የማህበረሰብ ወቅታዊ መረጃ

ሴፕቴምበር 9/2021

የተወደዳችሁ የ MCPS ማህበረሰቦች

ከሴፕቴምበር 9/2021 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እርስዎ ማወቅ ያለብዎት ሰባት ጉዳዮች፦
በትምህርት ቤቶች የሚደረግ የኮቪድ -19 ምርመራ፣ ስለ ሠራተኞች ክትባት ግዴታ፣ እና ለዊንተር እና ለስፕሪንግ ስፖርቶች የተማሪዎች ክትባትን በሚመለከት የወጡ አዳዲስ መስፈርቶችን እነሆ።

  1. የተማሪዎች ማግለልን (ኳራንቲን) ለመቀነስ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይተገበራል። MCPS ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ፈጣን ምርመራዎችን ያካሄዳል። እነዚህን ምርመራዎች መጠቀም፥ እኛ ካሉን ሌሎች የጤና አጠባበቅ እርምጃዎች ጋር በመቀናጀት በርካታ ተማሪዎችን በትምህርት ቤት ውስጥ ለማቆየት ይረዳል። MCPS በዚህ ፈጣን የምርመራ ፕሮግራም ትግበራ ላይ ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) ተጨማሪ መመሪያ ስለሚቀበል በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ መረጃዎች ይተላለፋሉ።
  1. የትምህርት ቦርድ ሁሉም የ MCPS ሰራተኞች ክትባት እንዲወስዱ የሚጠይቅ የጋራ ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔው በ MCPS ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች በሕክምና ዶክተር የተረጋገጠ የሕክምና ምክንያት ከሌላቸው በስተቀር ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱበትን ማረጋገጫ እስከ ሴፕቴምበር 30/2021 እንዲያቀርቡ፥ የሁለተኛውን ዙር ክትባት የወሰዱበትን ማረጋገጫ እስከ ኦክቶበር 29/ 2021 እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። ክትባት ላለመውሰድ የሕክምና ምክንያት ከተሰጠ፥ MCPS ባወጣው መስፈርት መሠረት ሠራተኛው(ዋ) በየጊዜው የኮቪድ-19 ምርመራ መውሰድ አለበ(ባ)ት። ቦርዱ ይህን ውሳኔ የሰጠበት ምክንያት በተለይ ለክትባት ብቁ ላልሆኑ ወጣት ተማሪዎች ወረርሽኙን መከላከያ እንደ ተጨማሪ እርከን ተደርጎ ነው። በ MCPS፣ DHHS፣ እና በሌሎች የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች የሚካሄዱ ክትባት የሚሰጡ በርካታ ክሊኒኮች በካውንቲው ይገኛሉ።
  1. ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች በጥጥ መጎርጎሪያ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወን የኮቪድ-19 ምርመራ ሴፕቴምበር 13 ይጀመራል። MCPS የፈቃድ መስጫ ቅጹን  እስካሁን ድረስ ሞልተው ያልመለሱ ቤተሰቦችን ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው። ለሳምንታዊ የኮቪድ -19 ምርመራ የመጀመሪያው ምዕራፍ (Phase 1) ፕሮግራም ሴፕቴምበር 13 በሚውልበት ሣምንት ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይጀመራል። በየሣምንቱ በዘፈቀደ ከተማሪዎች ናሙና እየተወሰደ ምርመራ የሚደረግ ሲሆን የእያንዳንዱ ምርመራ ውጤት ናሙናው ከተወሰደ በኋላ ከ 24-36 ሠዓታት ውጤት ይታወቃል። በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይቻላል

  2. ተማሪዎች በዊንተር እና በስፕሪንግ ስፖርቶች ለመሳተፍ የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ አለባቸው። ከኖቬምበር 15/2021 ጀምሮ በ MCPS የአትሌቲክስ መርሃ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች በሙሉ ከመሳተፋቸው በፊት ሙሉ የኮቪድ -19 ክትባት መውሰዳቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የኮቪድ -19 ክትባት ላለመውሰድ የህክምና ምክንያት መኖሩን ፈቃድ ባለው የጤና ባለሙያ ከተረጋገጠ በአትሌቲክስ ፕሮግራም እንዲሳተፉ ሊፈቀድ ይችላል። ይህ መስፈርት ለዊንተር እና ለስፕሪንግ ስፖርት ወቅቶች ይሠራል፤ ነገር ግን በፎል ስፖርቶች ውስጥ የሚሳተፉ ተማሪዎችም ክትባት እንዲወስዱ በጥብቅ ይበረታታሉ። ክትባቶች በብዛት የእንቅስቃሴዎች መቋረጥ እንዳይኖር እና በ MCPS አትሌቲክስ ውስጥ የግለሰብ እና የቡድን ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል። ዶኩመንቶችን ስለማቅረብ በሚቀጥሉት ሳምንታት ተጨማሪ መረጃዎችን እናጋራለን። ለዊንተር ስፖርቶች ምዝገባ ኦክቶበር አጋማሽ ላይ ይከፈታል፣ እና የክትባት ማረጋገጫ ከምዝገባው ሂደት ጋር መቅረብ አለበት።
  1. MCPS ስለ ኮቪድ -19 የ DHHS ን መመሪያ ይከተላል። MCPS የኮቪድ-19 ምልክቶች ያላቸው ተማሪዎችን እና ከእነሱ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው የክፍል ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ስለማግለል (ኳራንቲን ማድረግ) የ DHHS የኮቪድ-19 መመሪያን ይከተላል። እነዚህ መመሪያዎች ሴፕቴምበር 3 ለማህበረሰቡ ተሠራጭተዋል። እንደገና ሴፕቴምበር 8 ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ኦፊሰር በግልጽ ቋንቋ ተብራርቶ ለ MCPS የተጻፈ ደብዳቤ ተላልፏል። በተጨማሪም፥ DHHS በኳራንቲን ዙሪያ ያለው መመሪያ በአጠቃላይ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ግምገማ ያደረገ ሲሆን የ CDC መመሪያዎችን የሚያሟሉ የቅርብ ግንኙነቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት ከ MCPS ሠራተኞች ጋር በቅርበት መስራታቸውን ይቀጥላሉ። ለበለጠ ግልፅ መረጃ ይህንን አገናኝ-ሊንክ ይጎብኙ

  2. በኳራንቲን ውስጥ ላሉ ተማሪዎች ትምህርት እና ድጋፍ ይሰጣል። ኳራንቲን ተገልለው ለሚቆዩ ተማሪዎች ትምህርት እንዳይስተጓጎልባቸው ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ስልቶችን ተግባራዊ ያደርጋሉ። የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ኳራንቲን በሚቆዩበት ጊዜ ከመምህራን በቀጥታ ቨርቹወል ትምህርት እና ድጋፍ ያገኛሉ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሁሉም የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ተደራሽነት ስላላቸው ከመምህራኖቻቸው ጋር ዕለት ተዕለት ቨርቹወል ይሳተፋሉ። በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የመልካም ጤንነት ቁመና ቡድኖች (Well-being teams) ድጋፍ የሚሰጡ ሲሆን ቨርቹወል በሚማሩበት ጊዜ ተማሪዎችን ክትትል ያደርጋሉ።

  3. MCPS ለተቀናጀ የትምህርት አሰጣጥ ጠንካራ ዕቅድ አዘጋጅቷል። ከሜሪላንድ ስቴት ትምህርት መምሪያ (MSDE) የትምህርት ቤት ሕንፃዎች መያዝ ከሚችሉት አቅም በማሳነስ የተማሪዎችን ቁጥር ቀንሰው እንዲያስተምሩ ከታዘዘ፥ MCPS የተቀናጀ የትምህርት አቀራረብ ዕቅድ አዘጋጅቷል። ዕቅዱ ከሠራተኞች የተገኙ ግብዓቶችን እና ከባለፈው የስፕሪንግ ወቅት የተቀናጀ ትምህርት ትንታኔን ያጠቃልላል። የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን ለሚቀበሉ ተማሪዎች፥ ስለቴክኖሎጂ ድጋፎች መረጃ፣ እና የውጤት አሰጣጥና ሪፖርት የማድረግ ፖሊሲዎችን፣ ከሌሎች ነገሮች ጋር በተጓዳኝ የሚተገበሩ ስልቶችን ያብራራል። ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቦርድን ስብሰባ እዚህ ይመልከቱ።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools