elementary school students

ከ 5 እስከ 11 አመት እድሜ ላላቸው ብቁ ህጻናት የኮቪድ ክትባት አሁን ይኖራል።

November 5, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ፣ የሆሊ ክሮስ ሆስፒታል እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) ከ 5 እስከ 11 አመት ለሆኑ ተማሪዎች የኮቪድ-19 የክትባት ክሊኒኮችን ለማስተናገድ በመተባበር ላይ ናቸው። እነዚህ ክሊኒኮች በስድስት ትምህርት ቤቶች እና በአራት የ DHHS ጣቢያዎች ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 6 ይጀምራሉ። MCPS፣ Holy Cross Hospital እና DHHS የክትባት ክሊኒኮችን በሚከተሉት ትምህርት ቤቶች ያስተናግዳሉ፦
(የኮቪድ-19 የክትባት ክሊኒክ ጣቢያዎች)
በስራ ቀናት እና ቅዳሜና እሁድ ብዙ ቦታዎች ክፍት ይሆናሉ።
በተቻለ መጠን ብዙ ቤተሰቦችን ለመድረስ እነዚህ ቦታዎች በየሳምንቱ ይለወጣሉ። ቤተሰቦችን ወደ ክሊኒኩ ቦታዎች ለመውሰድ የ MCPS አውቶቡሶች በየአካባቢው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። የበለጠ ግንዛቤ እዚህ ያግኙ፦
ልጅዎን እዚህ ያስመዝግቡ፦ https://www.montgomeryschoolsmd.org/Coronavirus/Vaccinations። ለእያንዳንዱ የክትባት ቦታ የሚኖረው የክትባት መጠን የተወሰነ ስለሆነ ሁሉም ክሊኒኮች መጀመሪያ ቀጠሮ ያስፈልጋቸዋል። ወላጆች/አሳዳጊዎች የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት የልጃቸውን የሕፃናት ሐኪም ማነጋገር ይችላሉ። ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ህጻናት 2/3ኛው የክትባት መጠን በፋርማሲዎች፣ በህፃናት ሐኪሞች እና በሌሎች የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች የሚቀርብ ሲሆን 1/3ኛ (አንድ ሶስተኛ) የሚሆነው በጤና ዲፓርትመንት አማካይነት ይሰጣል። ነዋሪዎች ክትባቶችን እየሰጡ ያሉትን በርካታ ምንጮች እንዲጠቀሙ እናበረታታለን።
የኮቪድ-19 ክትባት ለቤተሰቦች የሚሰጠው በምርጫቸው (በፍላጎታቸው) ስለሆነ በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ለመከታተል አስገዳጅ አይደለም፤ ነገር ግን ከ 5 እስከ 11 አመት ለሆኑ ህጻናት ክትባት እንዲወስዱ በጣም ይመከራል።
የኮቪድ-19 የሕፃናት ክትባት MCPS የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተጠቀመበት ያለ አንዱ ስልት ሲሆን ይህም ተማሪዎች በየሳምንቱ ለአምስት ቀናት በትምህርት ቤት እንዲማሩ እና የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዳ ነው።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools