Oct. 27, 2021

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ በቤት ውስጥ ጭምብል የማድረግ ትእዛዝን እያነሳ ነው ይህም ከሐሙስ፣ ኦክቶበር 28፣ከ 12፡01 a.m. ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። ነገር ግን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የጭምብል አጠቃቀም ፖሊሲ ላይ ምንም ለውጥ አልተደረገም።

የክትባት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ሁሉም የ MCPS ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ጎብኚዎች በትምህርት ቤት ህንፃዎች እና ቢሮዎች ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። ይህ ውሳኔ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል እና የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ፣ እንዲሁም የአካባቢ የጤና ባለሥልጣናት መመሪያዎችና ምክሮች ጋር የተገናዘበ ነው። በተጨማሪም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በትምህርት ቤት አውቶቡሶች ላይ ጭምብል (ማስክ) እንዲጠቀሙ ይጠበቅባቸዋል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ከቤት ውጭ አያስፈልግም፣ ነገር ግን ያልተከተቡ ግለሰቦች ማስክ (ጭምብል) እንዲጠቀሙ በጥብቅ ይመከራል።

የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ ስለሚያሳዩት ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools