የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣

ይህንን ደብዳቤ የምንጽፍላችሁ ስለ ኮሮና ቫይረስ እና የጠቅላላ ተማሪዎችን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለሚያደርገው ጥረት ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ነው።

በትላንትናው ቀን (ማርች 3) የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት (DHHS) እና ከአስቸኳይ-ክስተት ማኔጅመንት እና ሆምላንድ ሰኩሪቲ ጽ/ቤት በካውንቲው ስለኮሮና ቫይረስ ዝግጁነት የተደረጉ ጥረቶችን በሚመለከት መግለጫ ተሰጥቷል። ካውንስሉ ስለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወቅታዊ መረጃ በማግኘት የሁሉንም ተማሪዎች ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ በካውንቲው ስለሚደረጉት ጥረቶች ተነጋግሯል። በዚህ አስፈላጊ ውይይት ላይ የ MCPS መሪዎች እና ሌሎች የማህበረሰብ አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ሁሉንም የማህበረሰባችንን አባላት እናደፋፍራለን መግለጫውን እንዲመለከቱእናእንዲያነቡመግለጫው ላይ የቀረቡትን ቁልፍ የሆኑ ዶኩመንቶችን።

በአጠቃላይ ለአሜሪካን ህዝብ ስጋቱ ዝቅተኛ መሆኑን DHHS ከመግለጹም በላይ እስካሁን ድረስ በሜሪላንድ ወይም በናሽናል ካፒታል ሪጅን የተከሰተ-የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩ ተገልጿል። በሜሪላንድ ህግ መሠረት፣ ህብረተሰብን የሚያሰጋ የጤና ስጋት ሲከሰት ትምህርት ቤት እንዲዘጋ የሚወስነው የካውንቲው የጤና ኦፊሰር ነው። እነዚህ አይነት ውሳኔዎች የሚሰጡት ከሌሎች የካውንቲው ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር ነው። በዚህ ወቅት፣ በ DHHS መመሪያ መሠረት፣ ትምህርት ቤቶች ክፍት ይሆናሉ እና በካውንቲው ደረጃ መደበኛ ሥራ ይቀጥላል።

በስቴቱ እና በካውንቲው ወረርሽኝ ከተከሰተ የተማሪዎችን ትምህርት እና ሥራዎችን ለማስቀጠል MCPS የተዘጋጀ እቅድ/ፕላን አለው። አጠቃላይ የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነትን አሠራር ቅደምተከተሎች ለመገምገም ዲስትሪክቱ በዚህ ሣምንት ከርእሰመምህራን ጋር ስብሰባ ያደርጋል። በትምህርት ቤቶች የቫይረሱ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ለመከላከል እና ትምህርት ቤት ሲዘጋ የተማሪዎችን ትምህርት ለማስቀጠል ደረጃ በደረጃ ስለምንወስዳቸው እርምጃዎች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልጉ የማህበረሰብ አባላትን መስማታችንን እንቀጥላለን። ስለትምህርት ቤት፣ ፋሲሊቲ እና ስለማስተማር ሁኔታ-ገፅታ ስለ ዲስትሪክቱ እቅድ የሚከተለው መረጃ ያመለክታል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ፋሲሊቲዎች

 • የ MCPS የህንፃ አገልግሎት ሠራተኞች የጋራ መጠቀሚያ ስፍራዎችን ከተላላፊ ተዋህሳት በጠራ ሁኔታ የማፅዳት ተግባር አዳብረዋል።
 • እጅን ከጀርም የሚያፀዳ "sanitizers" በሁሉም ፋሲሊቲዎች በብዛት እንዲኖር ይደረጋል እና የእጅ ንፅህናን ለመጠበቅ አዘውትሮ መታጠብ እንደሚያስፈልግ በየህንፃዎቹ ተገቢ ቦታዎች ሁሉ ላይ ሳሙና እንዲኖር የማድረጋችንን ትኩረት እንቀጥላለን።
 • ዲስትሪክቱ ስለ ጉንፋን እና ኢንፍሉዌንዛ ወቅትን በተመለከተ አጠቃላይ የጤና ሁኔታ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች እና ከሠራተኞች ጋር የሚያደርገውን ምርጥ ተሞክሮዎችን ማካፈል እንቀጥላለን። እነዚህ የመከላከል እርምጃዎች የሚያካትቱት፦
  • ቢያንስ ለ 20 ሰከንዶች ያህል እጅን በሳሙና እና በውሃ በተደጋጋሚ መታጠብ። ውሃ እና ሳሙና ከሌለ፣ የአልኮልነት ይዘት ባላቸው የእጅ መፀዳጃዎች መገልገል።
  • ባልታጠቡ እጆች አይኖችን ፣ አፍ እና አፍንጫን ከመንካት ይቆጠቡ።
  • ከታመሙ ሰዎች ጋር በቅርበት መነካካትን ያስወግዱ።
  • ከታመሙ እቤት ይዋሉ።
  • ግለሰቦች ምንም የትኩሳት ማስታገሻ መድሃኒት ሳይወስዱ (ብርድ ብርድ ሳይላቸው፣ ሙቀት/ትኩሳት ሳይሰማቸው፣ የሰውነት ላብ) ትኩሣት ወይም የትኩሳት ምልክት ሳይሰማቸው ቢያንስ 24 ሠዓት እቤታቸው እንዲቆዩ CDC አስተያየት ይሰጣል።
  • ሳልዎን ወይም ማስነጠስዎን በቲሹ ይሸፍኑ፣ ከዚያ ወዲያውኑ ቲሹዉን በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጣሉ።
  • ብዙ ጊዜ የሚነኩ ነገሮች/እቃዎችን እና ስፍራዎችን ማጽዳት እና ከጀርም ነፃ/ድስኢንፌክት ማድረግ።
  • በተነገረዎት መሰረት የታዘዙልዎትን ማንኛውንም ፀረ-ቫይረስ መድሃኒት ይውሰዱ።
 • ከ CDC የተገኙ መረጃዎችን የያዙ ፖስተሮች ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ይሠራጫል። ወላጆች እነዚህን ፖስተሮች በበርካታ ቋንቋዎች ማግኘት ይችላሉእዚህ

ለተማሪዎች ትምህርት የመስጠት ተግባሮች

 • MCPS ትምህርት ቤቶች ዝግ የሚሆኑበት ሁኔታ ከተከሰተ ከሙአለህፃናት እስከ 12ኛ ክፍሎች ለሁሉም ተማሪዎች የማስተማር ሥራ የሚቀትልበትን ሁኔታ እያዘጋጀ ነው።
 • የሁሉንም ተማሪዎች እና ቤተሰቦችን ፍላጎት ለማሟላት፣ እነዚህ የማስተማር እንቅስቃሴዎች በአውታረ-መረብ ተደራሽነት እና በህትመት ኮፒዎች ይሠጣሉ።
 • የማስተማር እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን በርካታ መገልገያዎችን እንጠቀማለን። ይህ የሚያካትተው፦
  • የትምህርት ቪድዎችን እና ሌሎች የማስተማሪያ ማቴሪያሎችን ለተለያዩ የክፍል ደረጃዎች እና ትምህርቶችን አግባብነት ባለው መንገድ ለማሠራጨት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ድረ-ገጽ መጠቀም።
  • የተለያዩ የክፍል ደረጃዎች እና ትምህርቶችን የሚያካትቱ ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን ለማሠራጨት የ MCPS የትምህርት ቴሌቪዥን መጠቀም።
  • ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ለማከናወን የሚችሉትን የትምህርት ተግባር ሃሳቦችን መስጠት።
  • "Google for Education Accounts" ተደራሽነት ያላቸው ተማሪዎች በተቀናጀ መልኩ በአውታረ-መረብ ትምህርቸውን ለመከታተል ይችላሉ። የእኛ ቴክኖሎጂ ለተማሪዎች ተደራሽ ሊሆን የሚችልበትን መንገዶችም እያሰብን/እያጠናን ነው።

ትምህርት ቤት የሚዘጋ ከሆነ

 • MCPS ፋሲሊቲዎቻችን እና አውቶቡሶች መደበኛ ሥራቸውን ስለሚያከናውኑበት ሁኔታ ከ DHHS የሚሰጠውን መመሪያ እንከተላለን።
 • የ MCPS ድረ-ገጽ በየጊዜው ወቅታዊ ይደረጋል እና ስለ ሥራ እንቅስቃሴዎቻችን ለማህበረሰብ አባላት መረጃ ይሰጣልበርካታ ዘዴዎችን በመጠቀምAlertMCPS፣ ConnectEd፣ ሶሻል ሚድያ/social media፣ the MCPS Information Line፣ እና QuickNotes ን ሁሉ ይጨምራል።
 • የፋሲሊቲዎቻችንን ንፅህና እና ጤናማ ሁኔታ ለማጣራት አስፈላጊ የሆኑ የ MCPS ሠራተኞች ከሌሎች ሠራተኞች ሁሉ አስቀድመው ይመለሳሉ።
 • ትምህርት ቤቶች የሚዘጉበትን የጊዜ ርዝመት በመመርኮዝ፣ በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ የሪጅናል መመገቢያ ስፍራዎች እንደመሆናቸው መጠን ምግቦችን ለማቅረብ ተዘጋጅተናል። ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ ስለ ቦታዎቹ ለማህበረሰቡ መረጃ ይገለጻል።

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

 • MCPS ወቅታዊ ይደረጋል ስለ ኮሮና ቫይረስ ድረ-ገጽበየቀኑ እና የማህበረሰቡ አባላት ዘወትር ድረ-ገጹን እንዲጎበኙ እናበረታታለን። ድረ-ገጹ ላይ ከካውንቲው፣ ከስቴት እና ከፌደራል የጤና ኃላፊዎች የሚተላለፉ ወቅታዊ መረጃዎች የሚኖሩት ሲሆን፣ ስኮሮና ቫይረስ ከልጆቻችሁ ጋር እንዴት ለመነጋገር እንደሚችሉ፣ እና በተደጋጋሚ ስለሚነሱ ጥያቄዎች በበርካታ ቋንቋዎች ጠቃሚ ሪሶርሶችን፣ እና ፍንጮችን ይሰጣል። በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች FAQs ስለ ትምህርት ቤት የመስክ ጉዞዎች፣ ስለ ማስተማር እቅዶች እና ወላጆች እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ተጨማሪ ጠቃሚ ርእሶች ላይ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

ስለ ካውንቲው ጥረት ጥያቄዎች የሚኖርዎት ከሆነ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና ወረርሽኝ ቁጥጥር ጽ/ቤት - Montgomery County Office of Disease Control and Epidemiology በስልክ ቁጥር 240-777-1755 ለማግኘት ይችላሉ። እባክዎ ስለ ዲስትሪክቱ የሥራ እንቅስቃሴ እና የተማሪዎች ትምህርት ጥያቄዎች ካሉዎት MCPS Office of Communications በስልክ ቁጥር 240-740-2837 ያነጋግሩ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (Montgomery County Public Schools)