McKnight

ጁን 1/2021

የተወደዳችሁ የ MCPS ቤተሰብ አባላት

ከ 20 ዓመታት በፊት በዚህ ጊዜ፥ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመጀመሪያ ዓመት የአስተማሪነት ስራዬን እያጠናቀቅኩ ነበር። በፓርክላንድ ሚድል ስኩል "Parkland Middle School" የመጀመሪያ ዓመት እየተገባደደ ሳለ በተማሪዎቼ ኩራት ይሰማኝ የነበረ ከመሆኑም በላይ የ MCPS ማህበረሰብ አባል በመሆኔ ከፍተኛ የአመስጋኝነት ስሜት ይሰማኝ ነበር። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተጠባባቂ ሱፐር ኢንተንደንት ሆኜ ይህንን ስጽፍ ትላንት የነበረኝን ለተማሪዎቻችን ከፍተኛ አድናቆትና ከትምህርት ቤት ቤተሰቦቻችን ጋር ያለኝ ጥልቅ ግንኙነትና አክብሮት በውስጤ እየተሰማኝ ነው።

እንደ ክፍል አስተማሪ፥ የሠራተኞች ሙያ ማዳበር መምህርት፥ ረዳት ርእሰመምህርት፣ ርእሰመምህርት እና የዋና ጽ/ቤት አስተዳዳሪ— ሆኜ በ MCPS—በሠራሁበት በእያንዳንዱ ቀን ለትምህርት ሲስተማችን ስኬታማነት ቁልፉ ምን እንደሆነ ግልጽ እየሆነ የመጣው ቁምነገር፦ MCPS ከፍተኛ ስኬታማ የሆነበት ምክንያት ድንቅ ሰዎች ስላሉት ነው።

ተማሪዎቻችን ምጡቆች እና ርኅሩኅ ናቸው፤ አስተማሪዎቻችን በሙያ የተካኑና የሚንከባከቡ ናቸው፤ የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሠራተኞቻችን ባለሞያዎችና የማዕከላዊ ጽ/ቤት ሠራተኞቻችን እጅግ በጣም ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው፤ ቤተሰቦቻችንም ኢንቨስት እያደረጉ ያበረታታሉ። በተቻለን መጠን የተማሪዎቻችንን የትምህርት፣ የማኅበራዊና ስሜታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በመካከላችን ቀጣይነት ያለው ትብብር ማድረግ ይረዳናል። አብረን የምንሠራው፣ ተማሪዎቻችን ከጋራ ጥንካሬያችን የመሚነጭ ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘት እንዳለባቸው ስለምናውቅ ነው።

በትምህርት ቤታችን ውስጥ እያደግሁ ስሄድ እነዚህን ባሕርያት በተደጋጋሚ ስላየሁና የ MCPS ማኅበረሰባችን ይህንን የመደጋገፍ መንፈስ ያዳበረ መሆኑን እንድቀበል አድርጎኛል። በማስተማር ሥራ ወደ ሜሪላንድ (MCPS) ስመጣ በትምህርት አብረን ከነበርን ቡድን ጋር የቅርብ ወዳጅነትና የቤተሰብነት ትስስር መሠረትኩ፤ ይህ ቡድን ከፋይናንስ እቅድ ጀምሮ ሁሉንም ነገር አስተምሮኛል። ወዲያው መቀበላቸው ሳውዝ ካሮላይና በአካባቢያችን ባለው ትምህርት ቤት ውስጥ እናቴ የምግብ አገልግሎት ሠራተኛ ሆና በምትሠራበት ጊዜ የነበረውን የቤተሰባዊነት ትሥሥር ያስታውሰኝ ነበር። ያ በትምህርት የተገናኘነው ቡድን በጣም ከምወዳቸው አሁን ካሉትና ጡረታ ከወጡ የ MCPS ሠራተኞች—ብዙ ጓደኞች መካከል የመጀመሪያውን ስሜት የፈጠረብኝ ሲሆን፤ በተማሪዎች ላይ ባለን የጋራ እምነትና እኛ ከምንሠራቸው የግል ግንኙነቶች የተነሳ የዳበረ የወዳጅነት ስሜት ነው። በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ትምህርት፣ ተስፋና ስጋት በተመለከተ ከተደረጉት ውይይቶች የተነሳ የቤተሰባቸው አባል እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አድርገውኛል።

የቀድሞ ተማሪዎቼ ስላሳለፏቸው ስኬቶችና ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሁንም በኮሌጅና በሙያቸው እያደጉና እየተሳካላቸው መሆኑን ስሰማ ስለቀድሞ ተማሪዎቼ ያለኝ ደስታ ይቀጥላል። አስተማሪ፣ መሪ፣ ባለቤትና እናት በመሆን፣ በግል እና በሙያዬ እድገት እንዲኖረኝ በማድረግ MCPS በጋራ አንድ መንደር ገንብቶልኛል።

ያ የመጀመሪያው ዓመት እየተገባደደ ሲሄድ፥ የተማሪዎቼን ስኬት ለማክበር እና በቀጣዩ ዓመት ተማሪዎቼን በተሻለ ሁኔታ የማገልገል ዕቅድ የማዘጋጀት እድል አግኝቼ ነበር። የዚህ ዓመቱ አስቸጋሪ ሁኔታ እየተቃለለ ስለሄደ—በ MCPS ያለዎት ሚና በትምህርት ቤት ወይም በቢሮ፥ ምንም ይሁን፥ እባክዎ የተሻለ ጠንካራ ዝግጅት ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ። እረፍት ያድርጉ፣ ዘና ይበሉ፥ እና ኃይልዎን ያድሱ፤ ደክመው ያገኙት ነው!
በሚቀጥሉት ሳምንታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወደፊት እንዲያድግ ለማድረግ የሚኖረኝን ዕቅድ እንደገና እጽፍላችኋለሁ። ዘወትር ለተማሪዎቻችን ድጋፍ ስላለዎት ቁርጠኝነት አመሰግናለሁ።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Acting Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክናሂት ዶ/ር
የት/ቤቶች ተጠባባቂ ሱፐርኢንተንደንት




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools