Important Message from the MCPS School System Medical Officer

Thursday, Dec. 15


በአሁኑ ጊዜ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጠን “ዝቅተኛ” የማህበረሰብ ስጋት ደረጃ ላይ ቢሆንም፣ ማንኛውም የወረርሽኙ መጨመር አሳሳቢ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል የሚሻ ነው። እንደ ማህበረሰብ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ የጋራ የጤና አጠባበቅ መገልገያዎቻችንን እና በጣም ተጋላጭ የሆኑትን የማህበረሰብ አባሎቻችንን ለመጠበቅ ይረዳል።
በተለይም ከባድ ሕመምን የመሳሰሉ በመተንፈሻ አካላት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ልንወስዳቸው የምንችላቸው በርካታ እርምጃዎች አሉ፦

  1. ክትባቶችን በየወቅቱ መውሰድ

የዚህ አመት የኢንፍሉዌንዛ (ፍሉ) ክትባት እና ሴፕቴምበር ላይ የፀደቀው አዲሱ የኮቪድ-19 ቡስተር ክትባት ሁለቱም አሁን ካሉት ቫርየንቶች ለመከላከል የሚረዱ ናቸው። ሁለቱንም ክትባቶች መውሰድ ከባድ በሽታን ለመከላከል የሚረዱ ስለሆነ 6 ወር እድሜ ያላቸው ድረስ ክትባቶቹን እንዲወስዱ ይፈቀድላቸዋል። የመጨረሻውን የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰዱ 2 ወራት ሞልቶ ከሆነ፣ አዲሱን ቡስተር ክትባት መውሰድ ይችላሉ።

  1. የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ቫይረሶችን ስርጭት ለመከላከል የጤና አጠባበቅ ልማዶችን መከተል ያስፈልጋል

በጥሩ ሁኔታ እጅ መታጠብ፣ ሳል እና ማስነጠስ ሲኖር ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ መሸፈን፣ብዙ ሰዎች የሚጋሩት እና ከፍተኛ የሰዎች ግንኙነት ያላቸውን ቦታዎች ማጽዳት እና ሲታመሙ ከሌሎች መራቅ ስርጭቶችን ለመከላከል ይረዳል።

  1. ተጋላጭነት ባለባቸው ቦታዎች ላይ የኢንፌክሽን ስርጭትን ለመከላከል ጭምብል ያድርጉ

 የካውንቲአችን ጤና ዲፓርትመንት ቤት ውስጥ በተጨናነቁ ቦታዎች በጥሩ ሁኔታ ተስማሚ የሆነ የፊት መሸፈኛ/ጭምብል መጠቀምን በጥብቅ ይመክራል። ኮቪድ-19 ካለብዎት ወይም በቅርበት ከተጋለጡ፣ እባክዎን CDC ራስን ማግለል እና ለበሽታ መጋለጥ መመሪያዎች መሰረት ጭምብል ያድርጉ። በአካባቢው ወረርሽኝ እየጨመረ ከሄደ ሰራተኞች እና ተማሪዎች በጊዜያዊነት ጭምብል እንዲያደርጉ ሊጠየቁ ይችላሉ።

  1. ምልክቶች ካሉዎት ወይም የተጋለጡ ከሆነ የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ

ምልክቶቹ የኮቪድ-19 ወይም ሌላ ጉንፋን መሰል በሽታ መሆናቸውን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ምርመራ ማድረግ የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት አስፈላጊው መንገድ ነው፣ አስፈላጊ ከሆነ የህክምና እንክብካቤ ሊያደርጉ እና ቫይረሱን ወደ ሌሎች ከማስተላለፍ ለመቆጠብ ይረዳቸዋል። የምርመራ ውጤታቸው ፖዚቲቭ የሆነ ሰራተኞች እና ተማሪዎች MCPS online tool/ኦንላይን ሪፖርት በመጠቀም የምርመራ ውጤታቸውን ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። ወረርሽኝ በትምህርት ቤቶቻችን ሲከሰት የምርመራ ውጤቶችን ሪፖርት ማድረግ ወረርሽኞችን ለመከታተል እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመቀነስ እርምጃዎችን እንድንወስድ ይረዳናል።

  1. በጉንፋን/ፍሉ ወይም ኮቪድ-19 ኢንፌክሽን ከፍተኛ ስጋት ካጋጠመዎት ወዲያውኑ ህክምና ይውሰዱ።

በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ከፍተኛ ተጋላጭነት ላይ ያሉ ሰዎች አስቀድመው መመርመርን በጥብቅ ያስቡበት እና የመተንፈሻ አካል ህመም ምልክቶች ካላቸው ከጤና ባለሙያ ምክር ይጠይቁ። ውስብስብ ወይም ከባድ በሽታን ለመከላከል የሚረዱ ሕክምናዎች ስላሉ ህክምናዎቹ ቀደም ብለው ሲሰጡ በጣም ይረዳሉ።




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools