የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ መልእክት፦ የመቆየት ምርመራ ፕሮግራምን "Test-to-Stay Program" ለማካተት የተሻሻለ የምርመራ እና የኳራንቲን መመሪያ

November 11, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ኦክቶበር የመጨረሻ ሳምንት የሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት (MDH) እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ስለ ኮቪድ-19 ለት/ቤቶች የተሰጠውን መመሪያ አሻሽለዋል።
አዲሱ መመሪያ ተማሪዎች በኮቪድ-19 መያዙ(ዟ) ከተረጋገጠ ተማሪ ጋር በቅርብ ግንኙነት ንክኪ ከተጋለጡ በኋላ በትምህርት ቤት እንዲቆዩ የሚያስችላቸውን ሶስት የተሻሻሉ የለይቶ ማቆያ አማራጮችን ያካተተ ሲሆን ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ተማሪዎቹ በተጋለጡበት ወቅት ጭምብል አድርገው ከሆነ ነው። ሦስቱ የተሻሻሉ የኳራንታይን አማራጮች፦ የመቆየት-መመርመር፣ ሳምንታዊ የማጣሪያ ምርመራ፣ እና ትክክለኛ እና ወጥነት ያለው በሚገባ የተገጣጠሙ ጭምብሎችን መጠቀም ናቸው። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት (DHHS) በተሰጡት ምክሮች መሰረት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በየሳምንቱ የሚያደርገውን የማጣሪያ ምርመራ በተሻሻለው የኳራንቲን አማራጭ መመሪያ መሠረት እየተጠቀመ ነው። ይህ የተሻሻለው የኳራንታይን አማራጭ በዚህ ሳምንት የተተገበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል ኳራንቲን እንዲቆዩ የሚደረጉ ተማሪዎች ቁጥር ቀንሷል።

የመቆየት ምርመራ ፕሮግራም፣ በ DHS እና MCPS እንደታቀደው ተማሪዎች በኮቪድ-19 መያዙ(ዟ) ከተረጋገጠ ሌላ ተማሪ ጋር በቅርብ ንክኪ ከተጋለጡ በኋላ ለአምስት የትምህርት ቀናት በየጧቱ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ይሰጣል። በየቀኑ ጠዋት ፈጣን ምርመራ እየተደረገላቸው የምርመራ ውጤቱ ኔገቲቭ እስከሆነ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ለቀሪው የትምህርት ቀን ክፍል ውስጥ እንዲማሩ ይፈቀድላቸዋል። በመጀመሪያ DHHS እና MCPS ለመጠቀም አቅደውት የነበረው፤ ተማሪዎች በምሣ ሠዓት በኮቪድ-19 መያዙ(ዟ) ከተረጋገጠ ተማሪ ጋር በቅርብ ንክኪ ከተጋለጡ የማቆየት ምርመራ ፕሮግራም "Test-to-Stay Program" ለማድረግ ነበር። ነገር ግን ከ MDH እና MSDE እንደተገለፀው፤ በተሻሻለው የኮቪድ-19 መመሪያ መሠረት የመቆየት ምርመራ ፕሮግራም "Test-to-Stay Program" ለዚህ አላማ ጥቅም ላይ አይውልም። በትላንትናው ቀን MDH፣ ከ DHHS ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ የመቆየት ምርመራ ፕሮግራም "Test-to-Stay Program" በዚህ አይነት እንዲቀጥል ደግፏል። ስለሆነም፥ በ 2ኛው የማርክ መስጫ ጊዜ ቀስ በቀስ ወደ በርካታ ትምህርት ቤቶች የማስፋፋት ግብ ይዘን ከ "Thanksgiving" የምስጋና ዕረፍት በፊት በትንሽ ቁጥር ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመቆየት ምርመራ ፕሮግራምን ከ DHS ጋር አብረን እንሰራለን። ፕሮግራሙ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ MDH፣ DHHS እና MCPS በጅምሩ ጊዜ መረጃዎችን በሙሉ ይገመግማሉ።

ይህ መረጃ ዛሬ በረፋዱ ላይ በ MCPS ድህረ ገጽ ላይ ይገለጻል። ወቅታዊ መመሪያዎችን ተከትለን ትምህርት ቤቶቻችንን በከፍተኛ ደረጃ ለመደገፍ ከካውንቲ እና ከስቴት አጋሮቻችን ጋር በምንሰራበት ጊዜ ትዕግስትዎን እና ግንዛቤዎን እናደንቃለን።

ከሰላምታ ጋር

 

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools