Skip to main content

International Student Admissions

ቋንቋ ምረጡ፡-


አንድ ቪድዮ ይምረጡ፡-:

ትምህርት ቤት መመዝገብ

 
 

አብዛኛውን ጊዜ፣ ወላጆች የአካባቢ/ቀበሌ ት/ቤት በማናገር ልጆቻቸውን ያስመዘግባሉ። ነገር ግን በአለፉት ሁለት አመታት ልጅዎ በዩናይትድ ስቴትስ ት/ቤት ካልተከታተለ/ች፣ እርስዎ በመጀመሪያ ወደ ተብሎ ወደ የሚታወቀዉ International Admissions and Enrollment/የት/ቤት ካውንስሊንግ (አማካሪ)፣ ሬዝደንሲ እና አለምአቀፍ ቅበላ ጽ/ቤት መሄድ አለብዎት።

ምንም እንኳ እርስዎ መጀመሪያ ወደ SCRIA፣ ወይም ቀጥታ ወደ አጎራባች (በቅርብዎ ወደሚገኝ) ት/ቤት ቢሄዱም፣ የተወሰኑ ሰነዶች መፈለጋቸው አይቀርም።

በSCRIA በሚኖርዎ የቀጠሮ ጊዜ፣ ሰነዶች ይታያሉ እንዲሁም የአቅራቢያ ት/ቤት ይወሰናል። የተማሪው/ዋ የትምህርት መረጃ/መዝገብ ከተገመገመ በኋላ የክፍል እና የትምህርት አይነት ምደባ አስተያየት ይቀርባል።

ከዛ በኋላ፣ ወላጅ እና ልጅ በዛው ህንጻ ውስጥ የሚገኘውን የካውንቲውን የጤና ክሊኒክ ይጎበኛሉ።    የጤና መዝገቦች ይታያሉ፣ ክትባቶች ሊሰጡ ይችላሉ፣ እንደዚሁም የክትባት የምስክር ወረቀት ይሰጣል።

በመጨረሻ  ከአስፈለገ ለአንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ግምገማ (English Proficiency Assessment) በESOL Testing and Accountability Center ቀጠሮ ይያዛል።

በSCRIA ከጨረሱ በኋላ፣ ከልጅዎ ት/ቤት ሬጅስትራር ጋር ተገናኝተው የምዝገባውን ሂደት መጨረስ ይኖርበዎታል። የሚከተለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፣ መጀመሪያ ከአካባቢዎ ት/ቤት ጋር ይገናኙ

ማስታወሻ፡- ለስደተኞች እና መኖሪያ ቤት ለሌላቸው ልጆች መመሪያው/አካሄዱ ትንሽ ይለያል። ስደተኞች ወደ SCRIA ሲመጡ ይዘውት አንዲመጡ የሚያስፈልግ የተለየ የመኖሪያ ቅጽ አለ። መኖሪያ ቤት የሌላቸው ቤተሰቦች SCRIAን ወይም የአካባቢ ት/ቤትን ለመጎብኘት ቀጠሮ ከማስያዛቸው በፊት የመኖሪያ ቤት ለሌላቸው ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤትን (Homeless Liaison Office) ማግኘት ይኖርባቸዋል።

ተዛማጅ ተያያዦች

በመጀመሪያ ከት/ቤትዎ ጋር ይገናኙ

 
 

ልጅዎ በዩናይትድ ስቴትስ ትምህርቱን/ቷን ሲከታተል/ስትከታተል ከቆየ/ች፣ ወይም የአለም አቀፍ ቅበላ ጽ/ቤትን ጎብኝተው ከነበረ፣ የሚቀጥለው እርምጃ የአካባቢዎን ት/ቤት ማግኘት እና የምዝባ ቀጠሮ ሬጅስትራር ተብሎ ከሚጠራው ሰው ጋር መያዝ ነው። ይህ ውይይት ቢያንስ አንድ ሰአት ሊፈጅ አንደሚችል መገመት ይችላሉ። እንግሊዘኛ በደንብ የማይናገሩ ከሆነ፣ በመጀመሪያ ት/ቤቱን ሲያናግሩ ለሠራተኛው/ዋ የቋንቋ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ ይንገሩ።

ተዛማጅ ተያያዦች

የትምህርት ቤት አውቶብስን በመጓጓዣነት መጠቀም

 
 

የትምህርት ቤት አውቶብስ ግልጋሎት ነፃ ነው፣ ነገር ግን ከትምህርት ቤቱ ቢያንስ የተወሰነ እርቀት መኖር ይኖርበዎታል። የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አንድ ማይል ወይም ከዚያ በላይ እርቀት መኖር አለባቸው። የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሚሄዱ አንድ ከግማሽ ማይል፣ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚሄዱ ከሁለት ማይል በላይ ከት/ቤት የራቁ መሆን አለባቸው። ተማሪዎች በእግር ለመጓዝ አደገኛ ሁኔታዎች የሚገጥማቸው ከሆነ በልዩ ሁኔታ ይታያል።

በመጀመሪያ በት/ቤት ምዝገባ ጊዜ፣ ሬጅስተራሩ/ሯ የት/ቤት አውቶብስ መረጃን ከአንተ/ችና ከወላጅ ጋር ያያል/ታያለች። እያንዳንዱ የትምህርት ቤት አውቶብስ የሚጓዝበትን መስመር መመልከት ትችላለህ/ያለሽ፣ እናም የአንተ/ቺን አውቶብስ መስመር ቁጥርን ጻፈው/ጻፊው። ይህን ቁጥር መዝግበህ/ሽ ያዘው/ያዢው፣ ምክንያቱም በጣም አስፈላጊ ነው።

የአውቶብስ ከየት እንደሚወስድህ/ሽና እንደሚጥልህ/ሽ እና፣ በስንት ስዓት በአውቶብስ መቆሚያው ላይ መገኘት እንዳለብህ/ሽ ለመወሰን የአውተብስ መስመር ቁጥርን ማወቅ ያስፈልግሃል/ሻል። በአውቶብስህ/ሽ ላይ፣ ይሄ ባለአራት አሀዝ የመስመር ቁጥር በጥቁርና ነጭ ምልክት በአውቶብሱ የጎን መስኮት፣ ከመግቢያው አጠገብ ይገኛል። ተጠንቀቅ/ቂ! በአውቶብሱ ላይ የተቀባው ቁጥር አይደለም። ይልቅስ በአውቶብሱ መስኮት ላይ በጥቁር እና ነጭ ምልክት ያለው ነው።

ሁሉም ተማሪዎች በአውቶብስ በሚጓዙበት ጊዜ መመሪያዎችን እንዲከተሉ ይጠበቃሉ።

ልጅዎ የበለጠ ምቾት እንዲሰማው/ት ት/ቤትዎ ምን አልባት የገለጻ ወይም “የጓድ” ፕሮግራም ሊኖረው ይችላል - ሬጅስትራሩን ይጠይቁ። እናም ልጅዎ ከአውቶብሱ የት ቦታ መውረድ አንዳለበት/እንዳለባት እርግጠኛ ካልሆነ/ች ከአውቶብስ ሹፌሩ ቀረብ ብሎ/ላ ይቀመጥ/ትቀመጥ። ሹፌሩም በአውቶብሱ ውስጥ የሚፈጠሩ ማንኛውም ሌሎች ችግሮችን ሊፈታቸው ይችላል። እና በማንኛውም ጊዜ የእርስዎን መምህር፣ የትምህርት ቤት አማካሪ ወይም የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ስለ ስጋቶችዎ ማናገር ይችላሉ።

ብዙ ት/ቤቶች በእያንዳንዱ ሳምንት ብዙ ቀናት ከትምህርት በኋላ ለሚካሄዱ "የተግባር/እንቅስቃሴ"/አክቲቪቲ አውቶብሶችን ያንቀሳቅሳሉ። የእንቅስቃሴ/አክቲቪቲ አውተብሱ ምን አልባት እቤትህ/ሽ አቅራቢያ ሊወስድህ/ሽ ይችላል፣ ነገር ግን በትክክል ወደ ሁል ጊዜ የአውቶብስ ማቆሚያ አይሆንም። የቤትህን/ሽን አድራሻ ማስታወስ እና የእንቅስቃሴ/አክቲቪቲ አውቶብሱ የሚቆምበትን ቦታ ማወቁን እርግጠኛ ሁን/ኚ። ከዚያ ቦታ ቤት ለመድረስ እገዛ የሚያስፈልግህ/ሽ መስሎ ከተሰማህ/ሽ ለወላጅ ተናገር/ሪ።

ጓደኛ በት/ቤትህ/ሽ አውቶብስ ማምጣት ከፈለክ/ሽ፣ ያ/ች ጓደኛ የአንተን/ችን አውቶብስ  በመደበኛነት የማትጠቀም ከሆነ፣ እርሱ/ሷ የአንተን አውቶብስ መጠቀም እንደሚችል/ትችል የሚገልጽ ማስታወሻ ከወላጁ/ጇ ያስፈልገዋል/ጋታል። በአንተ/ቺ ህንጻ ትክክለኛ አሰራሩን ለማወቅ የትምህርት ቤትህን/ሽን ዋና ጽ/ቤት ተገናኝ/ኚ።

ተዛማጅ ተያያዦች

ምግብ በትምህርት ቤት

 
 

የMCPS ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ቁርስ እና ምሳ ይሰጣሉ። ተማሪዎች ከት/ቤት ካፍተሪያ ምግቦችን መግዛት፣ ወይም ምግብ ወደ ት/ቤት ይዘው መምጣት ይችላሉ።

ተዛማጅ ተያያዦች

ስነምግባር በትምህርት ቤት

 
 

በአለም አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎች በበርካታ መንገዶች ይማራሉ፣ እናም ስነምግባር የሚቀረጸው በአካባቢው ባህል ነው። በMCPS ክፍሎች፣ ተማሪዎች በተደጋጋሚ ከአስተማሪያቸውና እርስ-በርሳቸው ይገናኛሉ/ይነጋገራሉ። ተማሪዎች እርስ-በርሳቸው እንዲሁም በክፍል ውስጥ ካሉ አዋቂዎች ለመማር በጥቂት ቡድኖች ሆነው ይሰራሉ። ይህም ተማሪዎች በፀጥታ እንዲቀመጡ ከሚጠበቅባቸው ጥቂት አገሮች በጣም የተለየ ነው።

ትምህርት ቤቶች ማህበረሰቦችም ናቸው። ተማሪዎች ለአዋቂዎች እና እርስ-በርሳቸው መከባበርን በማሳየት አዎንታዊ ስነምግባር እንዲኖራቸው ይጠበቃል።

በርካታ ትምህርት ቤቶች በአመቱ መጀመሪያ ጉባኤ በማካሄድ ስነምግባር እና ሌሎች የሚጠበቁትን በተመለከተ ይወያያሉ። ተማሪዎች ሁለት ሰነዶች ያገኛሉ፡- የMCPS የሥነምግባር ደንብ እና ለመብቶችና ለኃላፊነቶች የተማሪ መመሪያ

በMontgomery County፣ ወላጆች በልጃቸው የት/ቤት ህይወት በስፋት ይሳተፋሉ። ወላጆች ለወላጅ-መምህር ስብሰባዎች ይመጣሉ፣ በወላጅ-መምህር ማህበር ይሳተፋሉ፣ በክፍል ውስጥ የነጻ አገልግሎት ይሰጣሉ፣ በመስክ ጉዞዎች ጊዜ አስተማሪዎችን ያግዛሉ፣ እንደዚሁም በሌሎች የተማሪ ዝግጅቶች የነጻ አገልግሎት ይሰጣሉ። በማንኛውም ወቅት ቅሬታ ወይም ሀሳብ ሲኖርዎት የልጅዎን መምሀር፣ የት/ቤት ዋና ተጠሪ ወይም ሌላ ሥራ አስፈጻሚዎች ለማግኘት ነጻነት ይሰማዎ።

ተዛማጅ ተያያዦች

በትምህርት ቤት ተቆላፊ ማቆያዎች (ሎከሮች)

 
 

ተቆላፊ ማቆያ ጊዜያዊ የመጋዘን/ማስቀመጫ ቦታ ነው። ብዙ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች የግል ሎከር እንዲኖራቸው ይጓጓሉ - የራሳቸው ብለው የሚጠሩት ስፍራ! የመተላለፊያ ላይ ሎከር የጀርባ ቦርሳዎችን፣ ኮቶችን፣ መፃሀፍቶችን እና የት/ቤት መገልገያዎችን ለማስቀመጥ የተዘጋጀ ነው። ተማሪዎች በተጨማሪ የአካል ብቃት ትምህርት PE  ሲወስዱ የአካል ብቃት ትምህርት ሎከር ያገኛሉ።

ተቆላፊ ማቆያው የሚከፈተው ተከታታይ ቁጥሮችን በመጠቀም ነው። ይህም መዝጊያውን አስተማማኝ ያደርገዋል። ቁልፉን እንዴት መክፈት እንደሚችሉ ተማሪዎች እንዲያዩ ይደረጋሉ። ከዛ ለበርካታ ጊዜ መክፈትና መዝጋት ለመለማመድ እድል ይኖራቸዋል።

በተለመደ አጠቃቀም፣ በተማሪ ሎከር የሚገኙ እቃዎች የተጠበቁ ናቸው። ነገር ግን፣ ውስጡን ለማየት የግድ ከአስፈለገ፣ የት/ቤት ሰራተኞች ያለተማሪው ፈቃድ ሎከሮችን እንዲያዩ ይፈቀድላቸዋል። ሎከሮቹ የት/ቤቱ ናቸዉ፣ ስለሆነም ፍጹም የግል ነጻነት አያስተማምንም። 

የአካል ማጠናከርያ ትምህርት የሆኑ ስልጠናዎች የሚወስዱ ተማሪዎች የአካል እንቅስቃሴ  ልብሶች አንዲቀይሩ ያስፈልጋል። የPE ሎከሮች በPE ክፍለ ጊዜ የተማሪውን መደበኛ ልብሶች እና ሌሎች የግል ነገሮችን ይይዛሉ።

ሎከሮች ትንሽ ናቸው፣ ስለሆነም ተማሪዎች በውስጣቸው ሊያስቀምጡባቸው የሚችሏቸው ነገሮች የተወሰኑ ናቸው። ተማሪዎች እራሳቸውን ወይም ጓደኞቻውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ማንኛውንም ነገር ሎከራቸው ውስጥ ማስቀመጥ የለባቸውም።

ተዛማጅ ተያያዦች

የቤት ሥራ

 
 

የቤት ሥራ አስተሳሰብ ከአንድ ባህል ወደሌላው ባህል ይለያያል። ለምሳሌ፣ በፊንላንድ፣ ብራዚል እና ኮስታሪካ፣ ተማሪዎች ከት/ቤት ውጭ በጣም ትንሽ ሥራ ነው የሚሰሩት። እንደዚሁም፣ በሻንጋይ፣ ሩሲያ እና ጣሊያን፣ ት/ቤቶች በእርግጥ በየቤት ሥራ ላይ ያተኩራሉ። አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ት/ቤቶች በእነኝህ መካከል ላይ ይገኛሉ።

ተዛማጅ ተያያዦች