ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ፡-

ዛሬ ቀደም ብሎ፣ ስለ ኮቪድ-19፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ RSV እና ሌሎች በማህበረሰባችን ጤንነት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ምክረሃሳቦችን በሚመለከት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጤና መኮንን ደብዳቤ ደርሶዎታል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር እንደመሆኔ መጠን፥ እነዚህ በሽታዎች በት/ቤቶች እና በስርዓተ-ትምህርት ኦፕሬሽኖች ላይ የሚኖራቸውን ተጽእኖ ለማቃለል እንዴት እየሰራን እንዳለ መግለጽ አስፈላጊ ነው። MCPS ሰዎች የሚያከናውኑት ሥራ እንደመሆኑ፥ ትምህርት ቤቶቻችን ያለምንም እንከን እንዲሠሩ ለማድረግ በአውቶቡስ ሾፌሮች፣ አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንመካለን።

ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት፡ በአውቶቡስ ማጓጓዣ መስመሮች ላይ በቂ ሰራተኞችን የማግኘት/ያለማግኘት ተጽእኖ

ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በሰዓቱ ለማጓጓዝ ቁርጠኞች ነን፣ ስለሆነም አዳዲስ የአውቶቡስ ኦፕሬተሮችን በንቃት በመመልመል እና በማሰልጠን ላይ እንገኛለን። ከበሽታ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ብዙ መቅረት ባሉባቸው አካባቢዎች፣ የአውቶቡስ መጓጓዣ መስተጓጎል ሊኖር ይችላል። የሰራተኞች መቅረት በታቀደላቸው መስመሮች ላይ ተጽእኖ በሚያሳድርበት ጊዜ፣ ስለዘገዩ ወይም ስለተሰረዙ የአውቶቡስ መስመሮች ለማሳወቅ ከቤተሰቦች ጋር መገናኘታችንን እንቀጥላለን። ቤተሰቦች ከተማሪ ትምህርት ቤት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል፣ እና ስለሚዘገዩ እና ስለተሰረዙ የአውቶቡስ መስመሮች መረጃ MCPS የትራንስፖርት ወቅታዊ መረጃ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።

ትምህርት የመማር መቆራረጥን መቀነስ

የጤና መኮንኑ ዛሬ ቀደም ብለው እንደገለጹት፣ MCPS በመደበኛው የትምህርት ቤቶች ተግባራት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ በርካታ ነገሮችን ይቆጣጠራል። ደህንነታቸው የተጠበቀ ጤናማ የመማሪያ አካባቢዎችን ለመጠበቅ እንዲረዳ፣ MCPS ስለ ማንኛውም የአሠራር መስተጓጎል፣ የሰራተኞች መቅረት እና አስፈላጊ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ እርምጃዎችን ጨምሮ፣ ከተለመደው መጥፎ የአየር ሁኔታ መግለጫዎች በተጨማሪ ለቤተሰቦች ለማሳወቅ ይጥራል።

ጤናማ የአየር ጥራትን ማረጋገጥ

በህንፃዎቻችን ውስጥ የአየር ማናፈሻ እና የቤት ውስጥ አየር ጥራትን ለማሻሻል ጥረታችንን እንቀጥላለን። HVAC ማጣሪያዎችን ማሻሻል በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተጠናቋል፣ HVAC የአየር ማጣሪያ ሲስተም ለረዥም ጊዜ መስራታቸውን ይቀጥላሉ። MCPS ኮቪድ-19 እና ሌሎች በት/ቤቶቻችን ውስጥ ያሉ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ለመከላከል በበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከል (CDC) የተቀመጠውን የትምህርት ቤት አየር ማጣሪያ ምክሮችን አሟልቷል። ስለ አየር ማጣሪያዎችና አየር ማጽጃዎች እና ሌሎች የኮቪድ-19 መከላከያ ስልቶች ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።

ልጆቻችሁን በሰላም ወደ ትምህርት ቤት ለማድረስ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት በምንጥርበት ጊዜ ስለሚያደርጉልን ቀጣይ ድጋፍዎ እና ቁርጠኝነትዎ እናመሰግናለን።

ከልብ

M. Brian Hull
Chief Operating Officer
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools