አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 19


Fentanyl Awareness: Family Forum Set for Jan. 28

1. ስለ "Fentanyl" ለቤተሰብ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ለጃንዋሪ 28 ተዘጋጅቷል።

ስለዚህ ገዳይ መድሃኒት አደገኛነት ለመወያየት Montgomery Goes Purple ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ቤተሰቦች ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 28 እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

በመድረኩ ውይይት የሚያቀርቡት ባለሙያዎች ስለ fentanyl አደገኛነት እና ስርጭት፣ ለተማሪዎች የመከላከያ መሳሪያዎች እና የመከላከል ሁኔታዎች፣ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህክምና ግብዓቶች ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣሉ። ዝግጅቱ ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ 9:30 a.m.–11:30 a.m. ይካሄዳል። አድራሻው፦ Clarksburg High School cafeteria, 22500 Wims Road in Clarksburg በተጨማሪም ዝግጅቱ MCPS ዋናው ገጽ (MCPS homepage) ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

የሐሙስ ዘገባ ጋዜጣዊ መግለጫ ኮንፈረንስ ከትምህርት ቤት እና ካውንቲ መሪዎች እና አቀንቃኞች ጋር ይካሄዳል
ስለ "Fentanyl" ለማህበረሰብ የዲሴምበር መልእክት
የቤተሰብ ስለ "Fentanyl" የመድረክ ውይይት ቪዲዮ


Free SAT Prep for High School Students Available Now

2. ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ነፃ SAT ዝግጅት አሁን ይገኛል።

MCPS ለተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ቨርቹዋል የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜዎችን የእያንዳንዱን ተማሪ ፍላጎት ለማሟላት FEV Tutor ጋር በመተባበር ለማቅረብ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከአሁን ጀምሮ እስከ ማርች ድረስ ነጻ የስድስት ሳምንት ኮርስ ለመውሰድ መመዝገብ ይችላሉ።  FEV Tutor ኢሜል ያድረጉ ወይም ጥያቄ ካለዎት 855-763-2607 ይደውሉ።

ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚኖሩበት ጊዜ፦ 
ሰኞ–ዓርብ፥ 7 a.m.–10 p.m., ቅዳሜ፥ 8 a.m.–4 p.m. እና እሑድ ቀናት 11 a.m.–10 p.m.


Kids Day Out Set for Jan. 27

3. የልጆች ቀን ጃንዋሪ 27 ይካሄዳል

አርብ፥ ጃንዋሪ 27 ትምህርት ቤት ዝግ ሲሆን ለልጅዎ የሆነ ነገር ይፈልጋሉ? በሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ ስለሚካሄድ የአንድ ቀን አስደሳች እና ክትትል የሚደረግበት ዝግጅት ምን ይመስልዎታል። ሁሉም MCPS ተማሪዎች በምዝገባ ወቅት MCPSkid2022 የሚለውን ኮድ በመጠቀም ነፃ የትምህርት እድል ማግኘት ይችላሉ። የተለያዩ አይነት እንቅስቃሴዎች/አክቲቪቲዎች 8:30 a.m. እስከ 4 p.m. ይካሄዳሉ።

ለበለጠ መረጃ እና ቦታዎችን ለማወቅ ActiveMontgomery.org ይጎብኙ ወይም 240-777-6840 ይደውሉ።


Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

4. MCPS ፀረ-ዘረኝነት ስርዓት ኦዲት ላይ የማህበረሰብ ውይይቶች ይካሄዳሉ

"The Latino Student Achievement Action Group (LSAAG)" የላቲኖ የተማሪ ስኬት አክሽን ቡድን (LSAAG) ከ PODER አስተማሪዎች እና MCPS የስትራቴጂክ ተነሳሽነት ቢሮ ጋር በመተባበር መረጃዎችን ለመለዋወጥ እና ስለ MCPS ፀረ-ዘረኝነት ስርዓት የኦዲት ሪፖርት ከሂስፓኒክ/ላቲኖ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የሚሰጡትን አስተያየቶች ለማዳመጥ ቨርቹወል ስብሰባዎችን ጃኑወሪ 23 ያካሂዳል። ተማሪዎች 5:30-6:45 p.m. የሚሰበሰቡ ሲሆን ከቀኑ 7-8፡15 p. m. የወላጆች ስብሰባ በስፓኒሽኛ ይካሄዳል። ተማሪዎች እና ወላጆች እዚህ መመዝገብ ይችላሉ።


Students and Staff Spotlight This Week

5. የዚህ ሳምንት የተማሪዎች እና የሰራተኞች ትኩረት

በሙዚቃ መምህር ኤሚ ቫኔክ/Amy Vanek የሚመራው የክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ፣ እሮብ ጃንዋሪ 18፣ አናፖሊስ በተካሄደው የሜሪላንድ ስቴት ገቨርነር ዌስ ሙር/Wes Moore ታሪካዊ የምርቃት ፕሮግራም ላይ የመዝሙር ትርኢት አሳይቷል።

ወቅታዊ መረጃዎችን እና ዘገባዎችን ለማግኘት MCPS News Center ይጎብኙ።


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools