የመሳሪያ/ሽጉጥ ትምህርት ስብሰባዎች በ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች

September 13, 2022

ውድ የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቤተሰቦች፣

ሁላችንም የምንጋራው መሳሪያዎች/ሽጉጦች በማህበረሰባችን፣ በወጣቶች እና በት/ቤቶች ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ላይ ትኩረታችሁን ማምጣት እንፈልጋለን እናም እየጨመረ የመጣ እና ከፍተኛ አደጋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈጥሯል። በዚህም የተነሳ፣ የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከሞንጎመሪ ካውንቲ ስቴት አቃቤ ህግ ጽ/ቤት እና ሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቻችንን የት/ቤቶች እና ተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅ ላይ ለማስተማር በጥምረት ይሰራሉ። ይሄ አስፈላጊ አጋርነት በዋነኝነት የሚመረኮዘው ግንዛቤን፣ እውቀትን እና ትምህርትን ይሄንን የማድረጊያ ቁልፍ ግብዓቶች ማድረግ ላይ ነው።


እውነታዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
የሀገራዊ መረጃ ከ የመሳሪያ/ሽጉጥ ሁከት መዝገብ / Gun Violence Archive የተገኘው ሪፖርት እንደሚያደርገው በሽጉጦች የሚገደሉ ወይም ጉዳት የሚደርስባቸው ታዳጊዎች ቁጥር ከ 2014 ጀምሮ በእጥፍ ጨምሯል እና በአለማወቅ መታኮስ ውስጥ የሚሳተፉ ታዳጊዎች ቁጥር በ 44 ፐርሰንት ጨምሯል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥም አሳሳቢ ቁጥሮች አሉ፤ በዚህ አመት እስከ ኦገስት 14 ድረስ 790 ህገወጥ መሳሪያዎች ተይዘዋል፣ ከ 2020 አንስቶ ወደ 75 ፐርሰንት የሚጠጋ ጨምሯል፣ በዛ ጊዜ የተያዙት 452 መሳሪያዎች ነበሩ። ሜሪላንድ ውስጥ፣ ማንኛውም ሰው 21 አመት እስኪሞላው ድረስ መሳሪያ መያዙ ህገወጥ ነው። እውነታውም፣ ማንኛውም 16 ወይም ከዛ በላይ እድሜ የሞላው ሰው መሳሪያ ይዞ ቢገኛ የሚከሰሰው እንደ አዋቂ ነው።

ተማሪዎች ምን እንደሚማሩ፦
በመላው በ2022 ፎል ውስጥ ታቅደው በሚካሄዱ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስብሰባዎች፣ ተማሪዎች ህጉን በሚመለከት እና ህግ መጣስ ስለሚያስከትላቸው ነገሮች፣ ወጣቶች መሳሪያዎችን ወይም ሁከት/አደጋ ሳያደርሱ ችግሮችን የሚፈቱባቸው ስልቶች፣ እና በንቃት የመከታተል እና  “አንድ ነገር ካያችሁ፣ አንድ ነገር ተናገሩ” / “see something, say something” አካሄድ/አሰራር ላይ መረጃ ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም ስብሰባዎቹ እንዴት አንድ ሰው ራሱን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት ብጥብጥ ሊመርጥ እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶችን መለየት እንደሚችሉ፣ ማንነት ሳይገልፅ መረጃ መስጫ የሜሪላንድ ስልክ / Maryland Tip Line እና ከብጥብጥ-ነፃ የሆነ ማህበረሰብን አስፈላጊነት በሚመለከት መረጃ ይሰጣሉ።

ማወቅ የሚኖርባችሁ፦
እነዚህ ስብሰባዎች በሚመጡት ቀጣዮቹ ቀናት እና ሳምንታት ይጀምራሉ። ት/ቤቶች መቼ ላይ በልጅዎ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሊሰጥ እንደታቀደ በትክክል የሚያሳይ መረጃ ያጋራሉ/ይልካሉ። ከ MCPS ጋር ያለዎትን ዘላቂ አጋርነት እናደንቃለን እና እንደ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ እና ሞግዚቶች፣ ይሄንን መልዕክት በቤትዎም እንዲያስተጋቡ እንጠይቃለን። ተማሪዎች ከብጥብጥ ይልቅ መሻት/መፈለግ ያለባቸው የሚታወቅ አዋቂ ሰውን ድጋፍ ነው። ቤተሰቦች በቀላሉ የት/ቤታቸው አስተዳዳሪ ጋር በመገናኘት ከእነዚህ ትምህርቶች ልጆቻቸውን ለማስወጣት/ላለማካተት መምረጥ ይችላሉ።

ለማስታወስ ያህል፦ ወደ ት/ቤት ተይዘው የሚመጡ መሳሪያዎችን በሚመለከት ለረጅም ጊዜ ሲተገበር የቆየ ፖሊሲ እና ዲሲፕሊን አለ። በመሰረታዊነት ማንኛውም አይነት መሳሪያዎች ወደ የትኛውም MCPS ት/ቤት ይዘው መመጣት የለባቸውም። ማንኛውም ሽጉጥ ወይም ሌላ መሳሪያ ይዞ የተገኘ ተማሪ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃዎች ሊወሰዱበት/ባት ይችላል፣ ይሄም መሰረት ያደረገው MCPS የስነምግባር ኮድ/ህግ ነው እና የአካባቢ፣ የስቴት ወይም የፌደራል ህግንም መጣስ ሊሆን ይችላል።

የስቴቱን አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ለቁርጠኝነቱ እና አጋርነቱ ማመስገን እንፈልጋለን፤ በጋራ በመሆን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንቁ፣ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር መስራት እንችላለን።

Dr. Monifa B. McKnight Interim Superintendent, Montgomery County Public Schools
MCPS የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

John McCarthy
የስቴት አቃቤ ህግ፣ ሞንጎመሪ ካውንቲ

ጠቃሚ መረጃዎች፦

  1. ማንነት ሳይገልፅ ጥቆማ መስጫ ስልክ፦ 1-833-MD-B-SAFE (1-833-632-7233)፣ ኦንላይን በ safeschoolsmd.org
  2. በድንገተኛ አደጋ ጊዜ፣ 911 ደውሉ
  3. ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ BeWell365
  4. የአዕምሮ ጤና ግብዓቶች እና ድጋፎች


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools