Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 31, 2020


mcps logo

English |  español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

እርስዎ እና የእርስዎ ቤተሰብ በሙሉ ሠላም እና ጤና መሆናችሁን ተስፋ አደርጋለሁ። የ 2019-2020 የትምህርት ዓመት በፍጥነት እየተገባደደ ይገኛል እና እሑድ፣ ጁን 7 በሚካሄደው ዩንቨርሳል የምረቃ ሥነ ሥርዓት፣ የ2020 ተመራቂዎችን ጨምሮ የተማሪዎቻችንን የሥራ ክንውን Jose Andres የተባሉ እውቅ የስነምግብ ባለሙያ፣ የግብረሠናይ እና የ World Central Kitchen መሥራች ክብረበዓሉን አስመልክተው በሚያደርጉት ንግግር ለማክበር እየተጠባበቅን እንገኛለን። የሁነቱ ቅንብር ከ NBC4 ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ከ 10,500 በላይ ለሚሆኑ ሲንየሮች የአክብሮትና የአድናቆት መግለጫ ይሰጣል። የምረቃ ሥነሥርዓቱ ከ 6 p.m. ጀምሮ በሚከተሉት ቻነሎች ይተላለፋል፦ Cozi TV (broadcast over-the-air on channel 4.2, Verizon Fios channel 460, and Xfinity channel 208) and on MCPS TV (Comcast channel 34, Verizon channel 36 and RCN channel 89)። ከዚህ በተጨማሪ በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ለተማሪዎቻችን የሚያጓጓ እና አስደሳች የሆነ ይህንን ሁነት ከፍታችሁ እንደምትከታተሉ ተስፋ እናደርጋለን። በተጨማሪ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን በሙሉ እያንዳንዳቸው በግል ከ ጁን 8 - 12 ባለው ጊዜ ውስጥ ከትምህርት ቤት ማህበረሰቦቻቸው ጋር ያከብራሉ።

ከዚህ በታች በርካታ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ይገኛሉ፥ ይኼውም ስለዲስትሪክቱ የማገገሚያ እቅድ-recovery plan፣ ስለ ሠመር ትምህርት፣ እና ስለዲስትሪክት አቀፍ ክልላዊ ጥናት ዝርዝር ይገኝበታል።

በየጊዜው የሚያደርጉትን ድጋፍ እና እርዳታ እናደንቃለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ



የማገገሚያ እቅድ-Recovery Plan

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለትምህርት ቤቶች እና ለዋናው ጽ/ቤት ተማሪዎችን፣ ሠራተኞችን እና ቤተሰቦችን በ 2020-2021 የትምህርት ዓመት በትምህርት ማህበረሰባችን ውስጥ ወይ በትምህርት ቤቶች ህንፃዎች ውስጥ ካልሆነም የዳበረና የተሻሻለ የትምህርት ቀጣይነት ፕሮግራም ላይ እንደገና ስለማሰማራት እና በተባበረ ጥረት ደረጃ በደረጃ የሚሠሩ ተግባሮችን የማገገሚያ እቅድ እየተሠራ ነው። የእኛ የማገገሚያ እቅድ በስቴቱ “Maryland Strong: Road Map to Recovery” አማካይነት ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (Maryland State Department of Education) እና ከበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከሎች (Centers for Disease Control)፣ እና የአካባቢ የጤና ኃላፊዎች (local health officials) ከሚተላለፍ መመሪያ ጋር በአንድ ላይ ይፋ ይደረጋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የማገገሚያ እቅድ-The MCPS recovery plan የሚያካትታቸው ስትራቴጂዎች ከተማሪዎች እና ከትምህርት ቤት ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ የትምህርት ትኩረት ማድረግ፣ አካደሚያዊ ምጡቅነትን ማዳበር፣ ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች መደረግ ያለባቸው ድጋፎችን በመለየት ውጤታማ እና ተመጣጣኝ የሆነ ሙያዊ የትምህርት እድሎችን ለሁሉም ሠራተኞች መስጠት፣ ቀጣይ እድገትን ለማዳበር ወቅቱን የጠበቀ የኮሙኒኬሽን እና የግብረመልስ እድሎችን መፍጠር።

የማገገሚያ እቅድን በመፍጠር ላይ ወላጆች፣ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የሚያረጋግጥ መጠነ ሰፊ የሆነ ባለ ብዙ ፈርጅ አቀራረብ ዘርግተናል። በመጪዎቹ ሣምንቶች ይበልጥ መረጃዎች ይገለጻሉ። ሜይ 28 በትምህርት ቦርድ ስብሰባ የተካሄደውን ውይይት እዚህ መመልከት ይችላሉ።

የሰመር ት/ቤት

ሜይ 23 የማህበረሰብ ወቅታዊ መግለጫ ላይ ፣ እንደገለጽንላችሁ፣MCPS ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሪጅናል፣ ትምህርት ቤትን መሠረት ያደረገ እና ሌላ ዲስትሪክት አቀፍ ፕሮግራሞችን በሠመር ወቅት ትምህርት መስጠት እና እውቀት የማዳበር እቅዶቹን ይቀጥላል። እነዚህ ፕሮግራሞች፣ አንዳንዶቹ በነፃ የሚሰጡ ሲሆን፣ የሒሳብ እና የሊትረሲ ትምህርት ይሰጣል፣ በተጨማሪ እንደየተማሪዎቹ ፍላጎት የማዝናናት ችሎታ የማዳበር እድሎችን እና ማህበራዊ-ስሜታዊ/ስነልቦናዊ ድጋፍ ይሰጣሉ። ባለፉት ዓመታት እንደተደረገው ሁሉ፤ MCPS ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ኦንላይን ኮርሶችን ይሰጣል፣ በቅርቡ ምዝገባ ይጀመራል።

በዚህ ሠመር ቤተሰቦች የሚያጋጥማቸውን ውጣ ውረዶችን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ስለ ሠመር የሚኖራቸውን ሃሳብ ከወላጆች አስተያየቶቻቸውን መስማት እንፈልጋለን። ፕሮግራሞቹ በሙሉ የሚሰጡት ኦንላይን ቢሆን ይሳተፋሉ? ምን ያህል የረዘመ ፕሮግራም ወይም በቀን ለስንት ሠዓት ቢሆን ይመርጣሉ? እባክዎ ይህንን አጭር የዳሰሳ ቅኝት እዚህ ይሙሉ።

ፕሮግራሞቹ እስከ ጁላይ 13 ይጀመራሉ። ስላሉት ፕሮግራሞች፣ ስለምዝገባ ቀኖች እና ፕሮግራሞቹ ስለሚጀመሩባቸው ቀኖች ዝርዝር ጁን 8 በሚሆንበት ሣምንት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ድረ-ገጽ ላይ ለቤተሰቦች ይገለጻል MCPS Summer Programs webpage


ለስፔሻል ኢጁኬሽን ተማሪዎች የተራዘመ የትምህርት ዓመት ፕሮግራሞች

በአካል ፊት-ለ-ፊት ለማስተማር ያሉት ሁኔታዎች አስተማማኝ ባለመሆናቸው፣ የወቅቱ የተራዘመ አመት የስፔሻል ኢጁኬሽን ፕሮግራም (ESY) በቨርቹወል ይሰጣል። የስፔሻል ኢጅኬሽን አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ልጃቸው ለ ESY ብቃት ይኖረው-ይኖራት እንደሆን ለማረጋገጥ ከልጃቸው ኬዝ ማናጀር ጋር ስብሰባ ይኖራቸዋል። ESY ማለት ስንክልና ያላቸው ተማሪዎች በዚህኛው የትምህርት ዓመት በተራዘመ መዘጋት ምክንያት ለመከታተል ያልቻሉትን ክህሎቶች የሚሰጥ ነው። እነዚህ ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ ውስጥ ያካበቱትን የክህሎት እድገት ለመጠበቅ እንዲችሉ በግላዊ ሁኔታ ከሚሰጡት የትምህርት ፕሮግራሞች "Individualized Education Program (IEP)" ውስጥ የተወሰኑትን ትምህርት ቤቶች በሥራ ላይ በማይሆኑበት ክፍት ጊዜ በሠመር ወሮች አገልግሎት ይሰጣል።
ስለ ESY ውሳኔ የሚሰጥባቸው ስብሰባዎች በሙሉ እስከ ጁን 8 ይጠናቀቃሉ። ስለ ESY ፕሮግራሞች ካለንደር እንደሚከተለው ነው፦

  • ዓርብ፣ ጁላይ 10/2020 ለ ESY መምህራን የቅድመ -አገልግሎት ቀን ይሆናል
  • ሰኞ፣ ጁላይ 13-ዓርብ፣ ኦገስት 7/2020፦ ስለ አራት- ሣምንት ፕሮግራም ጠቃሚ መረጃዎች የሚሰጡባቸው ቀኖች ይሆናሉ።
  • ሰኞ፣ ጁላይ 13-ዓርብ፣ ኦገስት 14/2020፦ ስለ አምስት- ሣምንት ፕሮግራም ጠቃሚ መረጃዎች የሚሰጡባቸው ቀኖች ይሆናሉ።

በተናጠል ስለሚደረጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቨርቹወል የምረቃ ስነ ስርአቶች

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ለተማሪዎቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ከጁን 8 እስከ ጁን 12 በተናጠል ቨርቹወል የምረቃ ስነ ስርአቶች ያካሄዳሉ። እነዚህን የምረቃ ስነስርአቶች ለመመልከት፦ በ MCPS ድረገጽ ላይ - MCPS graduation webpage እና በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ድረገጽ ላይ ይገኛል። የምረቃ ስነ ስርአቶቹ በተጨማሪም በ MCPS TV (Comcast channel 33, RCN channel 88, and Verizon channel 35) በድጋሚ ይተላለፋሉ።


ዲስትሪክት አቀፍ የክልል ጥናት ትንታኔ

የትምህርት ቦርድ ሜይ 28 ባደረገው ስብሰባ ስለ ዲስትሪክት አቀፍ የማካለል ዝርዝር ጥናት የማጠቃለያ ሪፖርት እስከ ዲሴምበር 1/2020 ይፋ እንደሚደረግ ታሳቢ በማድረግ እንዲዘገይ ወስኗል። ይህ መዘግየት አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት በጠቅላላ የትምህርት ሲስተሙን እና የማህበረሰቡን ጥረቶች የወሰደብን የህዝብ ጤንነት ድንገተኛ-አጣዳፊ ሁኔታ በመከሰቱ ነው። የህዝብ ጤና በአስተማማኝነት በሚሻሻልበት ጊዜ እና ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ሁኔታው አመቺ ሲሆን የ MCPS ባልደረቦች እና የውጭ ኮንሰልታንት አጥኚ ቡድን፣ WXY፣ ፎል ላይ በዲስትሪክት አቀፍ የማካለል ጥናት ላይ እንደገና ይሠማራሉ።

ማርች 20/2020 MCPS ስለ ዲስትሪክት አቀፍ የክልል ጥናት ትንታኔ ጊዜያዊ ሪፖርት ቀርቧል። ሪፖርቱ በፕሮጀክቱ የመጀመሪያዎቹ ወራት ከማህበረሰብ የተገኙ ግብረመልሶችን በማሰባሰብ በማካለል ትንተና ላይ ግንዛቤ መሰጠት ያለባቸውን እውነታዎች መሠረት ያደረጉ ሰፊ እና ጥልቅ ጥናት እና ትንታኔዎችን በአንድ ላይ የያዘ ነው። ጊዜያዊ ሪፖርቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።


የተማሪ የአገልግሎት ትምህርት ቅጾች ቀነገደብ ጁን 5 ያበቃል

በ2019 ሠመር የተጠናቀቁ የተማሪ የአገልግሎት ትምህርት - Student Service Learning (SSL) የመጀመሪያ ሴሚስተር፣ እና የሁለተኛ ሴሚስተር በሪፖርት ካርዶች ላይ መመዝገብ ስለሚኖርባቸው ቅጾች በሙሉ መቅረብ ያለባቸው ቀነ ገደብ እስከ ጁን 5/2020 ነው። ቅጾቹ ለትምህርት ቤትዎ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት አስተባባሪ "SSL coordinator" ከጁን 5 ቀነገደብ በፊት በኢ-ሜይል መላክ አለባቸው። የ 2020 ሠመር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት - SSL ዶኩመንቶች ሴፕቴምበር 2020 ተመላሽ ይደረጋሉ። ተማሪዎች ተሞልተው የተዘጋጁ የ SSL ቅጾችን በቀጥታ ለትምህርት ቤቶቻቸው የተማሪ አገልግሎት ትምህርት አስተባባሪ-SSL coordinator ኢ-ሜይል ማድረግ አለባቸው፦


ስለ ምዋእለ ህፃናት ምዝገባ- Kindergarten Registration

ሴፕቴምበር 1/2020 5 ዓመት ለሚሞላቸው ልጆች የምዋእለ ህፃናት ምዝገባ-Kindergarten Registration ክፍት ነው። ተማሪዎች የዲስትሪክቱን የምንባብ እና የሒሳብ ግቦችን በከፍተኛ ደረጃ በማከናወን ከሚታወቁት መካከል የ MCPS ምዋዕለህፃናት ፕሮግራም በአገር አቀፍ ደረጃ በጣም ምርጥ ከሚባሉት አንድኛው እንደሆነ በስፋት የታወቀ ነው። ስኬታማ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኣምራች ዜጋ ለማዘጋጀት እጅግ ወጣት የሆኑት ተማሪዎቻችን ከጅምሩ የበለፀገና ሁለገብ የሆነ የትምህርት ተሞክሮ መቀበል እንዳለባቸው እናምናለን። ልጆቻቸውን ማስመዝገብ የሚፈልጉ ቤተሰቦችን ለመርዳት MCPS አዲስ ኦንላይን የምዝገባ ሂደት ጀምሯል። ቤተሰቦች ሒደቱን በሦስት መንገዶች ሊያጠናቅቁ ይችላሉ፦Kindergarten

  1. ኦንላይን፣ በዚህ የምዝገባ ዳሰሳ ይጀምራሉ Registration Survey
  2. በስልክ፦ 240-740-5999 በመደወል
  3. በወረቀት ቅጾች-ፎርሞች ይህንን የምዝገባ ቅኝት ይሙሉ ወይም ወደ እርስዎ ቤት በፖስታ እንዲላክልዎት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-5999 ደውለው ይጠይቁ።

ለፎል ስለሚኖርዎት እቅድ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ነገር ግን ልጅዎን ትምህርት ቤት ክፍት በሚሆንበት ጊዜ የሚልኩ ከሆነ፣ እባክዎ አሁኑኑ ያስመዝግቡ(ቧ)ት። የማስመዝገቢያ ማቴሪያሎችን ያገኛችሁ ቤተሰቦች በተቻለ ፍጥነት ቅጾቹን ሞልታችሁ እንድታቀርቡ ትጠየቃላችሁ።
ስለ MCPS Kindergarten Program ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ
ልጅዎን አሁኑኑ ያስመዝግቡ


"Pride Town Hall" ሜይ 27 ተካሂዷል

MCPS ሜይ 27 "virtual Pride Town Hall" አካሂዷል። የሁነቱ ዓላማ የኮሮና-COVID-19 የጤና ቀውስ ባለበት ወቅት MCPS ከ LGBTQ+ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰብ ጋር ዳግም ግንኙነት ለማድረግ ነው። ታወንሆል በተካሄደበት ጊዜ፣ የማህበረሰብ አጋሮች እና ድርጅቶች ያላቸውን ሪሶርሶች ለተማሪዎች እና ለቤተሰብ በማካፈል፣ በተራዘመ የትምህርት ቤት መዘጋት ወቅት የ LGBTQ+ ወጣቶች ስለሚያጋጥሟቸው ውጣውረዶች ተወያይተዋል። ከተሳታፊዎች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ የተገኙት፦ የ MCPS ሠራተኞች እና ከ Casa Ruby ተወካዮች፣ the Family Justice Center፣ GLSEN፣ the Montgomery County Council of Parent Teacher Associations (MCCPTA)፣ MoCo Pride Center፣ MoCo Pride Student Organization፣ PFLAG እና SMYAL ናቸው። Town Hall እዚህ መመልከት ይችላሉ።


የ 2020 የህዝብ ቆጠራ፦ የእርስዎ ድምፅ ዋጋ አለው

ለእያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ ስለ 2020 የህዝብ ቆጠራ በኦንላይን፣ በስልክ ወይም በፖስታ የመመለስ እድሎች ተሰጥተዋል። የመራጭነት ጥሪ ያልደረሳቸው ቤተሰብ ነዋሪዎች (ወይም ማግኘት ካልቻሉ) የመራጭ ጥሪ ያልደረሳቸውም ቢሆን—ወይም ያለ ቆጠራ መታወቂያ—አድራሻቸውን በመስጠት አሁንም በኦንላይን መመለስ ይችላሉ። በኦንላይን ለመመለስ፣ እባክዎ www.2020Census.gov ይጎብኙ ወይም በስልክ ለመመለስ ይህንን ቁጥር ይጠቀሙ፦ 844-330-2020


2020 የፕራይመሪ ምርጫ

በፊት ለኤፕሪል 28/2020 ታስቦ የነበረው የፕራይመሪ ምርጫ ወደ ጁን 2/2020 ተገፍቷል። ለተመዘገቡ እና ብቁ ለሆኑ መራጮች በጠቅላላ ስለዚህ ምርጫ የድምፅ መስጫ በፖስታ ተልኮላቸዋል። የተሞሉት የድምፅ መስጫዎች እስከ ጁን 2/2020 ድረስ በፖስታ መመለስ አለባቸው። ድምፃቸውን በምርጫ ጣቢያ ለማስገባት የሚፈልጉ መራጮች በድምፅ መስጫ መቀበያ ጣቢያዎች (lugares designados para dejarlos) ከሐሙስ፣ ሜይ 21/2020 እስከ ማክሰኞ፣ ጁን 2/2020 ለማስገባት ይችላሉ። በፖስታ ለመምረጥ ካልቻሉ፣ ምርጫ በሚካሄድበት ቀን ጁን 2/2020 ነዋሪ በሆኑበት አካባቢ የምርጫ ጣቢያ በአካል ለመምረጥ ይችላሉ። የበለጠ መረጃ እዚህ ይገኛል።


Important Online Resources: