5 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 15


COVID-19/Respiratory Illnesses Status Update

1. ስለ ኮቪድ-19/የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎች

በካውንቲው የጤና መምሪያ መረጃ መሰረት የኮቪድ-19 ስርጭት መጠን በዋሽንግተን ዲሲ ሪጅን ውስጥ እየጨመረ ነው። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ፣ ከምስጋና ቀን በዓል (Thanksgiving) ከተመለሱ በኋላ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተገመተውን ያህል ጭማሪ አይተናል። ወደ ዊንተር ዕረፍት እየተቃረብን ስለሆነ ጥቂት ማሳሰቢያዎች እነሆ፡-


MCPS Students Dually Enrolled at Montgomery College Will No Longer Be Charged Tuition

2. በሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጣምራ ትምህርት/Dually የተመዘገቡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ አይጠየቁም።

በቅርብ ጊዜ በሜሪላንድ ህግ በተደነገገው ለውጥ መሠረት በጣምራ-ምዝገባ ፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ የሚመዘገቡ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ አይጠየቁም። የሞንትጎመሪ ኮሌጅ በዚህ ፎል ለተወሰዱ የኮሌጅ ኮርሶች የከፈሉ ተማሪዎችን ክፍያ ይመልሳል። በቀሪው የትምህርት ዓመት የኮሌጅ ኮርሶችን የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ አይከፍሉም፣ ነገር ግን ለሌሎች የኮሌጅ ወጪዎች፣ የመማሪያ መጽሐፍት ወይም ሌሎች ክፍያዎችን ሊጠየቁ ይችላሉ። 2023-2024 የትምህርት አመት ጀምሮ፣ ሁሉም ብቁ ተማሪዎች የተፈቀደላቸውን የኮሌጅ ኮርሶች ያለምንም ወጪ መውሰድ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ FAQ ገጽ ይመልከቱ።.


Tune In to Operating Budget Presentation Live on Dec. 19

3. ዲሴምበር 19 በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፈውን የሥራ ማስኬጃ ባጀት አቀራረብ ይከታተሉ

ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ሰኞ ዲሴምበር 19 የበጀት ዓመት 2024 በማህበረሰብ የተመከረበትን የሥራ ማስኬጃ በጀት ገለጻ ይሰጣሉ። ዲስትሪክቱ በተማሪዎች የአካዳሚክ ተሞክሮዎች፣ የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ላይ ኢንቨስት ስለማድረግ እና በአመራር ደረጃ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና ለቀጣዩ የትምህርት አመት ግቦች ወደፊት አሻግሮ ለመመልከት እንዴት እንደታቀደ ያዳምጡ። የቀጥታ ስርጭት ይመልከቱ፦ MCPS homepage ወይም MCPS TV Channels (en Español Comcast 33, Verizon 35, RCN 88).


SPOTLIGHT: New York Times Bestselling Author Kwame Alexander Visits North Bethesda Middle School

4. ትኩረት፡ የኒውዮርክ ታይምስ ምርጥ ሽያጭ ደራሲ ክዋሜ አሌክሳንደር (Kwame Alexander) የኖርዝ ቤተዝዳ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤትን ጎብኝቷል።

የኖርዝ ቤተዝዳ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በክዋሜ አሌክሳንደር (Kwame Alexander) ገጣሚ፣ አስተማሪ እና የኒውዮርክ ታይምስ ምርጥ ሽያጭ 36 መጽሃፎች ደራሲ ጉብኝት ተደስተዋል። ተማሪዎች ስለ መጽሃፎቹ፣ የአጻጻፍ ዘይቤ እና Disney+ ላይ ስለሚወጣው አዲሱ ተከታታይ የቲቪ አውደ ርእይ ጥያቄዎችን ጠይቀዋል።


5. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በዘገባዎች/በዜና ማሠራጫዎች ላይ

ወቅታዊ ዜናዎችን እና መረጃዎችን ለማግኘት፦ MCPS News Center ይጎብኙ።.


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools