‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ 
All In blog by MCPS Superintendent Dr. Jack R. Smith

ሁላችንም አንድ ላይ ነን፦ የዚህን አስቸጋሪ ዓመት የ2020 ተመራቂዎችን ስሜት መጋራት

የተወደዳችሁ የ2020 ተመራቂዎች

እንኳን ደስ አላችሁ! በዚህ የቨርቹወል መመረቂያ ሣምንት፣ ስለ እያንዳንዳችሁ አሁን እና ለወደፊት እጅግ መልካሙን እመኝላችኋለሁ። እኔ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረቅሁት የዛሬ 45 ዓመት በዚህ ሣምንት ከ"Eastern Washington State" በአንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ ነው። ረዥም ጊዜ ነው ለማለት ይቻላል፣ ነገር ግን ጊዜው እንዴት እንደሮጠ-ወዴት እንደሄደ አላውቅም።

ከጥቂት ሣምንት በፊት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችሁን እየጨረሳችሁ ስለሆነ ከእናንተ አንዳንድ ሃሳቦችን በመሰብሰብ እንዲረዱኝ የትምህርት ሥርአት ባልደረቦችን ጠይቄ ነበር። ባቀረብኩት ጥያቄ መሠረት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምላሾች ተሰንዝረዋል። በዚህም መሠረት፣ የ2020 ተመራቂ አባሎች ከመለሳችኋቸው ጥቂቶቹን እነሆ።


Thought for the Day
እለቱን ሳስብ፦

ህይወት የሰጠቻችሁን ነገር በማሰብ አመስጋኝ ሁኑ እናም በረከቶቻችሁን ቁጠሩ።

ከማህበራዊ ግንኙነቶች መራቅን ተግባራዊ አድርጉ።

የእኔ የቪድኦ ጨዋታ ሱሰኝነት እየጨመረ ባልሄደ እና ድጋሚ ወደ ትምህርት ቤት ተመልሰን በሄድን ያሰኛል።

ራሳችሁን ከሌሎች ጋር እያወዳደራችሁ መዘናጋትት የለባችሁም፥ አሁንም ከፊትለፊታችሁ ስኬት አለ።

በጎነትን ምረጡ።

ከመታጠቢያ ክፍል ንጹሕ ሆኖ መውጣት ከተቻለ ፎጣዎች እንዴት ሊቆሽሹ ይችላሉ?

አንድ ሃሳብ ረብ የሌለው ቢሆንና፣ ነገር ግን የሚሠራ ከሆነ፣ እውነት ረብ የለውም?

እኔ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጣም ጥሩ ተሞክሮ ነበረኝ።

እንቅልፍ ማግኘት። ሁላችንም ብዙ ጊዜ በዚህ አይነት መንገድ ተጉዘናል።

አስተሳሰባችሁን ቀይሩ እና ዓለምን ትቀይራላችሁ።

ስለ ነገው።


Thought for the Day
የኮቪድ-19 አስቀያሚ ተሞክሮ

የእውነት በጣም ልዩ ለሆኑ ሰዎች ደህና ሁኑ አልልም።

የትም ቦታ ሲኬድ ጭምብል ተደርጎ ነው

ከጓደኞቻችን ጋር ሳንገናኝ ከማህበራዊ ግንኙነት ተራርቀን በየቤታችን ታግደን በመቆየታችን ምክንያት የደረሰብን የተደራረበ መሰላቸት እና ብቸኝነት አለ።

ፕሮም የለም፣ መመረቅ የለም

ምግቡም አነስተኛ ነው

ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አልተቻለም

ሁሉም ነገር ይከብዳል።

ስለ ኮቪድ-19 በጣም አስከፊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ፀጉሬን እንኳ መቆረጥ አልቻልኩም

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እጅግ ከባድ የሆነብኝ መድረክ-ደረጃ ላይ ለመውጣት አለመቻሌ ነው።

ማን እንዳለበ(ባ)ት ወይም ማን ተሸካሚ እንደሆነ(ች) ምንም ሳይታወቅ፥ ሰዎች እየሞቱና እየታመሙ ናቸው።

አንዳንዶቹ ቀኖች በጣም ዘገምተኛ ናቸው።

ቢሆንም፣ እንደሚመስለኝ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ከባዱ ነገር ጓደኞችን ወይም ዘመዶችን ለማየት አለመቻል ነው። አንዳንድ ጊዜ የእኔ አባት አገሩን ትቶ ከእኛ ጋር አብረን በሆንን እያልኩ እመኛለሁ። ተገልሎ መቆየቱ ለራሳችን ጤንነትና ደህንነት መሆኑን ማስታወስ ይገባል።

ስለ ዘመዶቻችን እና ስለጓደኞቻችን በእርግጥ የምናስብ ከሆነ፣ ማህበራዊ እርቀት የመጠበቅን መመሪያ መከተል እና ትእግስተኛ መሆን ብልህነት ነው። አንድ ቀን እናገኛቸዋለን።

ለሁለት ወሮች በቀጥታ እነዚያኑ ሦስት ሰዎች ብቻ ማየት (ቤተሰቦቼን እወዳቸዋለሁ፣ ነገር ግን፣ ጎበዝ፥ ጥቂት ፋታ ያስፈልገኛል)


Thought for the Day
ለ2021 ተመራቂ ተማሪዎች ምክር

አመታችሁን በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ።

በመጨነቅ ሳይሆን በጥበብ ሥሩ።

ትግሉን እስከምታጠናቅቁ ድረስ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ። በሲንየር ዓመቴ፣ አንዳንድ ትምህርቶችን ማለፍ እንደማልችል የማስብባቸው ጊዜያት ነበሩ። ይህ ዓይነት ስሜት ቢኖረኝም፥ ሴሚስተሩ ከመጠናቀቁ በፊት ተስፋ ከቆረጥኩ ራሴን ይቅር እንደማልል በልቤ ይሰማኝ ነበር። ስለዚህ፥ እስከፍጻሜው ድረስ፣ የምችለውን ሁሉ ስላደረግሁ፣ እነሆ ራሴን ማውጣት ችያለሁ።

መልካም እድል!

እናንተን ማስቆም የምትችሉት እራሳችሁ ናችሁ።

"AP classes" ክፍሎችን ትታችሁ፥ በጥንድ ለሚሰጥ ትምህርት ተመዝገቡ።

አትስነፉ።

ተስፋ አትቁረጡ።

በመጀመሪያ፥ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍሉ፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቁ ነገሮች ቢኖሯቸውም እና/ወይም አስጊ ሁኔታዎች እንኳ ቢኖሩ፥ ያገኛችኋቸውን እድሎች በከንቱ አታሳልፉ። ምን አይነት ውጤት እንደምታገኙበት አይታወቅም። ሁለተኛ፥ ከምታስቡት ይልቅ ቃላት ይበልጥ ሃይለኛ

ናቸው። ቃላትን በጥንቃቄ መምረጥ ያስሸልማል።

የኮሌጅ ማመልከቻዎችን "college apps" በጊዜ ለማጠናቀቅ ሞክሩ፥ ምክንያቱም አንዳች የጎደለ ነገር ቢኖር ለማሟላት በቂ ጊዜ ይኖራል።

የምታደርጉትን እንደምታውቁ-አውቃችሁም እንደምታደርጉ መገመት አለባችሁ።

በውጤታችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ፣ ሲንየር በመሆናችሁ መዘናጋት አያስፈልግም። ትኩረታችሁን ጠብቁ-አትዘናጉ።

እጆቻችሁን ታጠቡ።

እኔ ለማለት የምፈልገው አንድ ነገር ቢኖር ... በዚህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓመት እኛ ለመሻገር ከቻልን፣ እናንተም ትችላላችሁ።

በተቻላችሁ መጠን በጣም ጥሩ ለመሆን ሞክሩ። ጥሩ ምሳሌ ሁኑ። እናንተ ሲንየሮች ናችሁ።


Thought for the Day
ከመምህር ወይም ከአስተዳደር ተወዳጅ የሆነ ጥቅስ ወይም መግለጫ

"Elaborate."-ጥልቀትና ጥንቃቄ ይኑርህ(ሽ)— የምወደው የ AP ስነጽሑፍ መምህሬ

“Be good; do good.”-ጥሩ መሆን፥ ጥሩ መሥራት—Edward Owusu, principal

ትእግስት የሚያስፈልገው ለምንድነው? - “Why is patience so important? ትኩረት እንድንሰጥ ስለሚያደርገን ነው - Because it makes us pay attention.”—Kristen Bouvé, teacher

ይቅርታ ይደረግልኝ - "Excuse me."—Every teacher in the school እያንዳንዱ የትምህርት ቤት አስተማሪ

"አንዴ መድረኩ ላይ መውጣትህ(ሽ)ን ካየሁ፣ ደስታህ(ሽ)ን መጥተህ(ሽ) በማቀፍ ብትገልጽልኝ-ብትገልጪልኝ ይሻላል፣ ምክንያቱም ምንም እንኳ አስቸጋር-ከባድ ሁኔታን ብትጋፈጥ(ጪ)ም ተስፋ እንድትቆርጥ(ጪ) ብቻህ(ሽ)ን አልተውህ(ሽ)ም። ቢ ማለት ቁጥር ነው - “B is a number.”—David Kraft, teacher (Taken out of context, but funny nonetheless.)

ከሙዚቃ መሣሪያ አስተማሪዬ የምወደው ጥቅስ፦ ሁልጊዜም በርትተን እንድንሠራ ይነግረናል-ትነግረናለች እና ያንን ካደረግን በኋላ፣ ዘና ብለን መቀመጥ እና ኮካ ይዘን መዝናናት። Shout out to Mr. (Daniel) Grande!

ከአስተማሪዬ በጣም የምወደው ጥቅስ “Do it now, Marilyn የሚለው ነው። አሁን ሠርተህ ጨርስ-አሁን ሠርተሽ ጨርሺ እና ነፃ ሁን(ኚ) - Do it now and be free!”

ሙዚቃ መንፈስን ያድሳል/ያረካል - “Music is good for the soul.”—Ms. E., chorus teacher

በመጨረሻ እጅግ ጠቃሚ ስለሚሆን አሁን ጠንክረህ ሥራ-ጠንክረሽ ሥሪ “Work hard because in the end it’s worth it!”

ከእውነት አትሽሽ(ሺ) - “Don't be indifferent to the truth.”

“Don’t get lost in the sauce.” በቀልድ አትወሰድ(ጂ)— Mr Green

ምንጊዜም የማልረሳው አባባል በምንም አይነት ተስፋ አትቁረጥ(ጪ) ወይም ሰዎች እንዲያጣጥሉህ(ሽ) አትፍቀድ(ጂ) የሚለው አገላለጽ ነው- “Don’t ever give up or let people bring you down because of የአልጄብራ አስተማሪዬ አንድ ጊዜ የገለጸ(ች)ልኝ ከየትም የመጣህ(ሽ) ቢሆን እኮራብሃ(ሻ)ለሁ - “where you’re coming from.” “I’m proud of you.” የሚል ነበር።

ከሁሉም አስተማሪዎቼ የሰማሁት አንድ አይነት ምክር፦ ስለማጥናት እና በትጋት ስለመሥራት ነው - "Keep studying and work hard."

ቲማቲም አትክልት መሆኑን መለየት “እውቀት” ቢሆንም -ከፍራፍሬ ሳላድ ጋር ያለመቀላቀል ደግሞ “ጥበብ” ነው “Knowledge is knowing a tomato is a fruit. - Wisdom is not putting it in a fruit salad.”—Haroot Hakopian, AP language teacher

"You don't have to be here; you get to be here!"—Robyn Kleiner-Vilgos, teacher

የቡና ሱሰኝነቴን ስላረካኸ(ሽ)ኝ አመሰግናለሁ - “Thank you for feeding my coffee addiction.”—Matthew Albright, teacher

የእኔ AP Calc AB አስተማሪ ሁልጊዜ የራሳችሁን እቃ ለይታችሁ ማወቅ አለባችሁ - "You've got to know your stuff," ስንባል ተማሪዎችም ሁልጊዜ-"All the time." በማለት እንመልሳለን።

አልጄብራ፥ አልጄብራ፥ አልጄብራ - "Algebra, algebra, algebra"—Inyong Choi, teacher

እናንተ ሰዎች፥ ወደ "Chris Kenworthey Show" እንኳን ደህና መጣችሁ። ይህንን ነገር ካሜራው ሳይቆራረጥ በአንድ ጊዜ እንጨርሰዋለን። ሁላችሁም ቴሌቪዥን ላይ ትሆናላችሁ። ተዘጋጁ፦ መልካም እይታ ይሁንላችሁ! አሁን በቀጥታ ስርጭት ላይ ነን፦ 5, 4, 3, 2 እና 1.” (Cue the music. የሙዚቃ ባንዱ መጫወት ጀምሯል። የመልእክት ሙዚቃው በአድማጮች ጆሮ ሲያስተጋባ ጭብጨባው በድምቀት ጦዘ - "እና ተገልሎ የቆየው Mr. Kenworthey.” ይሄውና! —Christopher Kenworthey, social studies teacher

በርትታችሁ ሥሩ፣ ትሁትና ጨዋ ሁኑ፣ ጠንክራችሁ ስሩ - “Work hard, stay humble, stay humble, work hard.”—Mr Hall


ሲንየሮች፣ ሃሳባችሁን ስላጋራችሁን እናመሰግናለን። ጥበበኞች፣ ቀልደኞች እና አዋቂዎች ናችሁ። ስለ ፍትህ፣ ሚዛናዊነትና እኩልነት፣ እንዲሁም ስለሌሎች ደህንነት በጥልቀት ታስባላችሁ - ይገዳችኋል።

የወደፊት ጥረታችሁን እና ስኬታማነታችሁን ለመስማት እጓጓለሁ።

ራሳችሁን ጠብቁ እና ደህና ሰንብቱ

Jack Smith

 
Montgomery County Public Schools

View as a Web Page

Montgomery County Public Schools
850 Hungerford Drive, Rockville, MD, 20850
Call: 240-740-3000 | Spanish Hotline: 240-740-2845