ለሐሙስ፣ ኦክቶበር 27 ማወቅ ያለብዎት ዘጠኝ ቁምነገሮች

ለሐሙስ፣ ኦክቶበር 27 ዘጠኝ ቁምነገሮችን እነሆ! ዲስትሪክቱ የትምህርት ቤት አውቶቡሶችን በኤሌክትሪክ በሚሠሩ አውቶቡሶች ለመተካት ስላደረገው ጥረት፣ ተማሪዎች በሊተርሲ እና በሂሳብ ትምህርት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያሳዩት መሻሻል፣ ለብሔራዊ የርእሰመምህራን ወር ተማሪዎች የሚያከናውኑት የቀጥታ ሙዚቃ ልምምድ፣ ከፍተኛ የአፈጻጸም ችሎታ ያላቸው የተማሪ ሙዚቀኞች፣ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት ት/ቤት ስለሚዘጋበት ሁኔታ መረጃ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና አንዳንድ ማሳሰቢያዎች ተካተዋል።

 1. October is National Principals Month!

  1. ኦክቶበር ብሔራዊ የርእሰ መምህራን ወር ነው!

  ብሔራዊ የርእሰ መምህራን ወር ሲገባደድ፣ MCPS እንደ ፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር አሮን ሺን (Aaron Shin) ለመሣሰሉት ርእሰ መምህራን እና ረዳት ርእሰ መምህራንን አድናቆቱን ይገልጻል። ሺን (Shin) የሞንትጎመሪ ካውንቲ PTAs’ ካውንስል 2021 የዓመቱ ርዕሰ መምህር ነው። ርእሰ መምህራን በየቀኑ እንደ ባለራዕይ፣ የግምገማ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ ገንቢዎች፣ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች፣ የበጀት ተንታኞች፣ የፋሲሊቲ አስተዳዳሪዎች እና ሌሎችንም ስራዎች ሳይታክቱ ይሰራሉ።

 2. first day

  2. ትኩረት፡ የዲስትሪክቱ መሪዎች ለሁለት የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከፍተኛ የሊተርሲ እና የሂሳብ ልህቀትት እውቅና ሰጥተዋል

  Rየሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Rolling Terrace Elementary School) በሊተርሲ 39 በመቶ እና የዋሽንግተን ግሮቭ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Washington Grove Elementary School) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ማስረጃ ማዕቀፍ ሲመዘን በሂሳብ 29 በመቶ ነጥብ አስመዝግበዋል። ይህን የመሰለ ውጤት ሊገኝ የቻለው በርዕሰ መምህራን ጄሲካ ፓላዲኖ እና በዶ/ር ኤሚ ጄ. (Jessica Palladino and Dr. Amy J. Alonso) ከፍተኛ ጥረት በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል።

 3. first day

  3. በዘገባ የቀረበ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአሜሪካ በርካታ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ተጠቃሚ መሆኑን አክብሯል

  ዲስትሪክቱ ኦክቶበር 24 በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሀገሪቱ በርካታ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የትምህርት ቤት አውቶቡሶችን የማሠማራት ዝግጅት አድርጓል። በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አውቶቡሶች አጠቃቀም የነዳጅ ወጪን እና የትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ የካርበን ብክለት ይቀንሳል። ውጥኑ ከሃይላንድ ኤሌክትሪክ ፍሊትስ (Highland Electric Fleets) ጋር በመተባበር እየተተገበረ ነው። ቪድኦ ይመልከቱ

 4. first day

  4.የጨዋታ እና የውድድር ወቅት እየተቃረበ ነው።

  የፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጎልፍ ቡድን በዚህ ሳምንት 2A-1A የስቴት ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የስቴት ሻምፒዮና አሸንፏል። ቅዳሜ ኦክቶበር 29 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የቼርሊዲንግ ሻምፒዮና ውድድር በሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያበረታቱዎትን ተማሪ-አትሌቶችን ይደግፉ እና ያበረታቱ። ለእያንዳንዱ ዲቪዝዮን ትኬቶች እዚህ ይገኛሉ። የሚወዷቸውን ቡድኖች ሁሉንም MPSSAA State Championship Centralጣቢያ ላይ ይከታተሉ።

 5. first day

  5. የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ስትራትሞር ላይ የብሉዝ ሙዚቃን (Blues Music) ያቀርባሉ

  በዲስትሪክቱ ከ12,000 የሚበልጡ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች በዚህ ሳምንት በስትራትሞር በሚገኘው የሙዚቃ ማእከል የቀጥታ ሙዚቃ ኮንሰርቶች እያቀረቡ ነው። ተማሪዎቹ ለእነዚህ ኮንሰርቶች በመዘጋጀት የብሉዝ ሙዚቃን በትምህርት ቤት ሲያጠኑ ቆይተዋል። ሁሉም የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች በኖቬምበር ላይ ስትራትሞርን ይጎበኛሉ።

 6. first day

  6. MCPS ኖቨምበር 2 ቨርቹወል የስርዓተ ትምህርት ምሽት ያስተናግዳል

  ኖቬምበር 2 በቀጥታ ከ 6-8፡30 ፒኤም በሚቀርቡ ቨርቹወል ዝግጅት ስለ MCPS ስርዓተ ትምህርት የበለጠ ለማወቅ እድሉ እንዳያመልጥዎ። ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚያተኩሩት፥ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተዘጋጀ ሊተርሲ፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስነጥበባት በመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በሁሉም ደረጃዎች የሂሳብ ትምህርት፣ ለመመረቂያ የሳይንስ መስፈርቶች እና የሁለተኛ ደረጃ የጤና ትምህርት ላይ የተደረጉ ለውጦች በመሣሰሉት ርዕሶች ላይ ነው። ሁሉም ክፍለ-ጊዜዎች ቨርቹወል ስለሆኑ የሁሉም ዝግጅት እዚህ ይለጠፋል።ለመሳተፍ ምዝገባ አያስፈልግም እና ሁሉም ዙም አገናኝ (Zoom links) በድረ-ገጹ ላይ ባለው አጀንዳ ውስጥ ተካትተዋል።

 7. first day

  7. ትኩረት፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ሙዚቀኞች ለታዋቂ ብሄራዊ የሙዚቃ ቡድኖች ተመርጠዋል

  አራት የ MCPS ተማሪዎች ለታዋቂው ብሄራዊ የክብር ባንድ እና ብሄራዊ የክብር ኦርኬስትራ በዚህ አመት ተመርጠዋል። ሳራ ቦክ (Sara Bock)፣ የቶማስ ኤስ. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክላሪኔት ሙዚቀኛ እና ሺሱይ ቶሪ (Shisui Torii)፣ የቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፍሬንች ሆርን ሙዚቀኛ ለባንዱ ተመርጠዋል። የባሱን ሙዚቀኛ ጃክሰን በርናል (Jackson Bernal) እና ደብል ባስ ሙዚቀኛ አንደርሰን በርናል (Anderson Bernal) ከቶማስ ኤስ ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኦርኬስትራ የተመረጡ ናቸው። በሜሪላንድ ውስጥ ከተመረጡት አምስት ተማሪዎች አራቱ ከ MCPS ናቸው።

 8. first day

  8. 2022 ከፍ ባለ ድምፅ እና በኩራት የሚቀርብ የማርች ባንድ አውደ ርእይ

  ከ 2019 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የ MCPS ማርቺንግ ባንድ ትርኢት ኦክቶበር 22 በጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲካሄድ ቆይቷል። ትርኢቱ ክላርክስበርግ፣ ሴኔካ ቫሊ፣ ዋትኪንስ ሚል፣ ፔይን ብራንች፣ ኮል. ዛዶክ ማግሩደር፣ ደማስከስ፣ አልበርት አንስታይን፣ ሞንትጎመሪ ብሌየር እና ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና አዲስ በዚህ አመት፣ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የጅምላ ባንድ ዝግጅት ጀምረዋል። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ ለመጨረሻ የጅምላ ባንድ ትርኢት ተሰባስበዋል። ቪዲዮ ሊንክ (ድምጹን ከፍ ያድርጉ እና ይደሰቱ!)
  https://youtu.be/f6ee4JWMXuQ

 9. 9.የመዝጊያ ማስታወሻ፡ በመካሄድ ላይ ያሉ ማሳሰቢያዎች

  • ስም-የማይገለጽ የትምህርት ቤቶች ደህንነት የጥቆማ መስመር
   የሜሪላንድ የት/ቤቶች ሠላም ክፍት የስልክ መስመር ማንኛውንም የት/ቤት ወይም የተማሪ ደህንነት ስጋቶች ሪፖርት ለማድረግ የጠቋሚ ማንነት በምስጢር የሚጠበቅ እና ነፃ የሪፖርት ማቅረቢያ አሠራር ነው። (1-833-MD-B-SAFE / 1-833-632-7233)
   ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ..
  • ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ነጻ የማስጠናት አገልግሎት ይሰጣል።
  • የት/ቤት አውቶቡስ መስመር መሰረዝ ወይም ማዘግየት የመጨረሻ አማራጭ ውሳኔ ነው። የልጅዎ የአውቶቡስ መስመር ከዘገየ ወይም ከተሰረዘ ConnectEd መልእክት ይላካል። እርስዎ የሚገኙበትን መረጃ MCPS ፋይል ላይ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ!
   መሸፈን ያልተቻለ የአውቶቡስ መስመሮች ከአንድ ቀን በፊት ወይም በማለዳው 6፡15 a.m. ይፋ ይደረጋል። መልእክቱ የሚተላለፈው MCPS ድረገጽ እና ConnectEd መልዕክት ላይ ይላካል።
   ሽፋን ላላገኙ የአውቶቡስ መስመሮች የትራንስፖርት ዲፓርትመንት አሽከርካሪዎችን ለማግኘት ጥረት ያደርጋል። የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ በየ15 ደቂቃው እስከ ጠዋቱ 9፡30 a.m. ድረስ ይቀያየራል።
   የከሰዓት በኋላ የአውቶቡስ መስመሮችን በሚመለከት የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ 1፡30 p.m. ላይ ይወጣል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools