español |
中文 |
français |
tiếng Việt |
한국어 |
አማርኛ
ሁላችንም በአንድነት፦ በወዳጅነት-በጓደኝነት መንፈስ የመተማመን አስፈላጊነት እና ተማሪዎችን በመወከል ተቀናጅቶ መሥራት
እነዚህ ያለፉት ጥቂት ሣምንቶች የኮሮና ቫይረስ-COVID-19 ወረርሽኝን ለመዋጋት "Governor Hogan’s stay-at-home order" ከገቨርነር ሆገን በተላለፈው ትእዛዝ መሠረት ሆን ብሎ ራስን የማግለል ጊዜ ነበር። እነዚህ የመገለል ጊዚያት በተለይም ለተማሪዎቻችን እና ለትምህርት ባለሙያዎቻችን፣ በአብዛኛው ቀኖቻቸውን ፊት-ለ-ፊት በክፍል ውስጥ በትምህርት ላይ ሲያሳልፉ ለነበሩት በጣም ከባድ ጊዜ ነው። ነገር ግን፣ በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ብዙዎቹ እርስ በርስ ለመረዳዳትና በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን አዳዲስ የፈጠራ መንገዶችን ለማግኘት ችለዋል።
እኔ በግሌ ከ ኦክላንድ ተሬስ ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት-Oakland Terrace Elementary School፣ ተማሪዎቻቸውን በጥሩ ሁኔታ የማገልገል ብልኃት ለመፍጠር በአገሪቱ ውስጥ እርስ በርሳቸው እና ከጓደኞቻቸው-ከእኩዮቻቸው ጋር እንዴት እየተባበሩ እንደሆነ ለማወቅ ከዚህ በታች ከተጠቀሱት የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በርካታ ቃለመጠይቆችን-ኢንተርቪው የማድረግ እድል ነበረኝ “two-way immersion educators (Rachel Mann, Claudia Moncayo, Paula Liz Lueck and Genny Dorsainvil)”። ስለ ሚዛናዊነት-ፍትሃዊነት ተወያይተናል እና በእነርሱ በኩል ይህንን አዲስ እና የተለየ የርቀት ትምህርት ሁኔታ ልምድ በሚመለከትም ተነጋግረናል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የእነርሱ ተማሪዎች ስለ ራሳቸው ለመግለጽ ስለሚጠቀሟቸው የሚያስደንቁ አይነት ምስሎችም ያጋራሉ።
የኮሮና ቫይረስ-COVID-19 ወረርሽኝ ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን በአካል የለያየ ቢሆንም፣ የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰቦች ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የሚያስችላቸው የፈጠራ መንገዶችን እያገኙ ናቸው። በዚህ ሁላችንም አብረን ነን።
|