አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 26


Fentanyl Awareness: Family Forum Set for Jan. 28

1. ስለ "Fentanyl" ለቤተሰብ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ለጃንዋሪ 28 ተዘጋጅቷል።

ስለዚህ ገዳይ መድሃኒት አደገኛነት ለመወያየት Montgomery Goes Purple ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ቤተሰቦች ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 28 እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ተወያዮች ስለ ፌንታሊን ዕፅ / fentanyl አደገኛነት እና ስርጭት፣ ስለተማሪዎች መከላከያ መሳሪያዎች እና መከላከያ ምክንያቶች እና ስለህክምና ግብዓቶች ጠቃሚ መረጃን ያካፍላሉ። ዝግጅቱ ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ጠዋት 9:30 .–11:30 a.m. ይካሄዳል፣ 22500 Wims Road in Clarksburg። እባክዎ ይመዝገቡ።. በተጨማሪም ዝግጅቱ MCPS ዋናው ገጽ (MCPS homepage) ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። .


Free SAT Prep for High School Students Available Now

2. እያደጉ ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀማሪ እና ተመራቂዎችን ስለ እናንተ ስራ ቦታ እና የስራ መስክ እንዲማሩ እርዷቸው።

ለ Summer RISE 2023 ፕሮግራም በሁሉም የስራ ዘርፎች፣ በተለይም በስነ-ጥበባት እና መዝናኛ፣ አርክቴክቸር፣ ባዮሳይንስ፣ የንግድ አስተዳደር፣ የሳይበር ደህንነት፣ ምህንድስና፣ ጤና አጠባበቅ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ ህግ እና የእንስሳት ህክምና አገልግሎቶች ላይ፣ MCPS አዘጋጆችን/አቅራቢዎችን እየፈለገ ነው። Summer RISE ተማሪዎችን ስለ የስራ እድሎች እንዲማሩ ለመርዳት በ MCPS የተጀመረ ፕሮግራም ነው። በአካል በመገኘት፣ በቨርቹዋል ወይም ከሁለቱ በተቀናጀ መንገድ በጁን 26 እና በጁላይ 28 መካከል ባሉት ቀናት ተሞክሮ ለመስጠት ፍላጎት ካለዎት፣ ዛሬውኑ ይመዝገቡ። ምዝገባ አርብ፣ አፕሪል 14 ላይ ይጠናቀቃል።ለበለጠ መረጃ፣ www.MCPS-SummerRISE.org ይጎብኙ። .


Kids Day Out Set for Jan. 27

3. MCPS አስተማሪዎችን፣ አስተዳደሮችን፣ ድጋፍ ሰራተኞችን እና ሌሎችንም እየቀጠረ ነው

በአካል በመገኘት የሚደረግ የአስተማሪ ስራ አውደ ርዕይ ሰኞ፣ ጃንዋሪ 30 ላይ ከከሰአት 5-7 p.m. በ 15 W. Gude Drive in Rockville ይካሄዳል። ዲስትሪክቱ በጣም ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች የስራ ግብረ-ሀይሉን እንደ አስተማሪ ሆነው በ2023-2024 ትምህርት አመት እንዲቀላቀሉ እየፈለገ ነው። እርስዎ ወይም የምታውቁት ሰው ፍላጎት ካላው/ት፣ እባክዎን ምላሽ ስጡን (RSVP)።.

በተጨማሪም፣ የዋትኪንስ ሚል (Watkins Mill) ዳይሬክተሮች በስብስብ/ክላስተር ውስጥ በሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ እድሎችን ለማስተዋወቅ ሀሙስ፣ ፌብሩዋሪ 2 ላይ የተሰጥኦ/የችሎታ ምልመላ መርሀ ግብር ያዘጋጃሉ። የቅጥር መርሀ ግብሩ እየቀረበ እየመጣ ስለሆነ፣ ክላስተሩ የማስተማር፣ የአስተዳደር እና ሌሎችን ስራ መደቦች ለመሙላት እየፈለገ ነው። ፍላጎት ያላቸው መምህራን ምላሽ መስጠት (RSVP) አለባቸው። .


Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

4. የጨረቃ/ሉናር አዲስ አመትን ማክበር

በ Spark M. Matsunaga መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሚገኙ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሰራተኞች አመታዊ የጨረቃ/ሉናር አዲስ አመት ዝግጅትን እና ክብረ በአልን ጃንዋሪ 20 ላይ ታድመዋል። ከባህላዊ ውዝዋዜ እስከ አንፀባራቂ አልባሳት ድረስ፣ ከሁሉም አይነት የህይወት መስመር/አኗኗር ዘይቤ የመጡ ተማሪዎች የእስያ ባህልን እና ወጎችን አክብረዋል። ከዝግጅቱ ላይየፎቶ ስብስቦችን ተመልከቱ

የአስተማሪዎች ሊግ ለእስያ አሜሪካን እድገት (LEAAP) አመታዊ የጨረቃ አዲስ አመት የስኮላርሺፕ እራት በጃንዋሪ 18 አካሄደ። ይሄ ዝግጅት በማስተማር ዲግሪ ለመከታተል ለሚፈልጉ የእስያ እና የፓሲፊክ ደሴት አሜሪካውያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመራቂዎች የስኮላርሺፕ ገንዘብ ማሰባሰብያ ነው።


Students and Staff Spotlight This Week

5. ለእኛ ታላላቅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

የሜክ-አ-ዊሽ ፋውንዴሽን (Make-a-Wish Foundation) የMCPS የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን ኦብሪ ካምቤልን (Aubrey Campbell) ያልታሰበ ወደ ሃዋይ ጉዞ በመስጠት አስገረማት። ያልታሰበው እድል የተገለፀው በዚህ ሳምንት በክፍል ተማሪዎቿ ፊት በሬቸል ካርሰን (Rachel Carson) አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።

በ Shady Grove ፣ William H. Farquhar፣ Parkland እና Briggs Chaney መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች በ KID ሙዚየም በተካሄደው የዚህ አመት ወደ ፊትን መፍጠር ውድድር (Invent the Future Challenge) በዓል አከባበር ላይ አሸናፊዎች ተብለው ተሰይመዋል። 1,500 የሚደርሱ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በዚህ አመት ውድድር ላይ ተሳትፈዋል። የራሳቸውን ፈጠራዎች በመንደፍ፣ በአዳዲስ ፈጠራ እና ችግር በመፍታት፣ ተማሪዎች ይሄን ጥያቄ መልሰዋል፦ በዚህ ፕላኔት ላይ ህይወትን ለማሻሻል ምን ትሰራላችሁ? የአሸናፊዎችን ዝርዝር ተመልከቱ።.

ወቅታዊ መረጃዎችን እና ዘገባዎችን ለማግኘት MCPS News Center ይጎብኙ።.


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools