ሰኞ፣ ጃኑወሪ 3 ሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደገና ይከፈታሉ

ዲሴምበር 30/2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ሰኞ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የምንዘጋጀው፣ አራት የማህበረሰባችንን “ጥያቄዎች” ይዘን ነው። በተቻለ መጠን ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ ተማሪዎቻችንን ለማገልገል ቁርጠኝነት አለን፣ ነገር ግን የእርስዎንም እገዛ እንፈልጋለን። እባክዎ የእርስዎን ድርሻ ይወጡ።

  • ኮቪድ የተያዙ ካሉ ሪፖርት ማድረግዎን ይቀጥሉ።
    የእርስዎ ልጅ የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነ፣ እባክዎ ይህንን ቅጽ በመጠቀም ለ MCPS ሪፖርት ያድርጉ። ከሰኞ፣ ጃንዋሪ 3 ጀምሮ መረጃውን በኤሌክትሮኒክስ ማስገባት ካልቻሉ ወደ ልጅዎ ትምህርት ቤት መደወል ይችላሉ።
  • ከተቻለ ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሱ(ሷ) በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ ይ(ት)ውሰድ/ይውሰዱ።
    ልጆችዎን ዬት እና እንዴት እንደሚመረመሩ ለማወቅ የእርስዎን የጤና እንክብካቤ ሰጪ፣ የአካባቢ ክሊኒክ፣ ፋርማሲ ወይም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) ይጠይቁ።
  • ህጻናት ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ካላቸው ቤት ያቆዩዋቸው እና የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ።
    ምርመራ ማድረግ ተማሪዎች ህመማቸውን ወደሌሎች እንዳያስተላልፉ መደረግ ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው። እባክዎ ሲታመሙ እቤት ያቆዩዋቸው እና ለኮቪድ-19 ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያድርጉ።
  • ለምርመራ አዎ ይበሉ
    ወላጆች በትምህርት ቤት ለሚደረግ ምርመራ ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው እና ይህንን ቅጽ በመሙላት ፈቃድ መስጠት ይችላሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ እባክዎ የእኛን "Say Yes to the Test" ድረ ገጽ ይጎብኙ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና በመላ አገሪቱ የኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ኬዞች (በኮቪድ የመያዝ ሁኔታዎች) እየጨመሩ መሆናቸውን እንገነዘባለን። ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ለመክፈት ውሳኔ የተደረገው ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት (DHHS) ጋር በጥንቃቄ ከታሰበበት እና ቀጣይነት ያለው ትብብር እንደሚደረግ ከታመነበት በኋላ ነው። የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን፣ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ አባላትን ደህንነት ለማረጋገጥ በምንሰራበት ጊዜ በሚቀጥሉት ቀናት የኮቪድ ስርጭትን ለመከላከል ተጨማሪ ርምጃዎችን ተግባራዊ እናደርጋለን።

ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ፈጣን የቤት ውስጥ መመርመርያ እቃዎች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተዳደር በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በቤት ውስጥ ፈጣን የምርመራ ዕቃዎችን እንደሚያቀርብ ዛሬ ጥዋት ተረድተናል። ሁሉም ቤተሰቦች ለልጆቻቸው ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፥ ከዚያም ማንኛውንም ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ያሳውቃሉ። ስለእነዚህ የምርመራ መሣሪያዎች ስርጭት ተጨማሪ ዝርዝሮች በሚቀጥለው ሳምንት እንገልጻለን።

ለሠራተኞች የሚሰጥ ጭምብል
ሁሉም የሥራ ባልደረቦች ጃኑወሪ 3 በሚሆንበት ሳምንት ውስጥ የ KN-95 ጭንብል ይሰጣቸዋል።

በትምህርት ቤት የተማሪዎች የኮቪድ ምርመራ ይቀጥላል።
ምልክት ለሌላቸው ተማሪዎች የሚደረገውን የኮቪድ ምርመራ መጠን እንጨምራለን እና ከፍ ያለ መጠን በኮቪድ የተያዙ ፖዚቲቭ ሁኔታዎች ባላቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን። በተጨማሪም፣ ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ በትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ማቅረባችንን እንቀጥላለን - በት/ቤት የጤና ክፍሎች አማካይነት ምልክት ላላቸው ተማሪዎች ፈጣን ምርመራ እና ምልክት ለሌላቸው ሳምንታዊ የማጣሪያ ምርመራዎች ይደረጋሉ።

እስካሁን ያሉት የኳራንቲን መመሪያዎች አሁንም በሥራ ላይ ናቸው።
በሜሪላንድ የጤና መምሪያ (MDH) እና DHHS መመሪያ መሰረት፣ MCPS ኖቨምበር ላይ የተገለጸውን ተመሳሳይ የኳራንቲን መመሪያዎች መጠቀሙን ይቀጥላል። ከሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት ተጨማሪ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ። ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ያላቸው ግለሰቦች ምልክቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ለ10 ቀናት ወይም ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ቀናት ኳራንቲን ማድረግ/ራሳቸውን አግልለው መቆየታቸውን መቀጠል አለባቸው። የበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከል (Centers for Disease Control) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ስለ ኳራንቲን (ራስን ማግለል) መመሪያ በተመለከተ በሚዲያ መግለጫ ቢያወጣም፣ የሜሪላንድ ጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት (MDH) በእነዚህ መመሪያዎች ላይ የተደረጉትን ለውጦች አልተቀበለም።

ወደ ቨርቹወል ትምህርት የመሸጋገር መስፈርቶች
በየቀኑ የወረርሽኙን ስርጭት ሁኔታ መከታተል እንቀጥላለን። ቀደም ብለን እንደገለጽነው፣ 5 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት በኮቪድ የተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች (ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ 10 ግለሰቦች) በ 14-ቀን ጊዜ ውስጥ ፕዚቲቭ የምርመራ ውጤት ካላቸው፣ ት/ቤቱን ለ14 የካላንደር ቀናት በመዝጋት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር እንዳለበት ይወሰናል። እባክዎን የ 5 በመቶው ገደብ ወዲያውኑ/በቀጥታ የትምህርት ቤት መዘጋትን እንደማያስከትል ያስተውሉ፥ ሊታሰብበት የሚገባው ዋናው ነገር በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መጠን ነው። ይህንን ውሳኔ ለማድረግ የ MCPS ዋና ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ከ DHHS ጋር ይሰራሉ፣ እና ይህ ሁኔታ ሲከሰት በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያሉ ወላጆች/አሳዳጊዎች ይነገራቸዋል።

ለ 2022 የመጀመሪያው የትምህርት ቀን ስንዘጋጅ ስለምታደርጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

ጠቃሚ መረጃዎች



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools