boy in mask getting on bus

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ሜይ 18/21 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ ቦርድ የሰው ብዛት መጠን እገዳ ስለማንሳት እና ለካውንቲው ነዋሪዎች ጭምብል የመጠቀም መስፈርቶችን የማላላት አዲስ የጤና አጠባበቅ መመሪያ አጽድቋል። አዲሱ መመሪያ በሥራ ላይ የሚውለው እስከ ሜይ 28/2021 ሲሆን የጤና ጥበቃ ቦርድ መመሪያ የጊዜ ገደብ ካበቃ በኋላ ነው። እነዚህ ለውጦች ለ MCPS ምን ትርጉም እንዳላቸው ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ አራት ነገሮችን እነሆ፦

  1. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለእያንዳንዳቸው ተመራቂ ስንየሮች የምረቃ ወቅት የቲኬት ቁጥር ይጨመራል። በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሚጨመረው የቲኬት ቁጥር የሚወሰነው ካላቸው የተመራቂ ተማሪዎች ብዛት እንዲሁም በት/ቤት ግቢ ከቤት ውጪ በሚገኘው ስታዲየም ስፋት አቅም ላይ የተመሠረተ ይሆናል። በምረቃ ወቅት ስለሚያገኙት የቲኬቶች ብዛት ት/ቤቶች ለቤተሰቦቻቸው በቀጥታ ይገልጹላቸዋል።
  2. ለተማሪ ስፖርተኞችና ለተመልካቾች ከዚህ በኋላ ከቤት ውጪ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም አያስፈልግም። በተጨማሪም ከቤት ውጪ በሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ምን ያህል የሰው ብዝት መጠን መገኘት/መሣተፍ እንዳለበት ያለው ገደብ ተነስቷል። ለቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድሮች መገኘት የሚችል የሰው ብዛት መጠን 250 ነው። ስለ አትሌቲክስ ተጨማሪ ወቅታዊ መግለጫ እዚህ ይገኛል
  3. በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ህንጻዎች ውስጥ እና በትምህርት ቤት አውቶቡሶች ውስጥ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም የትምህርት ዓመቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ግዴታ ይሆናል። ይህ ከስቴት እና ከካውንቲው መመሪያ ጋር የሚጣጣም ነው። በመናፈሻ እረፍት ጊዜ ስለ ማስክ/ጭምብል አጠቃቀም አስፈላጊነት የበለጠ መረጃ በቅርቡ ይገለጻል።
  4. MCPS በአሁኑ ጊዜ የ5ኛ እና የ8ኛ ክፍል መዛወር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለውጥ አላደረገም። እድሜአቸው ከ12 ዓመት በታች ለሆኑ ተማሪዎች ክትባት ገና አልጸደቀም፤ ብዙ ተማሪዎች (እድሜአቸው 12 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው) ክትባት በመውሰድ ላይ ናቸው። የተማሪዎችንና የተቋማቱን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ቨርቹወል ሥነ ሥርዓቶች ይካሄዳሉ። ትምህርት ቤቶች የ5ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን የማጠናቀቂያ ሥነ ሥርዓቶችን እንዴት በጤናማ ሁኔታ በአካል ማክበር እንዳለባቸው ተጨማሪ መንገዶችን ለመወሰን ከሠራተኞች እና ከቤተሰቦች ጋር በጋራ እየሰሩ ናቸው።
በትምህርት ቤት ስርዓት ክንዋኔዎች፣ ክስተቶች እና ፕሮግራሞች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች ሲኖሩ ለማህበረሰቡ ወቅታ መግለጫ መስጠታችንን እንቀጥላለን።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools