Skip to main content

Amharic 12-21-2023


ዲሴምበር 13, 2023

ዲሴምበር 14 ሱፐርኢንተንደንቷ የሚያቀርቡትን የሥራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።

ማጠቃለያ፡ ሀሙስ፣ ዲሴምበር 14፣ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት የበጀት አመት 2025 የስራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር ያቀርባሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ መክናይት ለ 2025 የበጀት ዓመት የታቀደ የስራ ማስኬጃ በጀት መግለጫ ሐሙስ፣ ዲሴምበር 14 በኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 6 p.m. ላይ ያቀርባሉ። ማህበረሰቡ MCPS ድረ ገጽ ላይ፣ MCPS-TV YouTube ቻነል፣ እና MCPS-TV ቻናሎች ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ የሚተላለፈውን የቀጥታ ስርጭት እንዲመለከት ተጋብዟል።

 

የጥገና እና ኦፕሬሽን የስራ አውደርእይ ዲሴምበር 15 ይካሄዳል


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጥገና እና ኦፕሬሽንስ ክፍል አርብ፣ ዲሴምበር 15 የስራ አውደርዕይ ያስተናግዳል። ክህሎት ላላቸው የቧንቧ ሥራ ባለሙያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኒሻኖች፣ የጥገና አናጺዎች፣ የኤሌክትሪክ ጥገና ባለሙያዎች እና HVAC-R ቴክኒሻኖች በቦታው ላይ የመቀጠር ዕድሎች ይኖራሉ።


ሁለት ክፍለ ጊዜዎች የሚካሄዱ ሲሆን—የመጀመሪያው 7 a.m.–1 p.m. እና ሁለተኛው 3–7 p.m ይሆናል። ፕሮግራሙ የሚካሄድበት አድራሻ ይሄ ነው፦ Division of Maintenance and Operations offices, 8301 Turkey Thicket Drive, Building A, First Floor, Gaithersburg።
ያሉት ስራዎች ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ፈረቃዎች ነው።

የስራ ዓውደርዕይ፣ ዲሴምበር፣ 15, 2023

MCPS Careers

 

ቦርዱ 2024-2025 የትምህርት ዓመት ካለንደር አጽድቋል

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ 2024-2025 የትምህርት አመትን ካላንደር አጽድቋል። ካላንደሩ የትምህርት መስተጓጎሎችን ውስን በማድረግ እና በሙያ ማዳበር የትምህርት ቀናት ስርዓቱ በሰራተኞቹ ላይ ቀጣይነት ያለ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱን ትኩረት በማድረግ ከማህበረሰቡ ለተገኘው ግብዓት ምላሽ ይሰጣል።

 

2024-2025 የትምህርት ካላንደር የሚከተሉትን ያካትታል፦

 

  • መደበኛውን ካላንደር ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች፡ የተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 26, 2024 ሲሆን ትምህርት መጨረሻው ቀን አርብ ጁን 13, 2025 ይሆናል።
  • ኢኖቬቲቭ ካላንደር ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች፡ የተማሪዎች የመጀመሪያው የትምህርት ቀን ሰኞ፣ ጁላይ 8, 2024 ሲሆን የመጨረሻው የትምህርት ቀን አርብ፣ ጁን 13, 2025 ነው።
  • ዲስትሪክት አቀፍ የፕሮፌሽናል/የሙያ ቀናት አርብ፣ ኦክቶበር 18, 2024 እና አርብ፣ ጁን 6, 2025 ይሆናሉ
  • መደበኛ ካላንደር ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ቀድመው የሚወጡባቸው አምስት የታቀዱ ቀናቶች ይኖራሉ እነሱም፦ ሴፕቴምበር 27, 2024፣ ኖቬምበር 25-26, 2024 (ለተማሪዎች ኮንፍረንሶች የተመደበ)፣ ፌብሩዋሪ 28, 2025፣ እና ጁን 13, 2025 ናቸው።
  • የዊንተር የእረፍት ጊዜ ቅዳሜ፣ ዲሴምበር 21, 2024 ይጀምራል እና እሮብ፣ ጃኑዋሪ 1, 2025 ያበቃል።
  • የስፕሪንግ የእረፍት ጊዜ ቅዳሜ፣ አፕሪል 12, 2025 ይጀምራል እና ሰኞ፣ አፕሪል 21, 2025 ያበቃል።

 

ካላንደሩ በትምህርት አመቱ ውስጥ በተጠባባቂ ቀናት የተያዙትን 6 ቀናትን ጨምሮ 182 የትምህርት ቀናትን ይይዛል። እነዚህ ቀናቶች በስቴት ህግ ከተቀመጡት የበዓላት መዝጊያ ቀናት ተጨማሪ ናቸው።

 

FY 2025 የትምህርት ቤቶች መደበኛ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር

FY 2025 የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር

 

ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት ከ MCPS ጋር ግንኙነት ይኑርዎት


የክረምቱ የአየር ሁኔታ በቅርብ ርቀት ላይ እያለ፣ MCPS ከባድ የአየር ሁኔታ ሲኖር ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት፣ ዘግይቶ ስለመክፈት፣ እና ተማሪዎችን ከመደበኛው ሰአት በቅድሚያ ስለማሰናበት ለማሳወቅ ብዙ መንገዶችን እንደሚጠቀም ያስታውሱ። የአየር ሁኔታ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚወሰኑ እና ስለማንኛውም ለውጦች እንዴት መረጃ እንደሚያገኙ የበለጠ ይገንዘቡ።

 

2022-2023 አመታዊ ሪፖርት እና አዲስ የትምህርት ቤቶች መግለጫዎች ዳሽቦርድ አሁን ተዘጋጅቷል።

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2022-2023 አመታዊ ሪፖርት መውጣቱን ዲሴምበር 5 በተካሄደው የትምህርት ቦርድ መደበኛ ስብሰባ ወቅት በማህበረሰብ ድረ ገጽ ላይ አስታውቋል። ይህ አጠቃላይ ሪፖርት ያለፈውን የትምህርት ዓመት ክንውኖችን እና ዋና ዋና ጉዳዮችን በማጠቃለል ስለተማሪዎች እና ስለተግባራዊ አፈፃፀሞች፣ እንዲሁም ስለ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ራዕይ እና ተልእኮ በማሳካት ረገድ ስለታየው እድገት/መሻሻል ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል። ከሪፖርቱ ህትመት በተጨማሪ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ አሳታፊ የሆነ የኦንላይን ሪፖርት ተዘጋጅቷል


አመታዊ ሪፖርቱ ከ 2022-2023 የትምህርት ዓመት ወሳኝ ክንውኖችን ከዋና ዋና ፍሬነገሮች ጋር ያካትታል፡ የስርዓት አቀፍ ፀረ-ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር (Anti racist System Action Plan)፣ ለኮሌጅ፣ ለሙያ ስራ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዝግጁነት መንደርደርያ መንገድ፣ እና የተማሪዎች አፈፃፀም መረጃ፣ የተማሪዎች ምረቃ፣ አገልግሎቶች እና የስራ ግብረ ሃይል የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። በተጨማሪም ከስትራቴጂክ እቅዱ ላይ የእድገት/የግስጋሴ አሁናዊ ሁኔታዎችን እና በስራ ማስኬጃ እና በካፒታል በጀት ላይ መረጃ ይሰጣል። ይህ ሪፖርት ስለ ዲስትሪክቱ ስኬቶች እና እቅዶች ጠቃሚ፣ አጠቃላይ እይታ ይሰጣል።

 

አዲስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤት መግለጫ መረጃ ዳሽቦርድ


MCPS Schools at a Glance (ትምህርት ቤቶች በጨረፍታ እይታ) ሪፖርትን የሚተካ እና ከስርዓት አቀፍ ፀረ-ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር ጋር በማጣጣም የዲስትሪክት እና የትምህርት ቤቶች መረጃዎች ላይ ይበልጥ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ የሚሰጥ "School Profiles Dashboard" (የትምህርት ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ) ተከፍቷል። የትምህርት ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ ትምህርታዊ የእድገት ደረጃ መረጃዎችን፣ ወደ ኮሌጅ፣ ወደ ስራ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዝግጁነት ከሚወስደው መንደርደርያ ጋር ማሣለጥን ያካትታል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ሪፖርት የተደረጉትን ኦፊሴላዊ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችሉ የትምህርት ቤት መግለጫዎች ሊንኮች MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።

የትምህርት ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ የትምህርት ቤት እና የዲስትሪክት መረጃዎች ማጠቃለያ ቻርቶችን እና ግራፎችን በማቅረብ ሁሉን ያካተተ እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል። ሁሉም የማህበረሰቡ አባላት መረጃውን ማግኘት እና መረዳት እንዲችሉ ለማረጋገጥ በስምንት ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ይገኛል። ዳሽቦርዱ እንደአመቺነቱ አማራጮችንም ያቀርባል፣ ማለትም ተጠቃሚዎች እንደ Excel ፋይል መረጃን እንዲያስቀምጡ (save እንዲያደርጉ) ወይም PDF በህትመት ማስቀመጥ እንዲችሉ ያደርጋል። ዳሽቦርዱ ሁሉን አቀፍ ስለሆነ ተጠቃሚዎች የት/ቤት መረጃዎችን ወይም በሙሉ የዲስትሪክቱን መረጃዎች እየመረጡ እንዲመለከቱ ያስችላቸዋል።


"እነዚህ መሳሪያዎች የተገነቡት ለመገንዘብ-ቀላል-በሆኑ መንገዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማህበረሰባችን ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ነው፣ እና ለእድገታችን ግልጽነትን እና ግንዛቤን በመስጠት ረገድ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖራቸው እናምናለን''፣ በማለት የስትራቴጂክ እቅዶች ዋና ኃላፊ ስቴፋኒ ሸሮን መግለጫ ሰጥተዋል። "እነዚህን መገልገያዎች ለመፍጠር ቡድናችን ባደረገው ትጋት እና ቁርጠኝነት ኩራት ይሰማናል፣ እናም በማህበረሰባችን ላይ የሚኖራቸውን አዎንታዊ ተጽእኖ በጉጉት እንጠባበቃለን።"


የት/ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ ትግበራ በሦስት ደረጃዎች ይከናወናል።

 

የመጀመሪያው (Phase 1) የትምህርት አመት 2022-2023 መረጃን ያካትታል። የ MSDE መረጃዎች ተጠቃለው ከቀረቡ በኋላ የ 2023–2024 መረጃ 2024 መጀመሪያ ላይ (ወቅታዊ ይደረጋ፤)።


ሁለተኛው (Phase 2)፣ ለስፕሪንግ 2024 እንደሚቀርብ ታቅዷል፣ በዳሽቦርድ ግንባታ ወቅት በተሰበሰቡ ግብረ መልሶች ላይ በመመስረት ትኩረት ከተሰጣቸው  ማሻሻያዎች ጋር፣ ደህንነትን እና ጸጥታን እንዲሁም የልዩ ትምህርት መግለጫዎችን ይዞ ይቀርባል።


ሦስተኛው (Phase 3)፣ ለፎል 2024 የታቀደ ሲሆን፣ 2023–2024 የአካዳሚክ እድገት ደረጃዎች ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ተጨማሪ የተተኮረባቸው  ማሻሻያዎችን ያካትታል።


MCPS ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና የመረጃ ተደራሽነትን ለማህበረሰቡ ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው።

 

MCPS 2022-2023 ዓመታዊ ሪፖርት

MCPS የትምህርት ቤቶች መረጃ ዳሽቦርድ

 

የድጋፍ አገልግሎት ሽልማቶች የመጨረሻ ቀን እስከ አርብ ዲሴምበር 15 ተራዝሟል።

 

ለአመቱ የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሰራተኛ እጩዎችን የማቅረቢያ ቀነ-ገደብ እስከ አርብ፣ ዲሴምበር 15፣ ከቀኑ 5 p.m. ድረስ ተራዝሟል ለእጩነት ተጠቋሚዎች በቋሚ የሥራ መደብ ውስጥ ንቁ የድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች መሆን አለባቸው፣ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቢያንስ የሶስት ዓመት አገልግሎት ሊኖራቸው ይገባል። የበለጠ ለመረዳት፣ እዚህ ይጫኑ።
የተሞሉ የጥቆማ ሠነዶች በኤሌክትሮኒክስ memberservices@seiu500.org መቅረብ አለባቸው።

 

የሚከተሉትን ጨምሮ፣ ሌሎች ሰራተኞችንም እውቅና ለመስጠት እጩዎችን ለመጠቆም ክፍት ናቸው፣

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የአመቱ ምርጥ መምህር፡  እጩ ጥቆማ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሲምበር 22 እኩለ ሌሊት ይሆናል።

 

የየሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ "Rising Star Teacher" የእጩዎችን ጥቆማ ለማቅረብ የመጨረሻ ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ይሆናል።

 

የዋሽንግተን ፖስት የዓመቱ ምርጥ መምህር፡ የእጩዎች ጥቆማ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ነው።

 

የዋሽንግተን ፖስት የዓመቱ ምርጥ ርዕሰ መምህር፡ የእጩዎች ጥቆማ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ይሆናል።

 

የሽርሌይ ጄ. ሎውሪ ስለማስተማርዎ እናመሰግናለን ሽልማት፡ ለእጩዎች ጥቆማ የመጨረሻ ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ነው።

የሱፐርኢንተንደንት ዓመታዊ "Mark Mann Excellence and Harmony Award" የልህቀት ሽልማት፡ የመጨረሻ ቀን፡ ዓርብ፣ ዲሴምበር 22 እኩለ ሌሊት ይሆናል።

 

የዶክተር ኤድዋርድ ሸርሊ በትምህርት አስተዳደር እና ሱፐርቪዥን የልህቀት ሽልማት፡ የመጨረሻ ቀን፡ ዓርብ፣ ጃኑዋሪ 12፣ 2024፣ 4 p.m. ነው።

 

የሠመር ራይዝ ተቀባይ/አስተናጋጅ በመሆን ተማሪዎችን ይደግፉ።

 

ከ 2024-2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስኬታማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ጋር የስራ ልምድዎን ለማካፈል ይፈልጋሉ? 2024 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም እንዴት ተቀባይ/አስተናጋጅ መሆን እንደሚችሉ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ!

 

የአጋርነት ማስተባበሪያ ዲፓርትመንት ተማሪዎች በአካል፣ ቨርቹዋል ወይም በሁለቱ ጥምር ፕሮግራም ልምድ እንዲያገኙ ቢያንስ 50 ሰዓታት ተቀብለው የሚያስተናግዱ የንግድ ድርጅቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ይፈልጋል። ይህ እድል ተማሪዎች የወደፊት የኮሌጅ እና የሙያ ስራ ውሳኔያቸውን እንዲያውቁ በማድረግ ረገድ ከሚወዱት/ከሚፈልጉት የሙያ መስክ ጋር የተያያዙ የተግባር ተሞክሮዎችን/ልምዶችን እንዲቀስሙ ያስችላቸዋል።

የሠመር ራይዝ ፕሮግራም ከሰኞ፣ ጁን 24, 2024 እስከ አርብ፣ ጁላይ 26, 2024 ይካሄዳል።

 

ጃንዋሪ 30, 2024 ከቀኑ 11 a.m.–2 p.m. በሚካሄደው ሠመር ራይዝ የአስተናጋጆች ስብሰባ ላይ ከቀድሞ አስተናጋጆች፣ አዲስ ከተመዘገቡ አስተናጋጆች  እና ከሌሎች የወደፊት አስተናጋጅ ድርጅቶች ጋር ይቀላቀሉ። ተሰብሳቢዎች ስለ ሠመር ራይዝ፣ ስለ ምርጥ ልምዶች እና ከሠመር ራይዝ ባሻገር ከ MCPS ተማሪዎች እና ፕሮግራሞች ጋር እንዴት መስራት እንደሚችሉ ይተዋወቃሉ። በዝግጅቱ ላይ ለመገኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ እና ስለፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ እንዲያገኙ ጓደኛዎን/የሥራ ባልደረባዎን ይጋብዙ። በስብሰባው ላይ መገኘት (መሳተፍ) ካልቻሉ፣ ነገር ግን ስለ ምዝገባው ሂደት እና ስኬታማ አስተናጋጅ ስለመሆን የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ በመረጃ ክፍለ ጊዜ ለመገኘት መመዝገብዎን ያረጋግጡ

 

ስለ ፕሮግራሙ  የበለጠ ለማወቅ www.MCPS-SummerRISE.org ይጎብኙ፣ Davida Gurstelle ኢሜይል ይላኩ ወይም ያለዎትን ጥያቄ 240-740-5599 ደውለው ያነጋግሩ።

 

መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 14 – ፓረንት አካዳሚ፦ ፈንታንይልን የሚመለከቱ እውነታዎች/Facts About Fentanyl

ሰኞ፥ ዲሴምበር 25 —የበዓል ቀን ስለሆነ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው።

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 26—እሮብ፣ ዲሴምበር 27 — የዊንተር እረፍት፤ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ትምህርት አይኖርም። (ሁሉም ት/ቤቶች)

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 28—ዓርብ፣ ዲሴምበር 29 — የሥርአት አቀፍ ትምህርት ቤቶች ሁሉም ዝግ ይሆናሉ፣ ሁሉም ት/ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው።

ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 1 — በዓል፣ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ።

ማክሰኞ፣ ጃኑዋሪ 2 —ትምህርት የማይኖርበት ቀን፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ትምህርት አይኖርም (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)