Community Update

ጃኑወሪ 7, 2022

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

ይህንን የምንጽፈው በፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎች ምክንያት ትምህርት ቤቶች በአካል ከሚማሩበት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገራቸውን በሚመለከት ውሳኔዎች እንዴት እንደሚሰጡ የተደረገውን ለውጥ ለማሳወቅ ነው። የወረርሽኙ ስርጭት ሁኔታ ለብዙ የማህበረሰብ አባላት ስጋት መፍጠሩን ከቤተሰቦች፣ከተማሪዎች እና ከሰራተኞች ሰምተናል እና ያሉትን ስጋቶች ሁሉ እንገነዘባለን።
እነዚህ ማሻሻያዎች የተደረጉት ከሜሪላንድ ስቴት በተሰጡት የጤና ጥበቃ መመሪያዎች መሠረት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለመሸጋገር አግባብ ባለው አጠቃቀም ላይ ተመሥርቶ ነው - ስለሆነም MCPS በመላ አገሪቱ ያሉ ትላልቅ የትምህርት ተቋማት ት/ቤቶችን ከኮቪድ ጋር በተያያዙ ተግዳሮቶች ምክንያት ምን ያህል ደህንነታቸውን እየጠበቁ እንደሆነ ካላቸው አሠራር ጋር በማገናዘብ ነው። እኛ እነዚህን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በምንዳስስበት ጊዜ የማህበረሰባችንን ትዕግስት እና ጽናት እናደንቃለን።

የሜሪላንድ ስቴት በአሁኑ ጊዜ በአካል የሚደረግ ትምህርትን ለማገድ ማንኛውንም አውቶማቲክ ቅስቀሳ ወይም ገደብ አይመክርም። ስለዚህ፣ MCPS ከአሁን በኋላ 5% ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ንክኪ የሌላቸው ተማሪዎች እና ሰራተኞችን ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለማሸጋገር በ14-ቀን ጊዜ ውስጥ ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ያላቸው ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ምክንያት አድርጎ አይጠቀምም።

ወደፊት፣ MCPS እና የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ክፍል (DHHS) የትኛውም ትምህርት ቤት ለተወሰነ ጊዜ ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር ካለበት ለማወቅ ትምህርት ቤቶችን እንደየሁኔታቸው ክትትል/ግምገማ ይደረጋል። ከግምት ውስጥ የሚገቡት ነገሮች ፖዚቲቭ መሆናቸው የተረጋገጡ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ቁጥር መጨመር፣ በኳራንቲን ያሉ ተማሪዎች ብዛት፣ ከኮቪድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የቀሩ ሰራተኞች ብዛት፣ እና በትምህርት ቤት ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ደረጃ ይታያል።

የኮቪድ-19 ኬዞችን መለየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ወሳኝ እርምጃ ሆኖ ይቀጥላል። ማንኛውም ተማሪ የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ወይም ምልክቱ ከጀመረበት ለ10 ቀናት መነጠል ይኖርበታል።

በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ፈጣን የምርመራ ኪቶች ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ይሰራጫሉ። እነዚህ ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ ምርመራዎች በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ያሳያሉ። ፖዚቲቭ ኬዞችን በፍጥነት ይለያሉ፣ የኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ግለሰቦችን እንዲገለሉ ማድረግ በትምህርት ቤቶች እና በቢሮዎች የቫይረሱን ስርጭት የበለጠ ይቀንሳል።

ተማሪዎች እነዚህን ምርመራዎች እቤት ውስጥ እንዲያደርጉ ወላጆች እንዲረዷቸው እና የልጃቸው ምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ወይም ኔገቲቭ እንደሆነ የMCPS COVID-19 ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽን በመጠቀም ለት/ቤት እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። ከትምህርት ቤቶች የሚሰራጩትን ፈጣን የምርመራ እቃዎች ሲጠቀሙ ወላጆች ሁሉንም ፖዚቲቭ እና ኔገቲቭ ውጤቶችን ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። (ወላጆች ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ የሚያገኟቸውን ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶች ማሳወቅ አለባቸው።)

በትምህርት ቤቶቻችን እና በማህበረሰቡ ውስጥ በኮቪድ-19 ሁኔታዎች መጨመር ላይ ትልቅ ስጋት መኖሩን እንገነዘባለን። እባክዎ እነዚህን ስጋቶች እንደምንረዳ እና ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ እንዲኖር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናችንን ይወቁ።

ከአክብሮት ጋር፣

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools  
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

James Bridgers, Ph.D.
ጄምስ ብረገርስ (ዶ/ር)
Acting Chief Health Officer
ጊዜያዊ ዋና የጤና ጥበቃ ኃላፊ
የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ

 

ማሳሰቢያ፡ MCPS በመደበኛነት የሀሙስ የኢሜል ወቅታዊ መረጃ በዚህ ሳምንት ለማህበረሰቡ የተላከው እነዚህ አስፈላጊ ለውጦች እየተጠናቀቁ ባሉበት ወቅት ነው። ለማህበረሰቡ በመደበኛነት የምናስተላልፈው ወቅታዊ መረጃዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools