1. ዓመታዊ ሪፖርት፣ እና የተሻሻለው ስትራቴጂክ ዕቅድ አሁን ዝግጁ ነው።
2021–2022 የትምህርት አመት ለማህበረሰቡ የሚቀርብ አመታዊ ሪፖርት እና የተሻሻለው MCPS 2022-2025 ስትራቴጂካዊ እቅድ እነሆ ተዘጋጅቷል። ዓመታዊ ሪፖርቱ 2021–2022 የትምህርት አመት በቀላሉ ተደራሽ የሆነ ዲጂታል የመረጃ ማጠቃለያ እና የተማሪ እና የሰራተኞች መረጃ አጠቃቀም ቁልፍ ስርዓት እንዲሆን የተቀየሰ ነው። የሚያጠቃልለው፦
አመታዊ ሪፖርቱ እዚህ ይገኛል።ስትራቴጂክ እቅዱእዚህ ይገኛል።
2. ነጻ SAT የመሰናዶ ኮርስ መመዝገቢያ ቀነ ገደብ ተራዝሟል
MCPS ለተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቨርቹዋል የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜዎችን እንደየግላዊ ፍላጎታቸው አዘጋጅቶ ለማቅረብ FEV Tutor ጋር በመተባበር ስለሚሰራ ደስተኛ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከአሁን ጀምሮ እስከ ሜይ ድረስ ለነጻ የስድስት ሳምንት ኮርስ መመዝገብ ይችላሉ። ምዝገባው አርብ፣ ማርች 17 ይዘጋል ጥያቄ ካለዎት FEV Tutor mcps@fevtutor.com ወይም 855-763-2607 ማግኘት ይችላሉ።
ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚኖሩበት ጊዜ፦
3. ቀጣይ ስለ ፈንታኒየል የቤተሰብ ውይይት መድረክ/Fentanyl Family Forum ማርች 25 (Paint Branch High School) በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተዘጋጅቷል።
"Montgomery Goes Purple" ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር ስለ "Fantanyl" ሶስተኛውን የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ማርች 25 ከጠዋቱ 9 a.m.–እስከ እኩለ ቀን ድረስ (Paint Branch High School) በፓይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያስተናግዳል። ይህ መድረክ በተጨማሪ ስለ አደጋኛ እፅ ጥልቀት ያለው ግንዛቤ ማግኘትና የመማር እድሎች ላይ የሚያተኩር ከመሆኑም በላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ክፍለ-ጊዜዎችን መርጠው ለመሣተፍ እና እንዲሁም ስለ ናርካን ስልጠና፣ የዳንስ ልምምድ፣ የሪሶርሶች ሰንጠረዦች እና ሌሎችም ይገኙበታል። የውይይት መድረኩ ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች በየግል እና በጋራ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ክፍለ ጊዜዎች ይኖሩታል። መወያየት የሚገባቸው የናሙና አርእስቶች፡ከተማሪዎ(ዎች) ጋር ውይይት መጀመር፣ከወላጆች ጋር ውይይት መጀመር፣የአእምሮ ጤና እንክብካቤ፣ሪሶርሶችን ማግኘት እና፣ከጓደኞች ጋር ጤናማ የግንኙነት ድንበር መጠበቅ እና ሌሎችም ይካተታሉ።
አድራሻ፦ Paint Branch is located at 14121 Old Columbia Pike in Burtonsville.
ይመዝገቡ/RSVP
4. ለሕዝባዊ ትምህርት ሽልማት እጩዎችን ለማቅረብ የመጨረሻ ቀን ማርች 16 ነው።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 26ኛው አመታዊ የላቀ ህዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ሽልማቶች እጩዎችን ይፈልጋል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ህዝባዊ ትምህርት ላይ አርአያነት ያለው አስተዋጾ ላደረጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች እውቅና ለመስጠት እና አድናቆት ለማሳየት ሽልማቶቹ በቦርዱ የተደገፉ ናቸው። ለበለጠ መረጃ የቦርዱን የላቀ አገልግሎት ሽልማት ድረገጽ ይጎብኙ። የተሞሉ የእጩዎች ጥቆማ ቅጾች እስከ ሐሙስ፣ ማርች 16 ቀን እስከ 5 p.m መድረስ አለባቸው።
5. ለምርጥ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት
የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት ብሄራዊ የአትሌቲክስ ስልጠና በዚህ ወር እያከበረ ነው። ስለ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ጠቃሚ ስራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሀገር አቀፍ የአትሌቲክስ ስልጠና ወር በየአመቱ በማርች ወር ይካሄዳል። 2023 መፈክር «There’s an AT for That።"ዲፓርትመንቱ Twitter፥Instagram፥እና #ATsRAISE በመጠቀም የአትሌቲክስ አሰልጣኞችን ያነቃቃል።
የቼቪ ቼዝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Chevy Chase Elementary School) መምህርት አማንዳ ሀመርስላ/Amanda Hammersla የዘንድሮ "Rising Star of the Year" መምህር በመባል ተሰይማለች። በቼቪ ቼዝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሶስተኛ አመቷ፣ ሀመርስላ የተማሪዎቿን የመማር ፍላጎት በማቀጣጠል፣ የተዋጣላት፣ ፈጠራ የተሞላባት ብርቱ አስተማሪ ነች። ሣምንታዊ መጽሔት ላይ የበለጠ ያንብቡ።
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org