2022-2023 ት/ቤቶችን እንደገና ስለመክፈት የማህበረሰብ መልእክት

August 18, 2022

የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰቦች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎችን ማህበራዊ፣ ስሜታዊ እና አካዳሚያዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኞች ነን። ይህ ቁርጠኝነት በአስተማሪዎች፣ በአስተዳዳሪዎች፣ በአገልግሎት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ በወላጆች እና በማህበረሰቡ በጋራ የሚከናወን ነው። ይህ ደብዳቤ በ2022-2023 የትምህርት አመት ት/ቤቶች እንደገና ስለሚከፈቱበት መመሪያ ይሰጣል።

የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ጤና እና ደህንነት ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ምንም እንኳን ኮቪድ-19 አሁንም ከእኛ ጋር ቢሆንም፣ MCPS ለሁሉም ተማሪዎቻችን በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል በመገኘት ትምህርት ለመስጠት ቀጣይ ቁርጠኝነት አለን።አዲሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የህክምና ኦፊሰራችን ዶ/ር ፓትሪሺያ ካፑናን (Dr. Patricia Kapunan) ስለ ኮቪድ-19 መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ መላውን የት/ቤቶች ማህበረሰቦቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ይሠራል። 

ማወቅ ያለብዎት
የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC)፣ የሜሪላንድ ስቴት የጤና ዲፓርትመንት እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ት/ቤቶች ዳግም በሚከፈቱበት ወቅት አዳዲስ ምክረሃሳቦችን ለመስጠት የጤና እና የደህንነት የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሳሰድ መመሪያ ተሻሽሏል።
በትምህርት ቤቶች ውስጥ የኢንፌክሽን ስርጭትን ለመከላከል የሚረዱ ዋና ዋና የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄዎች፣ በደንብ እጅ መታጠብ እና ሲታመሙ ቤት ውስጥ መቆየት፣ የመሳሰሉት የኮቪድ-19 ስርጭትን የመከላከል ስልት ይተገበራል። ስለ ኮቪድ-19 ሳይንስ እና መረጃዎች እየታዩ አዝማሚያው ሲቀየር የኮቪድ-ተኮር ስትራቴጂዎች፣ ምክረሃሳቦች እና መስፈርቶች በትምህርት አመቱ ሊለወጡ ይችላሉ።

በኮቪድ-19 የመከላከል ስልታችን ውስጥ ያልተለወጠው ነገር ምንድነው?

  • ክትባት መውሰድ፡ ክትባት በኮቪድ-19 ኢንፌክሽን ምክንያት ከሚያስከትልብን ከባድ በሽታ ለመከላከል ወሳኝ ስልት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከ CDC ስለሚመከሩት ክትባቶች ብቁ የሆኑ ግለሰቦች ወቅታዊ መረጃ እንዲኖራቸው በጥብቅ ማበረታቱን ይቀጥላል፥ እንዲሁም ለሰራተኞቻችን እና ለተማሪዎቻችን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነትን እና እድሎችን ማግኘት እንዳለባቸው መደገፉን ይቀጥላል። በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ለመከታተል የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ አይጠበቅባቸውም። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች በአሁኑ ጊዜ የክትባት ማረጋገጫ ማቅረብ ወይም በህክምና መክንያት ክትባት ከመውሰድ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
  • ጭምብል ማድረግ፡ በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ መሠረት፣ በሜሪላንድ ፐብሊክ ስኩልስ ውስጥ ማስክ/ጭምብል መጠቀም ግዴታ አይደለም፣ የሆነ ሆኖ የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ዲስትሪክቶች ደህንነትን ለመጠበቅና በአካል መማርን ለማስቀጠል ጭምብልን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ሊወስኑ ይችላሉ። ጭምብሎች ለሁሉም ሰራተኞች እና ተማሪዎች ይዘጋጃሉ፤ በማንኛውም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የማህበረሰብ ስጋት ደረጃ ላይ ጭምብል መጠቀም የሚመርጡ ግለሰቦች ይደገፋሉ። በአካባቢያዊ ወረርሽኞች፣ ከፍተኛ ስጋት ባለባቸው ሁኔታዎች፣ ወይም በይበልጥ፣ የኮቪድ-19 ስርጭት በማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ጭንብል ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።

ከኮቪድ-19 የመከላከል ስልታችን ውስጥ ምን ተቀይሯል?

  • ምርመራ፡ CDC ከአሁን በኋላ K-12 ትምህርት ቤቶች መደበኛ የኮቪድ ምርመራ እንዲደረግ አይመክርም። MCPS በትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን ሳምንታዊ PCR ምርመራ አቁሟል። ፈጣን ምርመራ በትምህርት ቀን የኮቪድ-19 ምልክቶችን ለሚያሳዩ ተማሪዎች ወይም እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ወይም የት/ቤት እረፍትን ተከትሎ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለባቸው ሁኔታዎች የኮቪድ ምርመራ ማድረግ አሁንም ተግባር ላይ ይውላል።
  • ለይቶ የት/ኳራንቲንCDC ከአሁን በኋላ በኮቪድ-19 የተያዙ ግለሰቦች የቅርብ ግኑኝነት ንክኪ አላቸው ተብለው የተለዩትን ሁሉንም ተማሪዎች ወይም ሰራተኞች ኳራንቲን እንዲቆዩ አይመክርም። የክትባት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የቅርብ ግንኙነት ንክኪ ያላቸውም ቢሆኑ በአካል መማራቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ፥ምንም ምልክት እስካልታየባቸው ድረስ ኳራንቲን መቆየት አይኖርባቸውም፥ ስርጭትን ለመቀነስ ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይችላሉ።

ይህንን ዓመት ጥራት ያለው የመማር-ማስተማር ዓመት ለማድረግ ቃላችንን ስናድስ፣ ሁላችንም አንድ አይነት ግብ እና እምነት ይዘን ነው።

ሱፐርኢንቴንደንት እንደመሆኔ መጠን ሶስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች አሉኝ፡-

  • ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰብ ጋር መተማመንን መገንባት እና ዳግም መገንባት፣
  • የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነትን መደገፍ፣
  • ፍትሃዊ በሆነ መማር ማስተማር ላይ ማተኮር።

ግንኙነቶችን ማደስ ስንቀጥል እና ሁሉንም ተማሪዎች በእኩልነት ለማገልገል የታለመ ትምህርት ስንተገብር እነዚህ የትኩረት አቅጣጫዎች ወሳኝ ናቸው። የቀረው 2022-2023 ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመከፈት መመሪያ ከሌሎች የሥራችን ዘርፎች ምን እንደሚጠበቅ ይዘረዝራል፣ በተጨማሪም፡

  • ሥርዓተ ትምህርት እና ማስተማር፣ ልዩ ትምህርት እና ቨርቹወል አካዳሚን ጨምሮ
  • የማስጠናትና ማስተማር ጣልቃ ገብነት
  • የትምህርት ውጤት መስጠት፣ በትምህርት ላይ መገኘት፣ ተሳትፎ እና ተጠያቂነት
  • ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰብ የሚደረጉ ድጋፎች
  • የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ግንኙነት

አብሮ መስራት ተማሪዎቻችን ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ በጥሩ ስሜት እንዲማሩ እና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጋቸዋል። በአገሪቷ በጣም ጎበዝ እና ለማስተማር ቁርጠኛ በሆኑ ሰዎች ይደገፋሉ። ለመላው የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ የገባነው ቃል ለሁሉም ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ስኬታማ ጅማሮን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

ፎል ዳግም ስለ መክፈት ድረ ገጽ ይጎብኙ

ስለ መልሶ መክፈት መመሪያውን ያንብቡ

ከልብ

Dr. Monifa B. McKnight, Ed.D.
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools