክፍል ውጭ፣ የMCPS የኣትሌቲክስ ቡድኖች፣ 18 የስቴት ሻምፒዮናዎች፣ 112 የክፍል ወይም የዲስትሪክት ሻምፒዮናዎች፣ እና 44 የከፊል/sectional ሻምፒዮናዎችን የሚያካትት 212 ሻምፒዮናዎች ኣሸንፈዋል። በተጨማሪ፣ 150 የMCPS ተማሪ-ኣትሊቶች ግላዊ የስቴት ሻምፒዮና ኣሸንፈዋል።

ት/ቤቶቻችንና መምህራኖቻችንም የኣካባቢና ሃገራዊ እውቅና ኣግኝተዋል። በU.S. News Best High Schools Rankings/ከሁሉም በላይ ባለማእረግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ኣምስት ት/ቤቶች የወርቅ ሜዳይ ተቀብለዋል እናም ኣራት ት/ቤቶች የብር ሜዳዮች ተቀብለዋል፤ Farmland እና Ronald McNair የኤሌሜንታሪ ት/ቤቶች Maryland Blue Ribbon ት/ቤቶች ተብለው ተሰይመዋል፤ William Tyler Page Elementary School እና John Poole Middle School የ2017 U.S. Green Ribbon Schools Award ተሸላሚ ተብለው ተመርጠዋል፤ እናም ሁሉም 25 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ2017 America’s Most Challenging High Schools/የኣሜሪካ እጅጉን ፈታኝ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዝርዝር ውስጥ በThe Washington Post በሚታተመው ማእረግ ተሰጥቷቸዋል። ግላዊ መምህራንም ተሸልመዋል። The Washington PostRockville High Schoolን Sean Pang/ሻን ፓንግ የኣመቱ መምህር እና የRock Creek Forest Elementary Schoolን Jennifer Lowndes/ጄኒፈር ሎውንዴስን የመጨረሻ ዙር የኣመቱ ርእሰመምህር ብሎ መርጧቸዋል።

ለእኩልነትና ለኣይነተ-ብዙህነት የገባነው የረዥም ጊዜ ግዴታ በተጨማሪ በኣመቱ ውስጥ ትርጉም ያዘለ ሚና ተጫውቷል። ለፍትህ፣ ባህላዊ ብቃት እና ፀረ-ኣድልዎነት የገባውን ግዴታ ለማጠናከር የትምህርት ቦርድ መመርያ ACAን ከለሰ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጥላቻን ለመታገል እና የኣይነተ-ብዙህነትን፣ የኣድልዎን፣ እና ያለ ማስረጃ ፍርድ የመስጠትን ጉዳዮች ለመዳሰስ ኪነጥበብን፣ ቅኔን፣ ሙዚቃን እና ጭፈራን የተጠቀሙበትን የስርኣት-ኣቀፍ ውድድር MCPS ኣስተናገደ። በርካታ ት/ቤቶችም የኣይነተ-ብዙህነትን እና የመቻቻል ጉዳዮችን በStudy Circles/የጥናት ክቦች እና በሌላ በት/ቤት በተመሰረተ ውይይት ኣማካይነት ፊት ለፊት ገጠሟቸው።

የሰመሩ ስልት

ሰመር ለተወሰን ሰዎች እረፍት፣ ካምፖችና የባህር ዳር መስለው ሲታዩአቸው፣ ለተማሪ ብልፅና ተጨማሪ እድሎች ማለትም ይሆናል። በዚህ ሰመር፣ የBuilding Educated Leaders for Life/የተማሩ መሪዎችን ለህይወት መገንባት (BELL) ፕሮግራምን ሁለተኛውን ኣመት እንጀምራለን። ይህ ፕሮግራም፣ ከMontgomery County ምክር ቤት እና ከNorman R. Rales and Ruth Rales Foundation ጋር የጋራ የሆነ፣ በTitle I ት/ቤቶች ኣካዴሚያዊ ፍላጎት ለሚያሳዩ ራይዚንግ የ3ኛ 4ኛ፣ እና የ5ኛ ተማሪዎች የሰመር ኣካዴሚና ብልፅግና ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም የኛን የረጅም ጊዜ የELO STEP እና የELO SAIL የሰመር ትምህርት ፕሮግራሞችን ያሟላል። ተማሪዎችን ከቢዝነሶች መዋቅሮች፣ ቴክኒካዊ ክሂሎቶች፣ የቴክኖሎጂ ሚና፣ እና ከደንበኛ ኣገልግሎት ኣስፈላጊነት ጋር የሚያስተዋውቃቸው የሶስት ሳምንት የስራ መከታተያ ተሞክሮ የሚሰጣቸው ከWorkforce Montgomery ጋር በሽርክና በተፈጠረው ፕሮግራም በSummer R.I.S.E. የምረቃ ኣመትም በተጨማሪ ተደስተናል። በመጨረሻ፣ ነገር ግን ከሁሉም ባላነሰ፣ ተከታታይ የCareer Technology Education/የስራ ቴክኖሎጂ ትምህርት (CTE) በሰመር ካምፖች ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እንጀምራለን።

በኣድማስ ላይ

ሰመሩ እየጠለቀ ሲሄድና ቤተሰቦች ወደ ት/ቤት ለመመለስ ሲዘጋጁ፣ ኣስተማሪዎቻችን፣ ርእሰመምህራኖቻችንና ሰራተኞቻችን በደህንነት ላይ ከታደሰ ትኩረት ጋር ተማሪዎቻችንን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ይዘጋጃሉ፤ ኣዳዲስ ገንዘብና መገልገያዎች፤ እናም ጠንካራ ግዴታ ለሁሉም ተማሪዎች ፍትህና ኣካዴሚያዊ ልቀት።

ሰላማዊና ኣስተናጋጅ የመማርያ ኣካባቢ ለተማሪዎቻችን ማቅረብ በየእለቱ የመጀመርያው ተቀዳሚያችን ይሆናል። የደህንነት ሂደቶችንና ፕሮቶኮሎች በሁሉም ት/ቤቶቻችን በመገምገም ስራችን ይቀጥላል። ከዚህ ቀደም እንዳጋራሁት፣ MCPS በት/ቤቶቻችን ስርኣት ባለው የደህንነት ድህረእይታ ላይ ተጠምዷል። የድህረእይታው ቦታው-ላይ የግምገማ ክፍሎች ለሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተፈፅመዋል እናም የመካከለኛና የኤሌሜንታሪ ት/ቤቶችን ድህረእይታ በዚህ ሰመር እንጀምራለን። እንዳለቀ፣ የድህረእይታችንን ማጠቃለያ ኣቅርበን የሚቀጥሉ እርምጃዎቻችንን ከት/ቤት ማህበረሰቦች ጋር እንጋራለን።

ማሸማቀቅንና ወከባን፣ የልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነትን ለመታገል በረጅም ጊዜ ጥረቶቻችን ነቅተን እንጠብቃለን። በኣዲሱ የእሽታ ፅ/ቤት/compliance office በሚሰጠው መመርያ መሰረት፣ የልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነትን ስለመከላከል፣ ማወቅና ዘገባ መገለያዎችና ስልጠና ለሰራተኞቻችን እንሰጣለን፤የፆታ ወከባን መከላከልና መቋቋም፣ እና ት/ቤቶቻችን ከማሸማቀቅ፣ ወከባ እና ማስፈራራት ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ።

MCPS ኣንድ ኣዲስ ት/ቤት—Silver Creek Middle School በቤተስዳ—ይከፍታል እናም የሁሉን ተማሪዎችን ፍላጎቶች ለማገልገል ወሳኝ መገልገያዎችን የትምህርት ቦርድ $2.52 ቢልዮን የስራ ማስኬጃ በጀት ተቀብሏል፣ ይህም ከተማሪ እድገት ጋር ለመራመድ፣ በክፍል ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ ለመቀጠል፣ እና የግኝትንና የእድልን ክፍተት ለመዝጋት ጥረቶቻችንን ለማጣደፍ የሚያግዘን ነው።

በመማርያ ክፍል ውስጥ፣ የተማሪ ግኝት ከፍተኛ ደረጃዎችን እንከባከባለን እናም ሁሉም ተማሪዎች መማራቸውን ለማረጋጋጥ ትርጉም ያላቸው እርምጃዎች መውሰድ እንቀጥላለን። ይህ የት/ቤቶችና ግላዊ ተማሪዎች ውጤቶችን ለማሻሻል ግስጋሴዎችን ለመከታተል የበለፀጉ ስልቶች እና መሳርያዎችን ያካትታል። በሁለተኛ ት/ቤት ደረጃ፣ ስድስት ኣዳዲስ Equal Opportunity Schools/ባለ እኩል እድል ት/ቤቶች ከ1,000 በላይ በዘልምድ ኣነስተኛ ውክልና ያላቸው ተማሪዎችን ለጠንካራ Advanced Placement/ኣስቀድሞ ምደባ እና International Baccalaureate/ኣለም-ኣቀፍ ባካሎርያ ኮርሶች ያጋልጣሉ። በኤሌሜንታሪ ት/ቤት ደረጃ፣ ኣለም-ኣቀፍ ማጠርያዎችን ሁሉንም የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲያካትቱ በማስፋፋት ለCenters for Enriched Studies/የበለፀጉ ጥናቶች ማእከሎች ወደር የሌለው ኣካዴሚያዊ እምቅ ሃይል ያላቸውን ተማሪዎች ለመለየት እንቀጥላለን። በተጨማሪ፣ ሁለት ኣዳዲስ የኣካባቢ በለሁለት ኣቅጣጫ ኢመርሽን ፕሮግራሞች በBrown Station እና በWashington Grove ኤሌሜንታሪ ት/ቤቶች ይከፈታሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች፣ ከስማንት (ሰባት ኢመርሽን እና ኣንድ ባለሁለት ኣቅጣጫ ኢመርሽን) በተጨማሪ ሌላ የኤሌሜንታሪ ኢመርሽን ፕሮግራሞች በካውንቲው ከዳር እስከ ዳር፣ ወጣት ተማሪዎችን ወደ biliteracy and bilingualism/ባለሁለት መሰረተእምንርትና ባልሁለት ቋንቋነት መንገድ ያስቀምጧቸዋል።

MCPS በተጨማሪ በስራ ጎዳናዎችና ዝግጁነት ላይ ያተኩራል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ Navianceን ከፈትን፣ ይህም ለሁሉም የኣሁኑ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆኖ በሚመጡት ኣመቶች የሚስፋፋ ለኮሌጅና ለስራ ዝግጁነት ኣዲስ የሁለተኛ ደረጃ ትቤት መስመር ላይ ፕላን ማድረጊያ ነው። የCTE ፕሮግራሞችን መዳረሻ እና ኣፈፃፀምን እንጨምራለን እናም ተጨማሪ ተማሪዎች የኢንዱስትሪ የምስክር ወረቀት የሚኖራቸውና ሲመረቁ የስራ ኣለም ለመግባት ዝግጁ የሚሆኑ ተጨማሪ ተማሪዎችን የሚያፈራ የስራ ላይ ትምህርት ፕሮግራሞችን ትግባሬ እንጀምራለን።

ከተማሪ እድገት በተጫማሪ፣ በሰራተኛ እድገትም እናተኩራለን። MCPS በውጤታማ ልምዶችና የእውቀት ይዘት ለመምህራን ትኩረት ያለው ስልጠና እንሰጣለን። በተጨማሪ ለመምህራንና ረዳት-መምህራን የፍትህ ጉዳዮችን፣ ባህላዊ ብቃት፣ ግልፅ ኣድልዎ እና መልሶ ማስተካከልን ጨምሮ፣ ለመቋቋም ተፈላጊ ሙያዊ ስልጠና እንተገብራለን።

በ2016-2017 የትምህርት ኣመት በሙሉ ለተማሪዎቻችንና ለት/ቤቶቻችን ላደረጋችሁት ድጋፍ ኣመሰግናለሁ። ታላቅ ሰመር ያድርግላችሁ!

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
Jack R. Smith
Superintendent of Schools