ሐሙስ፣ ዲሴምበር 1 መታወቅ የሚገባቸው ጉዳዮች

ለሀሙስ ዲሴምበር 1 መታወቅ ያለባቸው ስድስት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ እግር ጉዞ የትምህርት ቤት አውቶቡስ ተነሳሽነት፣ ስለ መጪው የአእምሮ ጤና መድረክ፣ በሥራ ማስኬጃ በጀት ክዋኔ ሂደት እንዴት እንደሚሳተፉ፣ የረጅም ጊዜ የትምህርት ቦርድ አባል ዶ/ር ጁዲዝ ዶካ (Dr. Judith Docca) ጡረታ መውጣት መረጃ ፣ ስለ መጥፎ የአየር ሁኔታ መረጃ ማሳሰቢያዎች፣ እና ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች በዚህ አመት የስቴት ሻምፒዮና ስለ መድረሳቸው መረጃዎች ተካተዋል።

 1. walkers"Walking School Bus Initiative" ወደ ትምህርት ቤት የእግር ጉዞ አውቶቡስ ተነሳሽነትን MCPS እና MCDOT በትብብር ያካሄዳሉ።
  MCPS የትራንስፖርት ዲፓርትመንት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (MCDOT) ወደ ት/ቤት የሚወስዱ መንገዶችን በመፈለግ ህጻናት በክትትል ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ እና ሲመለሱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚያገኙበት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስደሳች መንገድ ላይ ለማገዝ በጎ ፈቃደኞችን ይፈልጋሉ።

  እግር ጉዞ ትምህርት ቤት አውቶቡስ መርሃ ግብር ተማሪዎች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ጎልማሶች እየተመሩ በተመደበላቸው መንገድ እንዲራመዱ ያስችላቸዋል፣ ልጆችን አስቀድሞ በተመረጠ መንገድ ከተዘጋጁ ፌርማታዎች ላይ በማንሳት ወደ ትምህርት ቤት ይወስዷቸዋል።

  ፍላጎት ያላቸው ጎልማሳ በጎ ፈቃደኞች ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ እና ይህን ፕሮግራም በትምህርት ቤት ማህበረሰብ ውስጥ ለመጀመር MCPS እና/ወይም MCDOT ተወካይ ጋር ለመነጋገር መመዝገብ ይችላሉ። በራሪ ወረቀት/FLYER
 1. story mattersMCPS ስለ አእምሮ ጤንነት የውይይት መድረክን ያዘጋጃል
  MCPS ማክሰኞ ዲሴምበር 6 ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የአእምሮ ጤና መድረክ ያስተናግዳል። " Your Story Matters" ርእሱ በአፍሪካ አሜሪካዊያን፣ በኤዥያውያን እና ስፓኒሽ ማህበረሰቦች ላይ ባለው ተጽእኖ ላይ ያተኩራል። ዝግጅቱ የፓናል ውይይቶችን እና አውደ ጥናቶችን ያካትታል። ዝግጅቱ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Richard Montgomery High School) 6-8፡30 p.m. በአካል ተገኝቶ ይካሄዳል። 6 p.m. ላይ በሮች ይከፈታሉ። RSVP
 1. budget processበዲስትሪክት የስራ ማስኬጃ በጀት ሂደት ውስጥ የመሳተፍ ቀጣይ እድል
  ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት (Dr. Monifa B. McKnight) እና MCPS የበጀት እና የፋይናንስ መሪዎች ሶስቱን የበጀት መረጃ ክፍለ ጊዜዎች በዚህ ሳምንት አጠናቅቀዋል። የትምህርት ቤት ማህበረሰብ አባላት እና ባለድርሻ አካላት በጀት እንዴት እንደሚሰበሰብ እና ገንዘቡ ከየት እንደሚመጣ እንዲገነዘቡ ለመርዳት በአካል እና ቨርቹወል ስብሰባዎች ተካሂደዋል። ተሳትፎዎን ለመቀጠል፣ ጃኑዋሪ 11 እና ጃንዋሪ 17 ስለ ስራ ማስኬጃ በጀት በሚካሄድ ውይይት ላይ በትምህርት ቦርድ የህዝብ አስተያየት መስጫ ላይ በመገኘት  በአጠቃላይ የካውንቲ በጀት ምደባ ውስጥ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገን በተሻለ ለመረዳት በካውንቲ አስተዳደርየበጀት መድረኮች ላይ መገኘት ይችላሉ። የኖቬምበር 28 የበጀት ውይይት መድረክ ይመልከቱ
 1. docca retirementዶ/ር ጁዲዝ ዶካ (Dr. Judith Docca) ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ለማህበረሰቡ ከ 49 ዓመታት በላይ ካገለገሉ በኋላ ጡረታ ወጥተዋል
  MCPS የረዥም ጊዜ የትምህርት ቦርድ አባል ዶ/ር ጁዲዝ ዶካን የጡረታ መውጫ ስነ ስርአት አካሄዷል። ዶክተር ዶካ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር ስራ የጀመሩት በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ነበር። እሷም በሰብአዊ ግንኙነት ባለሙያነት፣ በሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረዳት ርእሰመምህር እና በአርጋይል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰመምህር ሆነው አገልግለዋል። ያለፉትን 16 አመታት በቦርድ አባልነት ተመርጠው አገልግለዋል። እናመሰግናለን ዶ/ር ዶካ።
 1. በከባድ የአየር ሁኔታ ጊዜ MCPS ጋር እንደተገናኙ እንዲቆዩ ማሳሰቢያ
  መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲኖር ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት፣ ዘግይቶ ስለመክፈት እና ተማሪዎች ቀደም ብለው ስለሚሰናበቱበት ሁኔታ ለማሳወቅ MCPS ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል።
  • ConnectED System፥ ኤሜይል (Email) እና አጫጭር ጽሑፍ/ቴክስት መልክቶች (Text Messages)
   የአስቸኳይ ጊዜ መገናኛ መረጃዎች በልጅዎ ት/ቤት ማህደር ወቅታዊ መሆኑን እባክዎ ያረጋግጡ።
  • AlertMCPS እና MCPS Alerta (ስፓኒሽኛ)
   ከአየር-ጋር-የተያያዙ የአስቸኳይ ሁኔታዎች እና በት/ቤት ስርአት ተፅእኖ በሚያደርጉ ሌሎች አሳሳቢ ክውነቶች ወቅት የቴክስት መልእክቶች ወይም ኢሜይሎች ከMCPS ተቀበሉ። ወላጆች በተለይ የልጆቻቸውን ት/ቤቶች የሚመለከቱ ማስጠንቀቂያዎች ለመቀበል በኮምፒውተር መመዝገብ ይችላሉ።
   AlertMCPS ተመዝገቡ
  • MCPS መነሻ ድረ-ገፅ
   www.montgomeryschoolsmd.org
  • MCPS ኬብል (ቲቪ) ቻነሎች
  • Comcast 34 (1071 HD)፥ Verizon 36 ወይም RCN 89
  • የተዘገበ/የተቀዳ መረጃ
   301-279-3673
  • MCPSን ይጠይቁ
   240-740-3000. ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽ ቋንቋ ሠራተኞች የስልክ ጥሪዎችን ይቀበላሉ።
  • ትዊተር (Twitter)፣ፌስቡክ እና ኢንስታግራም (Facebook and Instagram) በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ
   http://twitter.com/mcps
   https://twitter.com/MCPSEspanol
   https://www.facebook.com/mcpsmd
   https://www.facebook.com/mcpsespanol
   https://www.instagram.com/mcps_md
  • ያካባቢ ሬድዮና ቲቪ ጣብያዎች
 1. football teamsአስደሳች ዜና

በዚህ ሳምንት ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፉትቦል ቡድኖች ወደ ስቴት ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድር አልፈዋል!
የኩዊንስ ኦርቻርድ (QO) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 4A የስቴት ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድር አልፏል፥ እንዲሁም የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 3A የስቴት ፉትቦል ሻምፒዮና አልፏል። QO ኩዊንስ ኦርቻርድ ከቻርለስ ኸርበርት ፍላወርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ፣ ሐሙስ፣ 7፡00 p.m. ይጫወታል። ደማስከስ ከኦካዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር ቅዳሜ 7፡00 p.m. ላይ ይጫወታሉ። ሁለቱም ጨዋታዎች በአናፖሊስ በሚገኘው የባህር ኃይል-ማሪን ኮርፕ ስታዲየም ይካሄዳሉ። በዚህ አስደናቂ ስኬት ለሁለቱም ቡድኖች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools