ከ MCPS የት/ቤቶች ጤና መኮንን የተላለፈ አስቸኳይ መልእክት

December 9, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ይህንን መልእክት የማስተላልፈው ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ማህበረሰባችንን ስለሚጎዳ አደገኛ የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም እንዲያውቁ ለማድረግ ነው። ሰው ሰራሽ አፒዮይድስ፣ በተለይም በህገ-ወጥ መንገድ fentanyl፣ ከመጠን በላይ በመጠጣት እና ከመጠን በላይ በመውሰድ የሞት ተጠያቂዎች ናቸው። በ 2021፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ከ70% በላይ ከሚወስዱት fentanyl ጋር የተዛመዱ እና fentanyl ሱሰኝነት ጋር የተጣበቁ ንጥረ ነገሮች ወይም ሌላ ነገር የሚመስሉ ንጥረ ነገሮች (ለምሳሌ Xanax፣ Adderall፣ Percocet፣ ወይም oxycodone) ነገር ግን በውስጣቸው fentanyl ነበረው። ለዚህ አደገኛ ወረርሽኝ ሁሉን አቀፍ እና የተቀናጀ አካሄድ MCPS ከአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በትጋት መስራቱን ይቀጥላል።

በህግ የተከለከለ ወይም ያልተፈቀደ ፌንታኒል/fentanyl ምንድን ነው?
Fentanyl ከሞርፊን ከ 50-100 እጥፍ የበለጠ ኃይለኛ ለህመም ማስታገሻ የሚታዘዝ መድሃኒት ነው። ከመጠን በላይ ፈንታኒል/ fentanyl መውሰድ የሚያስከትለው ሞት ህገ-ወጥ ከመሆኑም በላይ በዱቄት መልክ፣ በክኒን፣ በፈሳሽ ወይም በአፍንጫ በሚረጭ መልክ እየተሠራ ይሸጣል። ሌሎች እንደ ማሪዋና፣ ኮኬይን፣ ሄሮይን ወይም በህገወጥ መንገድ የሚሸጡ ክኒኖች በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች በማስመሰል ያለተጠቃሚው እውቀት በህገ-ወጥነት fentanyl ታሽገው ሊቀርቡ ይችላሉ።

ለምንድነው ወጣቶች እንደ ፋንታኒል/fentanyl ያሉ መድሃኒቶችን የሚወስዱት እና እንዴት ነው የሚያገኙት?
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች እና ትናንሽ ልጆች እንኳን ለብዙ ምክንያቶች ሕገ-ወጥ ንጥረ ነገሮችን ሊጠቀሙ ይችላሉ።  የሙከራ ወይም የእኩዮች ግፊት ወደ ተጨማሪ ችግሮች የሚያመራ የአጠቃቀም ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል። ከአእምሮ ጤና ሁኔታዎች ጋር የሚታገሉ፣ወይም ቀድሞውንም ሌሎች መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ ወጣቶች የመሞከር ዕድላቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ወይም ከአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ከ fentanyl ጋር ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር ስለሚካተት ግለሰቦች እንደሚወስዱት እንኳን ላያውቁ እንደሚችሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው። የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች የምርታቸውን አቅም ለመጨመር ፋንታኒል/fentanyl ሊጠቀሙ ይችላሉ። እንዲሁም አደንዛዥ እጾችን ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ ማህበራዊ ሚዲያን ይጠቀማሉ፣ ይህንንም ለወጣቶች ከእኩዮቻቸው ወይም በቀጥታ ከኦንላይን ምንጮች ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች የበለጠ ተደራሽ ያደርጋሉ። 

ለምንድነው ህገወጥ ፌንታኒል/fentanyl በጣም አደገኛ የሆነው?
ፌንታኒል በጣም ኃይለኛ ኦፒዮይድ ስለሆነ በጣም ትንሽ መጠን እንኳ ለአንድ ጊዜ ቢወሰድ ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከመጠን በላይ መውሰድን ሊያስከትል ይችላል፥ እና ግለሰቡ(ቧ) የወሰደ(ች)ው መድሃኒት ህገ-ወጥ ፋንታኒል/fentanyl እንዳለበት እንኳን ላይታወቅ ይችላል። የ fentanyl ሃይል ደግሞ ለመዝናናት፣ ለህመም ማስታገሻ ወይም ለመዝናናት ጊዜያዊ ደስታ የሚፈልጉ ግለሰቦች በፍጥነት በሱስ ሊያዙ ይችላሉ። አንዴ በሱስ ከተያዙ በኋላ በጣም የማይመቹ እንደ ከፍተኛ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ጭንቀት፣ ላብ ወይም ብርድ ብርድ ማለት ሊያስከትልባቸው ስለሚችል እነዚህን ምልክቶች ለማስወገድ በየ 2-3 ሰዓቱ መውሰድ ሊኖርባቸው ይችላል።

አዋቂዎች ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?
ወላጆች እና ሌሎች ተንከባካቢዎች እራሳቸውን ማስተማር እና ከልጆች ጋር ስለ አደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም አደገኛነት በተለይም ስለ fentanyl እና እንዴት መጠቀምን ማስወገድ እንደሚቻል፣የአደንዛዥ እጾችን መጠቀም አደገኛ መሆኑን በማስገንዘብ ረገድ ቤተሰብ ስለሚኖረው ተስፋ እና እርዳታ እና ድጋፍ እንደሚገኝ ከልጆች ጋር ውይይቶችን ማድረግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም፣ አሰቃቂ ሁኔታ እና የአእምሮ ጤና ምልክቶችን ማወቅ ወጣቶች እና ቤተሰቦች ቀደም ብለው ድጋፍ እንዲያገኙ እና አደገኛ ወይም ገዳይ ውጤቶችን ለማስወገድ ይረዳል።
ናሎክሶን (ናርካን)/Naloxone (Narcan) በአፍንጫ የሚረጭ የድንገተኛ ጊዜ መድሃኒት ሲሆን ይህም ኦፒዮይድ ከመጠን በላይ መውሰድ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስታገስ ወዲያውኑ ሊሠራ ይችላል። የ naloxone ማስታገሻነት ጊዜያዊ መሆኑን ማወቅ እና ከመጠን በላይ አደንዛዥ እፅ መውሰድን ለመታከም ግለሰቦች አስቸኳይ የሕክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል (911)። ውጤታማነቱም በመድኃኒቱ እና በተወሰደው መጠን ላይ የሚመረኮዝ ስለሆነ ልክ እንደ ሕገወጥ ፌንታኒል ያሉ ኃይለኛ ኦፒዮዶችን ለማስታገስ ከፍተኛ መጠን ያለው ናሎክሶን ሊያስፈልግ ይችላል። የሜሪላንድ Good Samaritan Law ግለሰቦችን ከአልኮል ወይም ከሌሎች መድሃኒቶች ጋር በተገናኘ ድንገተኛ አደጋ ላጋጠመው ሰው የህክምና እርዳታ የሚያደርጉ ሰዎችን በወንጀል እንዳይከሰሱ ጥበቃ ያደርጋል።

በቤት ውስጥ የመድኃኒት ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ወይም ወጣቶች አደገኛ የኦፒዮይድ አጠቃቀም አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ ስጋት ካደረባቸው ቤተሰቦች ናሎክሶን/naloxone በቤታቸው እንደሚገኝ ማረጋገጥ አለባቸው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የመድሃኒት ማዘዣ ሳያስፈልግ ናሎክሶን/naloxone ሊያገኙ እንደሚችሉ እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ስልጠና ማግኘት ይችላሉ።  ስለ ናሎክሰን/naloxone አጠቃቀም ስልጠና ከፈለጉ በዚህ ሊንክ መመዝገብ ይችላሉ።የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ናሎክሰን/naloxone በነጻ ለማግኘት ከፈለጉ DHHS Harm Reduction Services በስልክ ቁጥር 240-777-1836 መደወል ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በማህበረሰባችን ውስጥ ስላለው ህገወጥ fentanyl ምን እያደረገ ነው?
MCPS ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከአደንዛዥ እፅ-ነጻ የትምህርት ቤት አካባቢ፣ተማሪዎችን እና ሁሉም ማህበረሰባችን ውስጥ ስኬታማነታቸውን እና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የሚሰሩትን የመደገፍ ተልእኳችን ላይ ቁርጠኛ ነው። የትምህርት ቤቶች የጤና መኮንን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ክፍል (DHHS) እና ሌሎች የማህበረሰብ አጋሮች ጋር "Montgomery Goes Purple initiative" ማህበረሰብ አቀፍ ጥረቶችን ለማዳበር በቅርበት እየሰራ ነው። በቅድሚያ መከላከል፣ ጉዳትን መቀነስ እና ህክምና በመሳሰሉት እነዚህ ጥረቶች የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀምን እና የአዕምሮ ጤናን በሰፊው የሚመለከቱ እና እንዲሁም በህገ-ወጥ fentanyl ልዩ ችግሮች ላይ የሚያተኩሩ ተነሳሽነቶችን ያካትታሉ። የጋራ ግባችን በት/ቤቶች ውስጥ የተመሰረቱ ፕሮግራሞች ከአካባቢያዊ እና ካውንቲ አቀፍ ጥረቶች ጋር እንዲዋሃዱ ማድረግ ነው፣ ይህም በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ልጆች እና ቤተሰቦች የሚደርስ ነው። 

የኦፒዮይድ ቀውስ በአገር አቀፍ ደረጃ እና እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ አስከፊ ተጽእኖ እያሳደረ ስለሆነ፥ ሁሉም ሰው ይህን ወረርሽኝ በመዋጋት ረገድ የራሱን ሚና መጫወት ይኖርበታል። ወጣቶቻችንን እና ቤተሰቦቻችንን ለመጠበቅ እና ለወደፊት ጤናማ ህይወት እንዲኖራቸው ለመደገፍ ይህንን እድል በጋራ እንስራበት።

ከልብ

Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer

ተጨማሪ መረጃዎች/መገልገያዎች

ሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ሜሪላንድ፦

"Montgomery Goes Purple" - MGP የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ የማህበረሰብ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀምን እና ማገገምን በተመለከተ ለመላው ማህበረሰብ ትምህርት፣ ግብዓቶችን እና ድጋፎችን ይሰጣሉ። ከጥምረቱ የሚፈልጓቸውን ግብአቶች/ሪሶርሶች ይምረጡ፦

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለታዳጊዎች የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም ሕክምና አቅራቢዎች ዝርዝር (ተጨማሪ ግብዓቶች/ሪሶርሶች SAMHSA's Behavioral Health Treatment Services Locator) በኩል ሊገኙ ይችላሉ።

ለወላጆች ወይም ለልጆች ተንከባካቢዎች ወይም ለወጣቶች ከአእምሮ ጤና፣ ከአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም ወይም ከጋራ ተግዳሮቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚመለከት የቤተሰብ ድጋፍ ቨርቹወል ስብሰባዎች

የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ’

"የሚያስከትሉትን ስጋቶች ይወቁ" Opioid Resource Center - ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የሚሰጡ ትምህርቶች፣ አገልግሎቶች እና ሌሎች ግብአቶች/ሪሶርሶች።

የልጆች እና ጎረምሶች የምርመራ/የግምገማ አገልግሎቶች (CAAS፣ ቀደም ሲል SASCA ተብሎ የሚጠራው) - ዕድሜያቸው 18 ዓመት በታች ለሆኑ ነዋሪዎች የአእምሮ ጤና/የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም ምርመራዎችን ይሰጣል።  ቀጠሮ ለመያዝ 240-777-4000 ይደውሉ።

BTheOne - ከአእምሮ ጤና ወይም ከአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም ጋር የሚታገሉ ጓደኞችን እና የሚወዷቸውን ሰዎች እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ለታዳጊ ወጣቶች ተስማሚ መረጃ። ቀውስ እና የማቀንቀን መርጃዎችን ያካትታል።

የጉዳት ቅነሳ አገልግሎቶች/Harm Reduction Services- ነፃ የትምህርት እና የጉዳት ቅነሳ አቅርቦቶችን ለህብረተሰቡ መስጠት፣ የናሎክሶን/naloxone እና የስልጠና ተደራሽነት፣ የፈንታኒል/fentanyl መመርመሪያ እና ሌሎች የጉዳት ቅነሳ አቅርቦቶችን እና ከአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ጋር ለሚታገሉ ሪፈራልዎችን ይሰጣል። 240-777-1836 ይደውሉ ወይም

overdoseresponseprogram@montgomercountymd.gov ኢሜይል ያድርጉ።
"Parent CRAFT" በሜሪላንድ ለሚኖሩ ወላጆች እና ሌሎች ተንከባካቢዎች በአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ዙሪያ ታዳጊዎችን ለመደገፍ የሚያስችል ክህሎትን ለመማር ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የሚሰጥ ነፃ የቪዲዮ ስልጠና ነው።

የሜሪላንድ ኢንሹራንስ አስተዳደር - ለአእምሮ ጤና እና ለአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኞች ህክምና የጤና መድን ሽፋን መረጃ ይሰጣል። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይህንን እንክብካቤ በአብዛኛው እንዲሸፍኑ በህግ ይገደዳሉ። ተጨማሪ መረጃ Parity at 10 ድር ጣቢያ ላይ ይገኛል፤ በዚህ ምክንያት ህክምና ለማግኘት ከተቸገሩ ግለሰቦች Legal Action Center ማነጋገር ይችላሉ።

ድንገተኛ/የአደጋ ጊዜ መርጃዎች/ሪሶርሶች፦

988: The Suicide and Crisis Lifeline (formerly known as the National Suicide Prevention Lifeline) - Counselors offer confidential services 24/7 by phone by calling 988, or by web chat or SMS text. 25 ዓመት በታች ለሆኑ LGBTQ+ ሰዎች ልዩ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ 24 ሰዓት የቀውስ ማዕከል - 24/7 በአካል ወይም በቴሌፎን ለሁሉም ቀውሶች፣ ለሁለቱም የአእምሮ ህመም እና ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ድጋፎች ይኖሩታል። አገልግሎቶቹ የአደጋ ጊዜ ቀውስ ግምገማዎችን የሚያደርግ ተንቀሳቃሽ ቀውስ ገምጋሚ ቡድንን ያካትታሉ።ወደ ቀውስ ማእከሉ 240-77-4000 ይደውሉ፥ ወይም በአካል አገልግሎት ለማግኘት 1301 Piccard Drive, Rockville, MD 20850 ይፈልጉ። አገልግሎቶቹ በተለያዩ ቋንቋዎች እና በሁሉም እድሜ ላሉ ነዋሪዎች ይገኛሉ።
የሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት ከመጠን በላይ በተወሰደ አደንዛዥ እፅ የመጠቃት ምላሽ ፕሮግራም/Maryland Department of Health Overdose Response Program" Naloxone እንዴት መጠቀም እንደሚቻል" - ኦፒዮይድ ከመጠን በላይ መውሰድን እና ስለ naloxone የቪዲዮ ስልጠናን ያካትታል።

የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ዴቪስ፣ ሜዲካል ሴንተር፡ “ከመጠን በላይ ከተወሰደ የናሎክሶን ኪት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል” - ምቹ እና ተንቀሳቃሽ ባለአንድ ገጽ (ሁለት ጎን ያለው) ከመጠን በላይ መወሰዱን እንዴት መለየት እና ስለ ናሎክሶን/naloxone አጠቃቀም።

ጠቅላላ ትምህርት፡-

Children’s National Hospital - “Rainbow Fentanyl: The Trending Drug Parents Need to Know About” by Child and Adolescent Addiction Psychiatrist Dr. Kaliamurthy.

American Academy of Pediatrics’ Substance Use Resource Page - “The Opioid Epidemic: How to Protect Your Family”; “Talk to Your Teen About Drugs - And Keep Talking”; “When Teens Use Drugs: Taking Action”.

The CDC’s Opioid Resource Center includes specific information about fentanyl and other synthetic opioids, overdose prevention, and the emergency medicine naloxone (Narcan).

One Pill Can Kill , an educational campaign of the United States Drug Enforcement Administration - “What Every Parent and Caregiver Needs to Know about FAKE PILLS”; “Counterfeit Pills Fact Sheet”

ribbon Montgomery Goes Purple ribbon

community partners county partners


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools