banner

ንቁ ሁን! ኮቪድ-19 እስካሁን ከእኛ ጋር ነው።

ዲሴምበር 21/2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

በረርሽኙ የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያመጣው አደጋ ከባድ ሆኖ ይቀጥላል በምላሹ፣ ማህበረሰባችን ነቅቶ እንዲጠብቅ እየጠየቅን እና የራስዎን ደህንነት እና ጤንነት ለመጠበቅ እንዲረዳዎት ከአካባቢ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት የሚሰጠውን መመሪያ መከተሉን እንዲቀጥሉ እንጠይቃለን። ክትባቶች፣ የፊት መሸፈኛዎች እና ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀላል፣ እና አስፈላጊ እርምጃዎችን በመውሰድ የወረርሽኙን መስፋፋት ቁጥር ዝቅተኛ ለማድረግ እጅግ የሚረዳ ነው።

ጠቃሚ-ማሳሰቢያ፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በአካል ለመማር ክፍት እንደሆኑ ይቆያሉ በወረርሽኙ የተጠቂ ቁጥሮች እየጨመረ ቢሆንም፣ በአካል የመማሪያ አካባቢን ክፍት አድርጎ መቀጠል ለተማሪዎቻችን የሚሻል እርምጃ ነው። የክረምቱን (ዊንተር) ዕረፍት ተከትሎ፣ ጃኑወሪ 3 በታቀደው መሰረት ሙሉ በሙሉ በአካል ወደመማር ለመመለስ አስበናል።

የወረርሽኝ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡-
በብዙ የአገሪቱ አካባቢዎች ከምናያቸው አዝማሚያዎች ጋር ሲነፃጸር በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ እየጨመረ ነው። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ በ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች መካከል ያለው የኮቪድ-19 ሁኔታ ቁጥር እየጨመረ ነው። በዲሴምበር 1 እና ዲሰምበር 19 መካከል፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 1,196 በኮቪድ የተያዙ ሁኔታዎች ተመዝግበዋል። በንጽጽር ከኦገስት 31 እስከ ኖቨምበር 30 በድምሩ 1,155 በኮቪድ የተያዙ ሁኔታዎች ነበሩ–ይህም ማለት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዲስትሪክቱ በትምህርት አመቱ ከነበሩት ሶስት ወራት የበለጠ በወረርሽኝ የተያዙ ሁኔታዎች አጋጥሞታል ማለት ነው። ይህ እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልግ አስደንጋጭ አዝማሚያ ነው።

MCPS ትምህርት ቤቶችን ይዘጋል?
ሁሉንም የ MCPS ትምህርት ቤቶች የመዝጋት እቅድ የለንም። የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ በሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት (DHHS) እና በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) በተገለፀው መሰረት በተናጠል ትምህርት ቤቶች በሚከሰተው ወረርሽኝ ዙሪያ የ DHS መመሪያን እንከተላለን። ከጃኑወሪ ወር ጀምሮ፣ 5 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት ተዛማጅ ያልሆኑ ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች (ቢያንስ 10 ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች) በ14 ቀናት ጊዜ ውስጥ በበሽታው የተያዙ ከሆነ፣ DHHS እና MCPS ት/ቤቱ መሆን እንዳለበት ለመወሰን አብረው ይሰራሉ። ለ 14 ቀናት ይዘጋል እና ተማሪዎቹ ወደ ቨርቹወል ትምህርት ይሸጋገራሉ።

በኳራንቲን ወቅት መደረግ ያለበት ዝግጅት፦
መመርያው ተማሪው(ዋ)፣ የትምህርት ክፍል፣ ወይም ት/ቤቱ ኳራንቲን (ተለይተው መቆየት) ካለባቸው እና በጊዜያዊነት ቨርቹወል የሚማሩ ከሆነ ተዘጋጅቶ መጠበቅ አስፈላጊ ነው። በዊንተር/ክረምት እረፍት ጊዜ ተማሪዎች ማድረግ ያለባቸው፦

 • ክሮምቡክ እና ቻርጅ ማድረጊያ እቤታቸው መውሰድ አለባቸው
 • መጻሕፍት፣ ዎርክቡክስ/የመሥርያ መጻፎቻቸውን እና ከአስተማሪዎች የሚነገራቸውን ሌሎች ቁሳቁሶችን ሁሉ ወደቤታቸው መውሰድ ይኖርባቸዋል
 • በኦንላይን የ MCPS ይለፍ ቃል እንዴት መክፈት/መጠቀም እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው
 • የተማሪዎች ዙም Zoom for Students
 • የተማሪn አካውንት መክፈት Student Accounts and Access 
 • የወላጅ/ሞግዚት አካውንት መክፈት Parent/Guardian Accounts and Access
 • Clever አማካይነት myMCPS Classroom መክፈት Accessing myMCPS Classroom via Clever
 • የማህበረሰብ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ፖርታል Community Tech Support Portal 
 • ይህንን ኢሜይል - communitytechsupport@mcpsmd.org

በኮቪድ በሽታ የተያዙ ሁኔታዎችን ሪፖርት ማድረግ መቀጠል፦
ጃኑወሪ 3 ወደ /ቤቶች ለመመለስ አካባቢያችን ጤናማ እንዲሆን መጠበቅ ማለት በበሽታው የተያዘ() ተማሪን ሁኔታ ማወቅ እና ምላሽ የመስጠት ጥንቃቄ መውሰድን ያመለክታል። በዊንተር/ክረምት እረፍት ጊዜ የእርስዎ ልጅ ኮቪድ-19 ከያዘው ወይም ከያዛት እባክዎ ይህንን  MCPS ይግለጹ/ሪፖርት ያድርጉ። ሪፖርት ለማድረግ የሚችሉት (using this electronic form) ይህንን የኤሌክትሮኒክስ ቅጽ በመጠቀም ነው።

እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልግ ጥሪ፡-
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ከተማሪዎቻችን እና ከሰራተኞቻችን ብዙ ነገሮች ተጠይቀዋል። እንደ ተቋም ይህን ወረርሽኝ በመጋፈጥ ላደረጋችሁት ነገር ሁሉ እናመሰግናለን። በማህበረሰባችን ሁሉም ሰዎች ባደረጉት ጥረት በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል ወደ መማር ለመመለስ ችለናል። ነገር ግን፣ እየጨመረ ያለው በወረርሽኝ የመጠቃት ቁጥሮች መጨመር በአትሌቲክስ እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። ይህ አስደንጋጭ አዝማሚያ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የምንገኝ ሁላችንም የዚህን አሳሳቢነት እንድንገነዘብ እና ይህን ቀላል የጤና እና የደህንነት ስትራቴጂዎች ዝርዝር በመከተል ንቁ እንድንሆን ያደርጋል።

ማድረግ የሚችሉት እነዚህ ናቸው፡-

 • ክትባት ይውሰዱ። የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ ስለሆነ እድሜአቸው 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ይሰጣል።
 • booster shot ይውሰዱ– እርስዎ በበቂ ሁኔታ መከላከል እንደሚችሉ እርግጠኛ ለመሆን ሶስተኛው ዙር booster shot አሁን 16 ዓመት እድሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይሰጣል።
 • በ MCPS ህንፃ ውስጥ ወይም በህዝባዊ ሕንፃዎች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ በአፍንጫዎ እና በአፍዎ ላይ የፊት መሸፈኛ ጭምብል ያድርጉ።
 • ከመመገብዎ በፊትና በኋላ አይንዎን፣ አፍንጫህን ወይም አፍዎን ከመንካትዎ በፊት እና በኋላ እጅዎን አዘውትረው ይታጠቡ።
 • ለምርመራ አዎ ይበሉፍቃድ ይስጡ በ MCPS ትምህርት ቤቶች የዘፈቀደ እና ፈጣን የኮቪድ-19 ማጣሪያ ፕሮግራሞች። ይህ በሽታው ያለባቸውን ለመለየት እና በኳራንቲን ያሉ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
 • ከሰዎች ጋር ሲሆኑ ከቤት ውጭ ይዝናኑ። ቤት ውስጥ ከሌሎች ጋር ከተገናኙ፣ የተጨናነቁ እና በቂ አየር የሌላቸውን ቦታዎች ያስወግዱ። ከበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል ተጨማሪ ምክሮችን ይመልከቱ
 • ለመጓዝ እቅድ አለዎት? እንዴት በደህና ማድረግ እንደሚችሉ CDC ምን እንደሚመክር ይወቁ።

ብዙዎቻችን የወረርሽኙ ድካም እየተሰማን ነው። እስካሁን ረጅም መንገድ ተጉዘናል። ነገር ግን የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ የረዱትን የመከላከል ባህሪያትን መለማመዳችንን መቀጠል ወሳኝ ነው።

ባለፉት 20 ወራት ውስጥ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ እንዴት ወረርሽኙን ለመከላከል ስልቶችን እንደተጠቀመ እና ክትባቱን በከፍተኛ ቁጥር እንደተቀበለ ማየት በጣም አስደሳች ነበር። ቀላል ባይሆንም ወደ ፊት መጓዛችንን ቀጥለናል። የህብረተሰባችንን ደህንነት የመጠበቅ ጥረታችንን ማስቀጠል አለብን። ነቅተን መጠበቅ አለብን! ይህንን በጋራ ማድረግ አለብን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) በወረርሽኙ ወቅት በመተባበር የተገኙት ምክሮቻቸው MCPS ን ላለፉት 21 ወራት መርተዋል። ለቤተሰቦች ወይም ለሰራተኞች መመሪያው ከተቀየረ፣ MCPS ለውጦቹን በጊዜው ያስተላልፋል።

መልካም ጤናማ በዓል የምታከብሩበት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
 

Dr. Monifa B. McKnight
Interim Superintendent
Montgomery County Public Schools

Dr. James Bridgers
Acting Chief Health Officer
Montgomery County Department of Health and Human Services

ጠቃሚ መረጃዎችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools