አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 12

    inclusive books

  1. ዕድሜ-ተመጣጣኝ እና የክፍል ደረጃን የሚያካትቱ መጽሐፍት ወደ MCPS ትምህርት ቤቶች ሊላኩ ነው
    ሥርዓተ ትምህርታችን ሁሉንም ተማሪዎች ያካተተ መሆኑን ለማረጋገጥ ባለን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት፣ MCPS በክፍል ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ LGBTQ+-inclusive ጽሑፎችን አጽድቋል። የትምህርት ቤቶቻችንን ማህበረሰብ ብዝሃነት እና አለምን የሚያንፀባርቁ ታሪኮችን ማንበብና ማወቅ ለሁሉም ሰው መከባበርን እና መተሳሰብን ያበረታታል። እንደ ሁሉም የስርዓተ ትምህርት መርጃዎች፣ መምህራን ፅሑፎቹን የማስተማሪያ አካል አድርገው እንደሚጠቀሙበት ይጠበቃል። መምህራን የትኛውን ቁሳቁስ መጠቀም እንዳለባቸው ምርጫ ማድረጋቸው መደበኛ አሰራር በመሆኑ ቁሳቁሶቹን መጠቀም አማራጭ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። የጸደቁ ጽሑፎች አገናኝ ሊንክሥርዓተ-ትምህርት ክፍል ውስጥ ተካትቷል።MCPS LGBTQ+ ድረ-ገጽ የጸደቁ ጽሑፎችን ዝርዝር ያካትታል።

    MLK Day
  2. ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር Martin Luther King Jr. ቀን አከባበር እና አገልግሎት የሚሰጥበት እድል
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ አመታዊ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የልደት ቀን ክብረ በዓል ሰኞ፣ ጃንዋሪ 16 ቀን 4–5:30 p.m.በ ስትራትሞር/Strathmore የሙዚቃ ማእከል ይካሄዳል።
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኞች ማእከል አመታዊ የማርቲን ሉተር ኪንግ - MLK አገልግሎት ጃንዋሪ 16, ከቀትር እስከ 3 ፒ.ኤም በዚህ አድራሻ፦ Bethesda North Marriott Hotel and Conference Center, 5701 Marinelli Road in North Bethesda" ያስተናግዳል። ተማሪዎች ተገኝተው ከተሳተፉ እስከ ሶስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። የማርቲን ሉተር ኪንግ "MLK" አገልግሎት በሚከበርበት ቀን ዝግጅት ላይ ለመገኘት የአካባቢ እና የርቀት ቦታዎች ሙሉ ዝርዝር እዚህ ይገኛል።

    virtual college meeting
  1. ጃንዋሪ 19 ስለኮሌጅ ክፍያ ቨርቹዋል ስብሰባ ይካሄዳል።
    ልጅዎ በጊዜያዊ የተጠባባቂ ሁኔታ (TPS) ካለ(ች)፣ የዘገየበ(ባ)ት ከሆነ (DACA) ወይም ለሜሪላንድ ድሪም አክት/Maryland Dream Act ብቁ ከሆነ(ች)፣ MCPS እና ሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጋራ ባዘጋጁት ቨርቹወል መድረክ ላይ ስለ ኮሌጅ ክፍያ አማራጮች ጥያቄዎችዎን እንዲጠይቁ ተጋብዘዋል። ቨርቹዋል ውይይት ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 19 ቀን 6 p.m.  ላይ በስፓኒሽኛ ይካሄዳል።ጥያቄዎችን ያቅርቡ እና በሚከተለው በይነመረብ ላይ ይመዝገቡ፦https://bit.ly/Pagarporlauniversidad

    spotlight
  1. የዚህ ሳምንት የተማሪዎች እና የሰራተኞች ትኩረት
    የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህር ዲዮን ጆንስ (Dion Jones) ማክሰኞ ጃንዋሪ 10 "Milken Educator Award" ትምህርት ቤት አቀፍ ደማቅ ስብሰባ ላይ ያልተጠበቀ አድናቆት ተችሮታል። በፌርላንድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሶስተኛ ክፍል መምህር የሆነው ጆንስ 2022-2023 የትምህርት ዘመን "Milken Educator Award" ሽልማት ለመቀበል እና በሜሪላንድ ስቴት ተመራጭ የሆነ ብቸኛውን ሽልማት ለማግኘት በመላ አገሪቱ ካሉ 40 የመጀመሪያ ደረጃ አስተማሪዎች መካከል አንዱ ነው።
    news
    አራት የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች "Regeneron Science Talent Search Scholars" እውቅና ተሰጥቷቸዋል።ፍለጋው ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየሮች የሀገሪቱ አንጋፋ እና በጣም ታዋቂ የሳይንስ እና የሂሳብ ውድድር ነው። Nathan Shan, Josh Wang, and Celine Wu ከሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አንድሪው ዩዋን ከፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንኳን ደስ አላችሁ!
  1. MCPS በዘገባዎች ላይ

ወቅታዊ መረጃ እና ዜና ለማግኘት፦ MCPS News Center ይጎብኙ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools