ከቅርብ ወራት ወዲህ የጥላቻ፣ አድሏዊነት፣ ዘረኝነት፣ ፀረ-ሴማዊነት እና LGBTQ+ ጭፍን ጥላቻ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ዛሬ፣ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 27፣ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት በሰጡት መግለጫ ላይ ስለዚህ ጉዳይ እና በካውንቲው ልጆች እና ትምህርት ቤቶች ላይ ስለሚያስከትለው አሉታዊ ተጽእኖ ይገልጻሉ። ሙሉውን ንግግር እዚህ ያንብቡ
ማክሰኞ፣ ሜይ 2 እና ረቡዕ ሜይ 17፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ዊል ጃዋንዶን፣ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክኒት እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጀርሜን ዊሊያምስ የትምህርት ወጪዎችን በሚመለከት የሚከናወን የማህበረሰብ ውይይት ላይ ይገኛሉ። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ለሞንትጎመሪ ኮሌጅ የታቀዱ የስራ ማስኬጃ በጀቶችን ጨምሮ ስለ ካውንቲው ስራ አስፈፃሚ $6.8 ቢሊዮን ዶላር የበጀት እቅድ መሪዎቹ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።
ሜይ 2 ወይም ሜይ 17 በአካል ተገኝተው መሳተፍ ይችላሉ። ይመዝገቡ/RSVP
በአካል የሚካሄድ ውይይት ዝርዝር፡
ሜይ 2, 6:30-8:30 p.m.
Wheaton High School Cafeteria ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካፌቴሪያ
12401 Dalewood Drive, Silver Spring, MD 20906
የቨርቹወል ውይይት መረጃ
Zoom webinar: https://mcpstv-org.zoom.us/j/81629122344።
ስልክ፡ 301-715-8592
Webinar ID: 816 2912 2344
ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 29፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት በጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ ኮ/ል ዛዶክ መግሩደር/Col. Zadok Magruder ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 9 a.m.– እስከ እኩለ ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ተሳታፊዎች ለአዋቂዎች እና ለተማሪዎች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ከተዘጋጁት ከሁለት ደርዘን በላይ ትምህርት ሰጪ ክፍለ ጊዜዎች እና እንቅስቃሴዎች የፈለጉትን መምረጥ ይችላሉ። ርእሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አድራሻ፦ Magruder High School is located at 5939 Muncaster Mill Road in Rockville
ይመዝገቡ/RSVP
ለመጀመሪያው የተማሪዎች የአየር ንብረት አክሽን ካውንስል ማመልከቻ ለማቅረብ ክፍት ነው።
በአሁኑ ጊዜ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 8ኛ እስከ11ኛ ክፍል የምትማር(ሪ) ተማሪ ከሆንክ(ሽ) በለዘላቂነት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከካከል ፍላጎት አለህ(ሽ)? አሁን ለተማሪ የአየር ንብረት አክሽን ካውንስል አባልነት ለማመልከት ክፍት ነው። አዲስ የተቋቋመው የተማሪዎች ካውንስል የሚከተሉትን ተግባሮች ያከናውናል፦
ቅዳሜ ኤፕሪል 29፣ የመጀመሪያው የልዩ ትምህርት የወላጅ ማህበረሰብ ሪሶርስ አውደርዕይ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Gaithersburg High School) ይካሄዳል። የመገልገያ/ሪሶርስ አውደ ርዕዩ ከጠዋቱ 9፡00 –noon እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይካሄዳል፣ ንግግር የሚያደርግ ተጋባዥ እንግዳ፣ ለማህበረሰብ ጠቃሚ ግብዓቶች እና አቅራቢዎች፣ እዲሁም አዝናኝ የልጆች እንቅስቃሴዎች፣ moon bounce፣ የእጅ ጥበብ እና ፊት የመቀባት ትርኢቶችን ያካትታል።
ለመሣተፍ አስቀድሞ መመዝገብ የግዴታ ባይሆንም ግን ይመረጣል። ይመዝገቡ/Register.
የጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኘው በጌትስበርግ አካባቢ ነው//Gaithersburg High School is located at 101 Education Blvd. in Gaithersburg።
የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች
የክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ የዓመቱ ምርጥ የ MCPS መምህር በመሆን ተሰይማለች
ሻነን ማኬንዚ/Shannon McKenzie፣ በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የህፃናት እድገት መምህርት፣ 2023–2024 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህርት ተብላ በዓመታዊው የህፃናት ሻምፒዮንስ ሽልማት ክብረ በአል ላይ ተመርጣለች። አሁን ለሜሪላንድ የዓመቱ ምርጥ መምህርነት ለመወዳደር ትቀጥላለች።
ይበልጥ ያንብቡ
የተሸላሚዎችን ዝርዝር ይመልከቱ
13 ተማሪዎች ብሔራዊ የተደናቂነት ሽልማት በኮርፖሬሽኖች ስፖንሰር የሚደረግ ስኮላርሺፕ አሸንፈዋል
ከአምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 13 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በብሔራዊ ሜሪት ስኮላርሺፕ ኮርፖሬሽን የገንዘብ ድጋፍ ከብሔራዊ ሜሪት ኮርፖሬት ስኮላርሺፕ ተሰጥቷቸዋል። በመላ አገሪቱ ወደ 840 የሚጠጉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች 107 ኮርፖሬሽኖች፣ የኩባንያ ፋውንዴሽኖች እና በሌሎች የንግድ ድርጅቶች የሚደገፍ ናሽናል ሜሪት ስኮላርሺፕ እንዲያገኙ ተመርጠዋል።
ጀምስ ኦልሪች/James Allrich፣ የአርጋይል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰመምህር፣ MCPS የዋሽንግተን ፖስት የአመቱ ምርጥ ርዕሰ መምህር የመጨረሻ እጩ ናቸው። በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ መሳሪያ መምህር ቻርለስ ኦሪፊቺ/Charles Orifici የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የዋሽንግተን ፖስት የአመቱ ምርጥ መምህር የመጨረሻ እጩ ነው።
ይበልጥ ያንብቡ
MCPS በሙዚቃ ትምህርት እውቅና ተሰጥቶታል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሙዚቃ ትምህርት ከ "National Association of Music Merchants Foundation" የ 2023 ምርጥ ማህበረሰብ በመሆን ተሰይሟል! በዝርዝሩ መሠረት ለአስተማሪዎች፣ ለአስተዳዳሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች እና የማህበረሰብ መሪዎች የላቀ ጥረት እና ለሙዚቃ ትምህርት ያላቸውን ድጋፍ እውቅና ተሰጥቷል።
ኤፕሪል 22 "Earth Day" በቲልደን መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት MCPS የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል በተደረገው የወጣቶች ጉባኤ ላይ 250 በላይ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ተናጋሪዎች ስለ አየር ንብረት ለውጥ ያስረዱ ሲሆን አውደ ጥናቶችም ተካሂደዋል። ከ MCPS የመጓጓዣ አገልግሎት የመጡ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችም በሠርቶ ማሳያነት ቀርበዋል።
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org