ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 1 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

የሚከተሉት 10 ነገሮች ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 1 መታወቅ ያለባቸው ነገሮች ናቸው። የሚያካትቱትም የባስ/አውቶቢስ እና የእግረኛ ደህንነት፣ ስለ አዲሱ ሀሪየት አር. ተብማን (Harriet R. Tubman) መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቪድዮ፣ ለአትሌቶች መጓጓዣን የሚመለከት መረጃ፣ ParentVUE፣ ለነፃ እና የቀነሰ-ዋጋ ምግቦች እንዴት ማመልከት እንደሚቻል እና ሌሎችንም ነገሮች ነው።

  1. first day የመጀመሪያ የትምህርት ቀን እይታዎችን እና ድምፆችን ተመልከቱ!

    MCPS-TV የተማሪዎችን እና ሰራተኞችን በ2022 ትምህርት መጀመሪያ ቀናቸው ላይ የነበሯቸውን አስደሳች ጊዜያት ይዞ አስቀምጧል፦ https://www.youtube.com/watch?v=q4nMKf273AE
    የሚመለከቱት የፎቶ ስብስብ የትምህርት መጀመሪያ ቀን ፎቶዎችን ነው

  2. Harriet Tubman ስም ውስጥ ምን አለ? ሀሪየት አር. ተብማን (Harriet R. Tubman) መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

    የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል 210ኛ ት/ቤት የተሰየመው ለሀሪየት አር. ተብማን (Harriet R. Tubman) ክብር/መታሰቢያ ነው፣ የአሜሪካ ጀግና፣ የነፃነት ታጋይ እና ማህበራዊ አክትቪስት። ተከታዩ ቪድዮ ስኬቶቿን እና የህይወቷን መገለጫዎች ያሳያል፦ https://youtu.be/2wxxGcCRswE

  3. Respect the Bus አውቶብሱን አክብሩ! ህጎቹን እወቁ እና ደህንነታችሁን ጠብቁ

    ተማሪዎች ከት/ቤት እና ወደ ት/ቤት እየተጓዙ ነው። እየነዳችሁ እንዳለ የ MCPS ባስ ቀይ መብራቱ እየበራ እና አቁሙ የሚል እጅ እና ምልክት እያሳየ ከገጠማችሁ፣ ማቆም አለባችሁ! ህግ ነው እናም ህይወት ሊያድን ይችላል።
    በተከታዩ ቪድዮ ላይ የበለጠ ተማሩ፦ https://youtu.be/H8CMKOZDu6g?t=4
    ስለ ባስ ደህነነት የበለጠ ተማሩ

  4. Pedestrian Safety የእግረኞች ደህንነት፦ ውድድር አይደለም፣ በደህንነት ከምትሄዱበት ድረሱ

    ወደ ት/ቤት በእግር ስትሄዱ ደህንነታችሁን እንዴት እንደምትጠብቁ እወቁ። የእግረኛ ማቋረጫ ተጠቀሙ፣ ተራመዱ የሚለውን ምልክት ጠብቁ እና የሚታይ ቦታ ላይ ሁኑ። በተከታዩ ቪድዮ ላይ የበለጠ ተማሩ፦ https://youtu.be/8MbZjml4v-U
    ለእግረኞች፣ ሳይክል ለሚነዱ፣ እና መኪና ለሚነዱ ጠቃሚ ምክሮቹን ተመልከቱ

  5. WaymakingMCPS Wamaking፦ ስለ MPX ውይይት

    በዚህ MCPS Waymaking ክፍል ላይ፣ ኪምበርሊ ታውንሴንድ (Kimberly Townsend)፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጤና እና የሰው አገልግሎቶች ክፍል የበላይ አስተዳዳሪ፣ እና MCPS ት/ቤት ስርዓት የህክምና ባለሙያ፣ ፓትሪሲያ ካፑናን (Patricia Kapunan) ከዶ/ር ክሪስቲና ቼስተር (Dr. Christina Chester) ጋር በመሆን Monkeypox ቫይረስ ወይም MPX ላይ እና በምን መንገድ መስፋፋቱን መከላከል እንደሚቻል ይወያያሉ። https://youtu.be/mkdq9v8PuQk

  6. MCPS አትሌቲክስ፦ መጓጓዣን በሚመለከት ህጎችን ተገንዘቡ

    athleticsMCPS ባሶች ቡድኖች ከቦታቸው-ውጪ ለሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ወይም ክንውኖች ወቅቱን ሙሉ እንዲጠቀሟቸው ይገኛሉ፣ ይሄም ሹፌሮች እና ባሶች ይኖራሉ ብሎ በማሰብ እና በጨዋታ ሰአቱ መሰረት ነው። ማስታወስ የሚገባው፣ ባሶች ከትምህርት ሰአት በኋላ ተማሪዎችን ስለሚያመላልሱ፣ ባሶችን ከከሰአት 1:35-4:35 p.m. ከሰኞ-አርብ ማግኘት አይቻልም። ይሄ እክል/ችግር፣ ቆይቶ ከመውጣት እና ቀድሞ ወደ ቤት ከመሄድ ጋር ተደምሮ፣ የወላጅ እና የተማሪ ሹፌሮች የሚመደቡበት ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላል። የወላጅ ወይም የተማሪ ሹፌሮች ከቦታው-ውጪ ለሚካሄዱ ዝግጅቶች የሚመረጡ ከሆነ፣ የእያንዳንዱ ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች ከወላጅ ወይም ተማሪ ሹፌሮች ጋር ተማሪያቸው እንዳይጓዝ ያለመምረጥ መብት አላቸው። ወላጆች በየትኛው የመጓጓዥ አይነት ተማሪ-አትሌታቸው በወቅቱ እንዲጓዝ እንደሚስማሙ መመረጥ ይጠበቅባቸዋል። መረጃው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ይውላል። በመጨረሻም፣ የመጓጓዣ አይነቱን የመምረጥ ውሳኔው የሚደረገው የትብብር ሂደትን በመጠቀም የሚገኙትን ባሶች እና የወላጆችን/አሳዳጊዎችን ለእያንዳንዱ ነገር ስምምነት እና ምርጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ከልምምዶች እና ወደ ልምምዶች የሚደረግ ጉዞ የእያንዳንዱ ተማሪ-አትሌት እና ቤተሰብ ሀላፊነት ነው። አባክዎን አሰልጣኝዎን ወይም የአትሌትኪስ ባለሙያዎን ለተጨማሪ መረጃ ያማክሩ፤፡ በ MCPS አትሌቲክስ R.A.I.S.E. የዜና መፅሄት ላይ (በእንግሊዘኛ) እና (ስፔንኛ) የበለጠ መረጃ ያግኙ

  7. SSL ስለ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት የበለጠ ይወቁ

    የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ወይም SSL ለምርቃት አስፈላጊ መስፈርት ነው። ተመልክተው እነዚህን አስፈላጊ የሆኑ ሴፕቴምበር 2022 SSL ማሻሻያዎች የበለጠ SSL ስለሚፈጥራቸው እድሎች፣ ቅፆች እና እንዴት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ SSL ውጤታቸው እና ተግባራቸው ላይ ጊዜውን የጠበቀ መረጃ ያገኛሉ የሚለውን ይመልከቱ።
    SSL በተግባር ተመልከት፦ https://youtu.be/8k1QheMdl-8

  8. በስቴት የታዘዘ የጤና ትምህርት ስርዓት ማሻሻያ 

    የሜሪላንድ ስቴት ትምህርት ክፍል (MSDE) አሁን ላይ ተማሪዎች በ2025 ክፍል እና ከዛ በኋላ ለአሉት የ 1.0 የጤና ትምህርት የምርቃት መስፈርት እንዲያሟሉ ይጠብቃል። የጤና ትምህርት ይዘቶች የሚያካትቱትም በሁሉም ክፍሎች የሚገኙ ለተለያዩ ማህበረሰቦች መረጃ እና ግብዓቶችን ነው፣ ይሄም LGBTQ+ ማህበረሰብ አባላትን ያካትታል።
    ትምህርት ቤቶች በተናጠል ወላጆች እና አሳዳጊዎች የትምህርት ስርዓቱን የመገምገም አቅማቸውን ከጤና አስተማሪ ጋር ሆነው እንዲጠቀሙ እና በጤና ትምህርት ላይ ምን ጊዜ ላይ የትኛው ርዕሶች እንደሚዳሰሱ እንዲያውቁ ወደቤት መረጃ እየላኩ ነው።
    ቤተሰቦች በቤተሰብ ህይወት እና በሰው ፆታዊ ተፈጥሮ ትምህርት ክፍል ላይ አለመካፈል የሚችሉት ከስቴት ህግ ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ነው።
    MSDE የጤና ትምህርት A እና የጤና ትምህርት B ላይ ያሉ የህግ ይዘቶችን ለይቶ ያስቀመጠው MSDE Health Education Curriculum Framework ነው።

  9. በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ጥቅሞችን ለማግኘት በኦንላይን አሁን ያመልክቱ
    ለነጻ ወይም ለዋጋ ቅናሽ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች አሁን ለትምህርት ቤት የምግብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ነጻ የቁርስ እና የምሳ ምግብ ያገኛሉ።

    እዚህ ያመልክቱ።
    ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ

  10. ከትምህርት ቤትዎ ጋር ለመገናኘት ለ ParentVUE(ፓረንት ቪው)ይመዝገቡ

    ለMCPS አዲስ የሆኑ ቤተሰቦች በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ለParentVUE(ፓረንት ቪው) መለያ እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። ParentVUE(ፓረንት ቪው)  ስለ ክፍሎች፣ የተማሪ መገኘት መከታተያ፣ የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ፣ የmyMCPS ክፍል መክፈቻ እና ሌሎችንም በተመለከተ መረጃን ለመለዋወጥ ለት/ቤቶች እንደ ዋና የመገናኛ መዘዋወርያ ሆኖ የሚያገለግል የኦንላይን  የወላጅ ፖርታል ነው።
    ParentVUE(ፓረንት ቪው) ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና የተማሪዎችን መረጃ የሚመለከቱበትን መንገድ ያቀርባል። ለአትሌቲክስ፣ ለልዩ ፕሮግራሞች ይመዝገቡ፣ ከመምህራን ጋር ይገናኙ እና የተማሪዎን መረጃ በየአመቱ ያረጋግጡ።
    ParentVUE(ፓረንት ቪው) እንዲሁም የዲጂታል ትምህርት መድረክ የሆነውን Canvas/MyMCPSClassroomን(ካንቫስ ማይ ኢምሲፒአኢስ ክላስሩም)ን ይፈቅዳል። ወላጆች እና አሳዳጊዎች የማስተማሪያ መረጃን እና ግብዓቶችን ማየት እና ስለ ምደባዎች እና ውጤቶች ማንቂያዎችን/መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/ Montgomery County Public Schools 
###



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools